Monday, April 29, 2013

በስታቫንገር ኖርዌይ ነዋሪ የሆነው ወጣት አብዮ ጌታቸው ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና ስለ ቦንድ ግዢ የሚለን ነገር አለ

እስክንድር  አሰፋ
ከኦስሎ  ኖርዌይ 
april 29.2013

watch video
 ወጣት አብዮ ጌታቸው በኖርዌይ እስታቫንገር ነዋሪ ሲሆን ለብዙ አመታት በዚሁ ከተማ የኢትዮጵያን ወራሪ መንግስትን በመቃወም ዲሞንስትሬሽን  በማድረግና እንዲሁም ማንኛውንም እናት ሐገሩ የምትፈልገውን ነገር በአቅሙ እያገለገለ  የሚኖር እውነተኛ ዜጋ ነው።

 የወያኔ መንግስት በሐገራችን ህዝብ ላይ በአባይ ግድብ ስም ከእለት ጉርሱ ላይ እየነጠቀ ለግል ጥቅሙ እንደሚያውል አመታት አስቆጥሯዋል  እንዲሁም   በሐገር ቤት አልበቃ ብሎት ወደ ዲያስፖራው ፊቱን በማዞር አለምን በማካለል  ይገኛል  ለምሳሌ በምድረ አሜሪካን ፤በአውሮፓ፤ ሳውዝ አፍሪካ እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ የሚገኙትን ኢትዮጵያኖች አምታትቼ ኮሮጆዬን እሞላለሁ በሚል የህልም ቅዥት በሄደበት አህጉራት ሁሉ የቅሌትን ሸማ  ተከናንቦ  እየተዋረደ ይገኛል  ። 

አሁንም በምድረ ኖርዌይ ይህንኑ ቅሌቱን በአለም ላይ እራሱን  ለማዋረድ ቀና ደፋ ሲል ቆይቶ በApril 20 .2013 stavanger  ሊያደርግ ያሰበውን የቦንድ ሽያጭ ማሰባሰቢያ  በጀግኖች ልጁቻችን መደናቀፉና መዋረዱ የቅርብ ቀን ትዝታ ነው ።

 እናም በዛ ወቅት በእስታቫንገር ከሚኖሩ የናት ሀገራቸን የቁርጥ ልጆች ከሆኑት አንዱ የሆነው ወንድማችን አብዮ ጌታቸው ሲሆን  ለወያኔ ካዝና ማደለቢያ ሊጋዝ የነበረውን ገንዘብ አዘጋጆቹ እንደቋመጡ  እንዲቀር  ካደረጉት አንዱ ወገናችን ሲሆን  እንዲሁም በዛ ወቅት ከተለያየ አካባቢ ለሄድነው ወገኖቹ የሚሆን መስተንግዶና ማረፊያ በቀላሉ እድናገኝ ያደረገና እንዲሁም  በብዙ ነገር ሃላፊነትን ተረክቦ ቀና ደፋ ሲል የነበረ  ታጋይ  ነው ።

 በዛው ቀን በተገነናኘንበት ጊዜ ትንሽ ስለ ዝግጅቱ ሁኔታና ስለሐገራችን ወቅታዊ  ጉዳይ  ተወያይተን ነበር በእለቱም  በምስል ስለቀረጽኩት እንድትመለከቱት ስል በትህትና  እጠይቃችኋለው።

ድል ለኢትዮጵያ ሞት ለዘረኙችና ለከፋፋዮች
ቸር ያሰማን 



No comments:

Post a Comment