Tuesday, October 30, 2018

የብልሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) የመጀመርያ የአውሮፓ ጉዞ ለምን ወደ ፈረንሳይ ሆነ?

ጉዳያችን/Gudayachn
ጥቅምት 20/2011 ዓም (ኦክቶበር 30/2018 ዓም)


የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማርኮን(Emmanuel Macron)እና 
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር)


ኢትዮጵያዊውን ዕውቅ ዲፕሎማት የቀረፀች ፈረንሳይ! 


በ1904 ዓም በቡልጋ ከአለቃ ሀብተወልድ ካብትነህ እና ከወይዘሮ ያደግድጉ ፍልፈሉ የተወለዱት የኢትዮጵያጵያው ስመ ጥር ዲፕሎማት አክሊሉ ሀብተወልድ  አዲስ አበባ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አማርኛ ጠንቅቀው ከተማሩ በኃላ ዘመናዊ ትምህርት ለሶስት ዓመት ዳግማዊ ምንሊክ ትምህርት ቤት እንደተማሩ እና በመቀጠል ወደ ግብፅ እስክንድርያ ከተማ የሚገኘው የፈረንሳይ ሊሴ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ማጠናቀቃቸውን ታሪካቸው ያስረዳል።ከግብፅ  ለከፍተኛ ትምህርት ያመሩት ወደ ፈረንሳይ ታዋቂው ዩንቨርስቲ ሶቦርን (Sorbonne) ነበር ።በሶቦርን  ዩንቨርስቲ የንግድ ሕግ እና የፖለቲካ ሳይንስ ተምረው ሲጨርሱ ዘመኑ 1928 ዓም ጣልያን ኢትዮጵያን የወረረችበት ወቅት ነበር። 


የፈረንሳይ ትምህርት ውጤት ታላቁ ዲፕሎማት አክሊሉ ሀብተወልድ በፈረንሳይ ሀገር በድፕሎማትነት በመቀጠል በጀኔቭ የኢትዮጵያ ልዑካን መሪ የነበሩት የፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተከለ ማርያም ልዩ ረዳት በመሆን በጣልያን ወረራ ወቅት በያኔው የዓለም ማኅበር ፊት የነበረውን የዲፕሎማሲ ውግያ ከንጉሰ ነገስቱ ጋር በመሆን የተፋለሙ  አክሊሉ ሀብተ ወልድ የፈረንሳይ የዲፕሎማሲ ትምህርት ውጤት ናቸው።የአክሊሉ ሀብተወልድ በሃያኛው ክ/ዘመን ኢትዮጵያ በነበራት ዲፕሎማሲ አሻራ ከሱማሌ ድንበር እስከ ኤርትራ ውህደት፣ከጋምቤላ የድንበር ጉዳይ እስከ መካከለኛው ምስራቅ ውስብስብ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እስከ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ (የከተማ ይፍሩ ጥረት ሳይዘነጋ) የአክሊሉ ሀብተወልድ ምክር ያላረፈበት ቦታ የለም።


የብልሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የመጀመርያ የአውሮፓ ጉዞ ለምን ወደ ፈረንሳይ ሆነ? 


ፈረንሳይ በዲፕሎማሲ ትምህርት ማዕከል መሆን የጀመረችው በ18ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ነበር።ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ሲነሳ የፈረንሳይ አስተዋፅኦ መዘንጋት አይቻልም።ስለ ዓለም አቀፍ ሕግ ሲነሳ ከአውሮፓ ተሃድሶ ጋር የሚነሳው የፈረንሳይን አስተዋፅኦ ቸል ማለት ይከብዳል።ኢትዮጵያ ከጣልያን ወረራ በፊት የትምህርት ሥርዓቷን በፈረንሳይኛ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች እንደነበሩ እና ጣልያን ከኢትዮጵያ መባረር ተከትሎ ኢትዮጵያ የገቡት እንግሊዞች እና በመቀጠልም የአሜሪካ ልዕለ ኃያልነት መጉላት እንግሊዝኛ ቦታውን እንዳስለቀቀው ይነገራል። ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴም የፈረንሳይኛ ተናጋሪም ጭምር ነበሩ። የጣልያንን ወረራ ተከትሎ በጀኔቭ ለዓለም ማኅበር (አሁን የተባበሩት መንግሥታት የተሰኘው) ፊት ቀርበው አቤቱታቸውን ሲጀምሩ  '' ንግግሬን በፈረንሳይኛ ባደርገው በወደድኩ ነበር።ሆኖም ግን ሃሳቤን በሚገባ የማብራራው አማርኛ ስለሆነ በእዚሁ ንግግሬን አደርጋለሁ'' በማለት የጀመሩት ታሪካዊ ንግግርን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።


