Friday, May 24, 2013

ዋናው ጤና ነው

ረሃብን ለማስወገድ በሚደረገው ዓለምአቀፍ ጥረት ውስጥ የጥንዚዛ፣ የአባጨጓሬ፣ የንብ፣ የተርብና የጉንዳን ዘሮችን ለምግብነት መጠቀም እጅግ ጠቃሚ ሚና ሊጫወት እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የግብርና ድርጅት - ኤፍኤኦ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በዓለም ዙሪያ አሁን እነዚህን ነፍሣት የዕለት ምግባቸው አድርገው የሚኖሩ ከሁለት ቢሊየን በላይ ሰዎች መኖራቸውን አመልክቶ በገንቢና አልሚ ምግቦች የከበሩ፣ በቅባት፣ በበረትና ሌሎችም ማዕድናትና ንጥረነገሮች የበለፀጉ ናቸው ብሏል፡፡

ነገ-ነፍሣትነገ-ነፍሣት
የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥም ጠቃሚ ናቸውና በመላው ዓለም መለመድ ያለባቸው የምግብ ዓይነቶች መሆን አለባቸው ሲል ኤፍኤኦ ሃሣብ አቅርቧል፡፡

በሌላ ዜና ደግሞ በአስም ለሚንገላታ በዓለም ዙሪያ ከሦስት መቶ ሚሊየን በላይ ለሚሆን ሰው መጠነኛም ቢሆን እፎይታን ሊያስገኝ ይችላል የሚል ጥናት በዝንጅብል ላይ እየተካሄደ ነው፡፡

በዚህ ድንቅ የሥራ ሥር ውጤት ውስጥ - አሉ የረዥም ጊዜ ክትትል ሲያደርጉ የቆዩት የኒው ዮርኩ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች - የመተንፈሻ አካላትን ጡንቻዎች የሚያዝናና ኃይል ያለው ንጥረ ነገር አለ፡፡ ያንን ንጥረ ነገርም ነጥለው አውጥተው በመድኃኒቶቹ ውስጥ ሊያስገቡ የሚችሉባቸውን መንገዶች እያሰቡ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ሌላ ዘገባ እንደሚናገረው ደግሞ ተዋናይት እና የተባበሩት መንግሥታት የበጎ ፍቃድ አምባሣደር አንጀሊና ጆሊ ‘…አንድ ቀን …ወደፊት .. ልጋለጥ እችል ይሆናል’ በሚል ሁለቱንም ጡቶቿን ማስወገዷ የሰሞኑ የመገናኛ ብዙኃን አጀንዳ እና የካንሠር መከላከያ ቀዶ-ሕክምናም መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
http://amharic.voanews.com/content/health-05-21-13/1664923.html

No comments:

Post a Comment