Wednesday, August 21, 2013

ወ/ት ሐዲያ ሙሀመድ ከሳምንታት የእስር ቤት ስቃይ በሁዋላ ተፈታች

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራር የሆነቸው ወ/ት አዲያ አህመድ ከሀምሌ 22 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ  ስቃይ እስር ቤት ውስጥ ከደረሰባት በሁዋላ በዛሬው እለት በዋስ ተፈታለች።
ወ/ት ሐዲያ እንዳለችው መርማሪ ፖሊሶቹ በቁጥጥር ስር ያዋሉዋት አንድነት ፓርቲ ሀምሌ 28 በሶዶ ከተማ ሊያደርገው የነበረውን ህዝባዊ ስብሰባ በተመለከተ የቅስቀሳ ወረቀቶችን መበተኑዋን ተከትሎ ነው።
ፖሊሶቹ በሀድያ ጉዳይ አንድነትን ከድምጻችን ይሰማ የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር በማያያዝ ለመወንጀል ቢፈልጉም፣ ሀድያ ባሳየችው ያቋም ጽናት ሳይሳካለቸው ቀርቷል።
መርማሪ ፖሊሶች ” ገልብጠን እንገርፍሻለን፣ አንገትንሽን ጠምዝዘን ገደል እንወረውረዋለን፣ ቀደም ሲል የታሰሩ እስረኞች እንዳወቁበት እወቂ” የሚሉና ሌሎችንም የማስፈራሪያ ቃላት በመጠቀም እነሱ አዘጋጅተው ባመጡት ወረቀት ላይ እንድትፈርም ለማድረግ ቢሞክሩም፣ ሀድያ ለማስፈራሪያው ልትንበረከክ አለመቻሉን ተናግራለች ( )
በታሰረችበት እስር ቤት መጸዳጃ ቤቱ ሞልቶ በምኝታቸው ላይ ይፈስ እንደነበር የምትለው ሐድያ፣ የወላይታ እስር ቤት የምድር ሲኦል ነው በማለት በእስር ቤቱ ውስጥ ያየችውን በዝርዝር ለኢሳት ተናግራለች። ከወ/ት ሀድያ ሙሀመድ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለምልልስ ሰሞኑን እናቀርባለን ።
በዚህ አጋጣሚ ወ/ት ሀድያ ወደ ፍርድ ቤት ስትሄድ በመቆያነት ታስራበት የነበረውን ጊዜያዊ እስር ቤት ከፊል ገጽታ በፎቶ በማንሳት ላካፈለን የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ተወካይ አቶ ዳንኤል ሽበሺ ከፍተኛ ምስጋናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

No comments:

Post a Comment