የዘመናችን ብልሁ መሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ (ዶ/ር) የመጀመርያ የአውሮፓ ጉዞ ያደረጉት ወደ ፈረንሳይ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታሪክ አዋቂ ናቸው።የፈረንሳይ ስረ መሠረትነት፣ታሪካዊ እና ባህላዊ ዳራ ሁሉ ሳይማርካቸው አልቀረም።ከቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ በኃላ ለፈረንሳይ የተሰጠው  ያልሞቀ እና ያልደመቀ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ፍትሓዊ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ልታገኝ የምትችላቸው በርካታ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የባሕላዊ ዕሴት አጠባበቅ ጥበቦች ሁሉ በሚገባ አለመቀሰማቸው ሳይቆጫቸው የቀረ አይመስልም። ጠቅላይ ሚኒስትር የፈረንሳይ ጉብኝታቸውን ዛሬ ጥቅምት 19፣2011 ዓም  ሲጀምሩ በሶስት መልኮች ኢትዮጵያ  ከፈረንሳይ የምታገኛቸው ጉዳዮች ላይ ማረጋገጫ ማግኘታቸውን ከፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ጎን ለጎን ሆነው በአማርኛ ለዓለም አቀፍ ሚድያ ፓሪስ ላይ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።  እነርሱም በቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት፣የኢትዮጵያ ጦር ማዘመን እና የቦሌ አየር መንገድን በመቶ ሚልዮን ኢሮ ወጪ ማዘመን የሚሉት ይጠቀሳሉ።


ዶ/ር አብይ ልዩ ሰው የሚይደርጋቸው አንዱ መገለጫ ዲፕሎማስን በግልብ ግንኙነት ላይ በተመሰረተ መልክ ሳይሆን የሚመሩት ታሪካዊ ግንኙነትን መሰረት አድርገው ነው።ቅድምያ የሚሰጡትን ከማይሰጡት የመለየት አቅማቸው እጅግ ድንቅ ነው።በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሲያቀርቡ እና ሲቆጡ እንዲሁም የኢትዮጵያን ግንኙነት በእኩል ልበ ሙሉነት እና ኩሩነት ሲመሩት ያስደምማሉ።ይህ ሁሉ ደግሞ ከድንቅ ፈጠራ ጋር ታክሎበት መሆኑ ሰውየውን ግሩም ዲፕሎማት ያደርጋቸዋል።ይህ አገላለጥ ለአንዳንዶች የተጋነነ መስሏቸው ከሆነ እስካሁን ካዩት የበለጠ ወድፊት ስለሚያዩት ያኔ ይረዱታል።ስልጣን እንደያዙ በሰአታት ውስጥ  ከክልል ከተሞች ወደ ጅጅጋ የሄዱበት እና ሁሉንም የጎረቤት ሀገሮች በመጎብኘት የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲ ያረጋጉበት መንገድ መመልከት፣ ለአመታት ፈገግታ የራቃቸውን የኤርትራ መሪ አቶ ኢሳያስ ሳቅ በሳቅ ያደረጉበት የዕርቅ ሂደት፣አሜሪካንን ያህል ሃያል ሀገር ሄደው ፕሬዝዳንቱን ሳያገኙ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻቸውን በአሜሪካ አደባባይ አዘምረው የዋሽንግተን ከንቲባን አስደምመው እና የኢትዮጵያን ቀን በእየዓመቱ ለማክበር ቃል እንዲገቡ አድርገው ሹልክ ብለው ዋይት ሃውስን ቁልቁል እያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ጳጳሳት ይዘው ወደ ሀገራቸው እብስ ያሉበት መንገድ ሁሉ ድንቅ ዲፕሎማሲ፣ድንቅ የአፈፃፀም ችሎታ ነው። ማድነቅ እና ማሞገስ ካለብን ዓብይ በሕይወት እያለ አለማድነቅ እና አለማመስገን አለመታደል ነው።ይህ ብቻ አይደለም የተባበሩት አረብ ኤምሬት ልዑል በክረምቱ ወራት ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ከቦሌ አየር ማረፍያ የቦሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሲያስጎበኙ እራሳቸው መኪናቸውን እያሽከረከሩ ያስጎበኙበት ምላሽ ልዑሉ ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሀገራቸው በተመሳሳይ መንገድ እየነዱ ከወሰዷቸው በኃላ የኢትዮጵያን የሰላም ሀገርነት የገለጡበት ድንቅ እኩል ምላሽ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ።


