Thursday, August 29, 2013

በፍቼ በአንድነት ፓርቲ አባላት ላይ የደረሰ ድብደባ

በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው እንግልትና ድብደባ ብሎም ግድያ  እየተባባሰ መምጣቱ እውነት ከልማቱ ጋር አብሮ እያደገ የመጣው የወያኔ እርአይ ውጤት  መሆኑ ነው  ልማታዊው ወያኔ ሐይ ባይ በማጣቱ  እያደረሰ ያለው መረን ያጣ ውንብድናና እረገጣ እጅ እጅ እያለ መጥቷል ስለዚህም  ወገን ስለ ሐገሪ ስለወገኔ ይሰማኛል ያገባኛል የምትል ወግን ሁሉ የአምባ ገነኑ የወያኔ  ገዢ መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ መወገድ እንዲኖርበት የየራሳችንን አስተዋጽዎ ማድረግ ይኖርብና  ለዚህም  ምርጫችን አንድና አንድ ነው  እሱም  ወያኔ በቃህ በቃህ በማለትና እንዲሁም  በግንባር ግሮሮ ለግሮሮ እተናነቀዋለሁ ሕይወቴን ለሐገሬ መስዋት አድርጌ  እገብራለሁ  ብለው ለተነሱት ወገኖቻችንን ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሐይል ደጀን በመሆን አለንላችሁ ከናተ ጋር ነን በማለት እነሱ የተከበረ ሕይወታቸውን መስዋት ለማድረግ ሲወስኑ እኛስ ለነሱ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛው ተገቢ አስፈላጊ ነገሮችን የማቅረብ የውዴታ ግዴታ አለብን በማለት  አጋርነታችንን ማሳየት  ያስፈልጋል ።

ሐገራችን ኢትዮጵያ ለ3000 አመታት ተከብራና ተፈርታ የቆየችውን ያህል አሁን በ22 አመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ተናግረውት የማይጨርሱ ሐገራዊ ክብሯ የተዋረደበትና ሕዝቦቿ ኢ ስብአዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው ሐገር ለቀው በመሰደድና እንዲሁም በተቃዋሚ ጎራ ውስጥ ተሰልፈው እንታገላለን የሚሉትን ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው መከራና ስቃይ የምናውቀው የምናየው ስለሆነ በዚህም ከቀጠለ መጨረሻው ምን እንደሚሆን መገመት አያቅትም ።

በቅርቡ በፍቼ ከተማ ለቅስቀሳ  ከተጓዙት የአንድነት ፓርቲ አባላት መካከል  መራሹ የወያኔ መንግስት ያደረሰባቸውን ኢ ሰብአዊ ድርጊት  በማውገዝ የተሰማኝ ስሜትና በሐገራችን ኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለውን አረመኔያዊው አገዛዝ ከስር ከመሰረቱ ለማፍረስ እጅ ለእጅ ተያይዘን  እንድ በመሆን በኖርዌ ኦስሎ ከተማ  ሴብቴምበር 28 በሚደረገው ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሐይሉ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ የየራሳችንን  ሐገራዊ ግዳጃችንን  እንድንወጣ ያስፈልጋል በማለት መልእክቴን አስተላልፋለሁ  ። የወያኔ አገዛዝ በቃህ በቃህ  ማለት ያስፈልጋል   ሞት ለወያኔ ድል ለኢትዮጵ ቸር ያሰማን።

ኢትዮጵያ ለዘልአለም ተከብራ ትኑር

እስክንድር አሰፋ
ኦስሎ ኖርዌ

ፍቼ በአንድነት ፓርቲ አባላት ላይ የደረሰው ድብደባ ከተጠቂዎቹ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ  ይመልከቱ




No comments:

Post a Comment