Thursday, November 22, 2012

የሙስሊም ተከሳሾች የፍርድ ቤት ዉሎ

  የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ና ወንጀል ችሎት ፣ ልደታ ምድብ፣ በአነ አቡበከር አህመድ መዝግብ ፣ ዐቃቤ ህግ የከሰሣቸውን 31 ተካሳሾች ጉዳይ ዐይቶ ትእዛዝ ሲሰጥ፤ የአነ አቶ አንዱዓለም አራጌን የይግባኝ ሂደት የሚመለከተው ጠ/ፍርድ ቤት 1ኛ የወንጀል ችሎት፤ ደግሞ የይግባኝ አካሄዱን መርምሮ ለመወሰን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር በተገኘበት የ4ኛ ወንጀል ችሎት የልደታ ምድብ ችሎቱን ለመከታተል፣ በርካታ የአሥልምና ሃይመኖት ተከታዮችና ቤተሰቦቻቸው በፍርድ ቤቱ ግቢና ከግቢም ውጭ ተኮልኩለው ውለዋል። ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የተከታተለው የነአቶ አንዱዓለም ጉዳይ የታየበት ችሎት በበኩሉ ጉዳዩን ለታኅሳስ 10 ቀን 2005  ዓ ም፣ መቅጠሩን የላከልን ዘገባ ያስረዳል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ተክሌ የኋላ 

AUDIOS  ON THE TOPIC 

ይገልብጡ

No comments:

Post a Comment