ዶ/ር አብይ ወደ ፈረንሳይ የመጀመርያ ጉዞ ሲያደርጉ ታሪካዊ ዳራውን እና መጪውን የፈረንሳይ አካሄድ በሚገባ አላዩትም ማለት አይቻልም። ፈረንሳይ በኢትዮጵያ ያለፈ የአርባ ዓመታት የፖለቲካ ሹክቻ ውስጥ እጇ አልተነከረም።በ1830 ዓም ከአጤ ምንሊክ አባት ከንጉስ ኃይለመለኮት ጋር ግንኙነት የጀመረችው ፈረንሳይ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በይፋ የጀመረችው በ1897 ዓም በአፄ ምንሊክ ዘመነ መንግስት ነው።የፓርስን ከተማ ከደብረ ብርሃን ከተማ ጋር  ታሪካዊ ቁርኝት የፈጠረችው ፈረንሳይ፣ ለኢትዮጵያ ከሰባት መቶ ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው የመጀመርያ የባቡር  መስመር ዝርጋታ ከአዲስ አበባ እስከ ጅቡቲ የተዘረጋው ከአንድመቶ ዓመት በፊት ነበር።በአሁኑ ወቅት ከሰላሳ በላይ የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በሥራ ላይ መሆናቸው ሲታወቅ በአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ተጨማሪ ባለ ሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ይጠበቃል።



ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ እና አንጌላ ሜርክል 

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቻይና ግሎባል ኔትዎርክ አፍሪካ የተሰኘው ቴሌቭዥን ማምሻውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉብኝት አስመልክቶ ሲዘግብ ፈረንሳይ ከእዚህ በፊት በመካከለኛው እና ምዕራብ አፍሪካ ላይ አተኩሮ የነበረው ዲፕሎማሲ አሁን ወደ ምስራቅ አፍሪካ መዞር የመጀመር አዝማምያ መታየቱን ገልጧል።የዜና ዘገባው እንደገለጠው ፈረንሳይ ከሩዋንዳ ጋር የነበራት ግንኙነት በመቀዛቀዙ አሁን ትኩረቷን ለኢትዮጵያ እና ኬንያ ማድረግ መጀመሯን ምልክቶች መታየታቸውን ያብራራል።በእዚሁም መሰረት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማርኮን (Emmanuel Macron) በሳምንታት ውስጥ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ እንደሚመጡ ዘግቧል።በዛሬው የጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እደሳ፣ከአንድ መቶ ሚልዮን ዩሮ በላይ የቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ለማዘመን፣የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ለማዘመን ስልጠና እና ትጥቅ እና የዓለም ባንክ ከሚሰጠው በተጨማሪ በሁለትዮሽ ግንኙነት ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደሚኖር ተሰምቷል።እነኝህ ስጦታዎች ዝርዝር ጉዳይ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ በቅርቡ በሚኖራቸው የኢትዮጵያ ጉብኝት ወቅት እልባት እንደሚያገኙ ይጠበቃል።


