Thursday, November 15, 2012

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባል የሆነችዉ አስፈላጊ መስፈርቶችን በማሟላትዋ ነዉ ተባለ

የኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሆና መመረጥዋ ሲቀርቡብን የነበሩ ክሶችንና ዉንጀላዎችን ዉድቅ ያደረገ ነዉ ሲል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል።

የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ቃል አባይ አቶ ዲና ሙፍቲ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃል ኢትዮጵያ አባል ሆና የተመረጠችዉ አስፈላጊ መስፈርቶትን በማሟላትዋ ብለዋል። ከአንድ መቶ ዘጠና ስምንት አገሮች አንድ መቶ ሰባ ስምንቱ ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ምክር ቤቱ አባል እንድትሆን መደገፋቸዉ ዓለም አቀፍ ድጋፍ  እንዳላት ያመለክታል ሲሉ አክለዋል።

በሌላ በኩል የተቃዋሚዉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ምክትል ሊቀመንበርና ቃል አቀባይ  ዶክተር በየነ ጴጥሮስ በስብአዊ መብቶች ጥሰት የምትታወቅ አገር ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክር ቤት አባል ሆና መመረጥዋ እኛን ብቻ ሳይሆን ለመብት የሚቆረቆሩ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን ጭምር  የሚያሳዝን ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያን መንግስት የምክር ቤት አባልነቱን ለፖሮፓጋንዳ ለመጠቀም ከሆነም ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ጉዳት በመሆኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በእርምጃዉ ትልቅ ስህተት ማድረጉን መረዳት ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ዘገባ ያድምጡ  http://amharic.voanews.com/content/article/1546345.html

No comments:

Post a Comment