Thursday, August 8, 2013

የዛሬው የደሴ የተቃውሞ ውሎ


ንፁሀን በደላቸውን ለማሰማት በዳዮችም የግፍ ሴራዎችን ሲያጤኑ ከርመው ኢድ ቀን የተወሰነው ፍጥጫ በሙሊሙና በመስጂድ ነጣቂዎች በአሳሪ አሳሳሪዎች በደብዳቢ አስደብዳቢዎቹ ካድሬዎች ዛሬ ቀኑ ደርሶ መንግስታዊ እስልምና አራማጆችና ካድሬዎች ፈጥነው የሰላቱን የመጀመሪ ሶፍች በለሊት ተቆጣጠሩ፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ልክ ከዚህ በፊት እንደሚደረገው የከረጉቱ ሜዳን ሞልቶ ተቀመጠ እዚህ ጋር ነው የተሸረበው ሴራ ፡፡ የአንድ ሰፈር ሙስሊም ሊያሰግድ የማይችል ሰማይ ቢደፋ የደሴን ሙስሊም ሊይዝ እንደማይችል እየታወቀ ሙስሊሙን ለሁለት ለመክፈልና ካድሬና አህባሾችን ከጥቃጡ ለመጠበቅ ብሎም ከጠባቧ ሜዳ መውጫ እንዳያገኛ ከመስጊዱ ጎን ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ በአጥር የተከለው ጠባብ ሜዳ ላይ ህዝቡን በፖሊስና ልዩ ሀይል እየፈተሹ ማስገባት ጀመሩ፡፡ ያቺ ጠባብ ሜዳ ሞልታ ህዝቡ በአግራሞት ይመለከት ጀመር፡፡ ከኢድ ሰላት በፊት የሰላተል ጀናዛ ስግደት ነበር፡፡ 

የተከለለችው ሜዳ ውስጥ ያሉት ወንድሞች ብቻ ሰላቱን ቆሙ ወዲያው የኢዱን ሰላት ኢማሙ ሲጀምሩ ሰፊውና ነባሩ ሜዳ ላይ የተሰበሰበው ህዝብ ተክቢራ ጀመረ በዛች ጠባብ መሬት ላይ ከፊሉ የኢዱን ሰላት ጀምሯል ከፊሉ የወንድሞቹን የእህቱን ቁጣን ያዘለ የተቃውሞ ድምፅ ሰምቶ ከጠባቧ በአጥር የተከበበች ሜዳ መውጣት ጀመረ፡፡ ኢማሙ ሰላቱን ቀጥለዋል ሙስሊሙም ልዩ ልዩ የተቃውሞ መልዕክቱን እያሰማ ቆይቶ ለዲናችን እንሞታለን የሚለው ለሙስሊም ጥላቶች መሪር ቃል ሲሰሙ የጭምብል ለባሾች ልዩ ሀይል ወዲያው ከየት እንደመጡ ሳይታወቅ ሙስሊሙን መክበብ ጀመሩ ከመጡት ቁጥር አንፃር ሙስሊሙን መክበብ አይደለም ከምንም አይገቡም አንዳንድ ወንድሞች በድንጋጤ መሮጥ ጀመሩ….. አስለቃሽ ጭስ መተኮስ ተጀመረ…. ሁሉም ነፍሴ…… ነፍሴ……. ሰው በሰው ላይ መረማመድ ጀመረ፡፡ የሴቶች እና የህፃናት ጮኸት ምድሪቱን አናወጧት ወንዶች በተክቢራ…. ወደ ተራራው ….ወደ ተራራው ሩጫ ….ያንን ቀጥ ያለ ተራራ ጉልበት ያለው ወጣ፡፡ ደካማዎች ሴቶችና ህፃናት ይንከባለሉ ጀመር መርዘኞቹ ጭንብል ለባሾች ልዩ ሀይሎች ያገኙትን ጨፈጨፉ፡፡ 

በሚገር ሁኔታ በአንደኛው አቅጣጫ ከጥቃት የሚሸሸው ህዝብ ያንን ተራራ ሸለቆ ሲታገል በታጠረ ትንሽ ሜዳ የነበሩ ወንድሞች ኢማሙ እንዳሰላመቱ የቀለተ ተቃውሞቸውን እያሰሙ ከአጥሩ ወጡ ህዝቡን እንደ ውሻ የሚያሳዱ ጭንብል ለባሽ ተኩላዎች አስለቃሽ ጭሰ አድክሞት የጣለውን ሰው መደብደብ ትተው ወደ ቀለጠው ሁለተኛ ተቃውሞ አመሩ በዕርግጥ ከዚህ በኃላ ምን እንደተፈጠረ ይህ የሚፅፍላቹ ወንድም አያውቅም ብዙ ተራራና ሸለቆዎችን አቆራርጦ አብረውት ከነበሩ ወንድም እህቶቹ ጋር ወደ ቤቱ አምርቷል፡፡ ጦርነቱ አንዱ በመሳሪያ…. አሽባሪ የተባለው ህዝብም በቃሉ …የነበረው የኢድ ተቃውሞ በአንድ በኩል ይህን ይመስላል፡፡ ይህን ታሪካዊ ተቃውሞና ጭፍጨፋ በቪዲዮ በአላህ ፍቃድ ሰሞኑን ይቀርባል ::



 ይህ ፎቶው ላይ የምታዩት በቀይ የተከበበት አካባቢ የመኪና ጭስ አይደለም መኪናዎቹ የቆሙ ናቸው አረመኔዎቹ ህዝቡ ላይ የተኮሱት አስለቃሽ ጭስ ነው:: 
“ሰው ዋሽቶ ይታሰራል ሰው ሰርቆ ይታሰራል በኢስላም መታሰር እድሉ አይገኝም እንጂ ከተገኘ ሸረፍ ነው ያ ኢኸዋን ሞቱም ካገኘኸው ኢዝ ነው ክበር ነው፡፡” 
አላህ እርዳታውን ይስጠን!
ኢንሻአላህ ነገ እነዚህ ሰዎች እግራችን ስራ የሚወድቁበት ቀን ቅርብ ነው 

ሰብር ሰብር ሰብር
አላሁአክበር!!!

No comments:

Post a Comment