ከሃያ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የሚታደሙበት የጀርመኑ ስብሰባ 


ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከፈርንሳይ በመቀጠል የሚጎበኙት የአውሮፓ ሀገር ጀርመን ነች።ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላት ሀገር ስትሆን ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ በቴክኒክ ትምህርት በቀዳሚነት እገዛ ከሚያደርጉ ሀገሮች ጀርመን ተቀዳሚ ነች።በቅርቡም በኢትዮጵያ የቮልስቯገን መኪና መገጣጠምያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመክፈት ጀርመን ፍላጎት እንዳላት የኩባንያው ኃላፊዎች በቅርቡ በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት አስታውቀዋል።


የጀርመኗ መራሂ መንግስት አንጌላ መርክል በኢትዮጵያ አሁን እየተካሄደ ላለው ለውጥ ከፍተኛ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት አላት።ጀርመን ከኢንዱስትሪ ልማት በተጨማሪ በንግድ ክህሎት (ኢንተርፕረነርሽፕ) ስልጠና እንዲሁም በቤቶች ግንባታ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ደረጃ ላይ ትገኛለች።እነኝህን ክህሎቶች ደግሞ በ''ጂ ቲ ዜድ'' እና የግል ድርጅቶቿ ወደ ኢትዮጵያ የማስተላለፍ ስራዎች በመጠኑ ጀምራለች።ከእዚህ በተጨማሪ በጀርመን የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን ሙያ ለሀገራቸው እንዲያፈሱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት አይነተኛ በር ይከፍታል።ከእዚህ ጋር ተያይዞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የጀርመንን የቴክኒክ አቅም በጣና ሀይቅ ላይ ለተከሰተው የእንቦጭ አረም መላ ለመዘየድ የጀርመን ኩባንያዎችን ሊያነጋግሩ እንደሚችሉ ይገመታል። 


በመጨረሻም የጠቅላይ ሚንስትር የጀርመን ጉብኝት ትልቁ ቦታ የሚይዘው ከሃያ ሺህ በላይ ኢትዮያውያንን የሚያገኙበት የፍራንክፈርት ስብሰባ ነው።በእዚህ ስብሰባ ከመላው አውሮፓ የሚሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ሲታወቅ በስብሰባው ላይ  በርካታ ሃገራዊ ጉዳዮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚነሱ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩም ማብራርያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።ወደጀርመን ተጉዘው ከጠቅላይ ሚኒስትር  ጋር መገናኘት ለሚፈልጉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚያደርጉት የጋራ ስብሰባ ቀን፣ሰዓት እና የስብሰባው ስፍራ  ከእዚህ በታች ይመልከቱ።



የስብሰባ ቀን Date: 31st October 2018
የስብሰባ መጀመርያ ሰዓት Time: 13:00 (1:00pm)
የስብሰባው ቦታ እና አድራሻ  Venue: Commerzbank Arena, Morfelder Landstrasse 362, 60528 Frankfurt am Main, Germany
Skilde   ጉዳያችን/Gudayachn

Tuesday, June 12, 2018

በኦሮሚያ በጭናክሰን ዐስራ አራት ሰዎች በሶማሌ ልዩ ፖሊስ መገደላቸውን አምነስቲ አስታወቀ






ፎቶ፡ አምነስቲ ኢተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት ካወጣው ሪፖርት ላይ የተወሰደ ነው።
ከኦሮሚያና ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች ምላሽ እንዲሰጣቸው አስፈላጊው ጥበቃም እንዲደረግላቸው አሳስቧል።

በምስራቅ ሐረርጌ በጭናክሰን ወረዳ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል አባላት በከፈቱባቸው ጥቃት የብዙ ሰው ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም አምነስቲ ኢንተናሽናል ዛሬ ባወጣው መግለጫም ከአርብ ጀመሮ እስከዛሬ ድረስ በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ዐሥራ አራት ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል።
ድርጅቱ አርብ ዕለት ባወጣው መግለጫ ደግሞ ከኦሮሚያና ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች ምላሽ እንዲሰጣቸው አስፈላጊው ጥበቃም እንዲደረግላቸው አሳስቧል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ዘርን ያማከሉ ጥቃቶችና በተያያዥነት የሚፈጠሩ መፈናቅሎችን ለማስቆም እንዲሁም ዜጎችን ከጥቃት ለመከላከል መሥራት አለበት ብሏል።