Sunday, May 26, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ ሁለት አባላቱ ለምን ጥቁር ልብስ ለበሳቹ ተብለው ታሰሩ


ሰማያዊ ፓርቲ ከግንቦት 15 እስከ 17 /2005 ዓ.ም ጥቁር ልብስ የመልበስና ግንቦት 17/2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት ፊለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ ጥቁር ልብስ ለምን ለበሳችሁ በማለት የፓርቲው የኦዲትና ኢንስፒክሽን አባል የሆነው ወጣት ሀብታሙ ደመቀና በነጋታው እርሱን ለመጠየቅ የሄደው ወጣት ራቅሊስ ካሣ መታሰራቸውን ፓርቲው ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

በአሁኑ ወቅትም የፓርቲው አመራር እና አባላት በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመገኘት ታሳሪዎች እንዲፈቱ የጠየቁ ሲሆን በቀጣይ የታሰሩ አባሎቻችን አስመልክቶ ሰማያዊ ፓርቲ የሚሰጠው መግለጫ ይኖራል፡፡

No comments:

Post a Comment