Thursday, May 2, 2013

በእነ አንዱዓለም አራጌ እና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለለፈው ፍርድ በ/ጠ/ፍ/ ቤት ፀና


ሰበር ዜና
ሚያዝያ 24 ቀን 2ዐዐ5 

በእነ አንዱዓለም አራጌ እና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለለፈው ፍርድ በ/ጠ/ፍ/ ቤት ፀና፡፡ እነ አንዱዓለም አራጌ ያቀረቡትን ይግባኝ መርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ጠ/ፍ ቤት ዛሬ ሚያዝያ 24 ቀን 2ዐዐ5 ዓም በሰጠው ብይን፣ ይግባኝ ባዮች በሽብርተኛነት ተግባር ላለመሳተፋቸው አሳማኝ የሆነ መከላከያ አላቀረቡም ብሏል፡፡ በዚህ የተነሳ የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አፅንቷል፡፡

“እውነት ተደብቆ አይቀርም” እስክንድር ነጋ (ከፍርዱ በኋላ በችሎት ውስጥ) 
“የተከራከርነው ፍትህ እናገኛለን ብለን አይደለም፤ ፍትህ ወዳድ በመሆናችን ነው” ናትናኤል“ 
የእኛን ጉዳይ ለመከታተል እዚህ ስለተገኛችሁ እናንተ የእኛ ጀግኖች ናችሁ” አበበ ቀስቶ 
“የእስክንድር ወንጀል አገር መውደድ ብቻ ነው” (ሰርካለም ፋሲል- ከፍ/ቤት ውሳኔ በኋላ) 
“ግንቦት ሰባት የእስክንድርን እጅ የመጠምዘዝ ኃይል የለውም” (ሰርካለም ፋሲል በችሎት ውስጥ የተናገረችው)

No comments:

Post a Comment