Friday, November 16, 2012

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ውስጥ - የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽኗ እና የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ

በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት መመረጥ ላይ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነሯ እና የሰመጉ ዳይሬክተር ለቪኦኤ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አምባሣደር ጥሩነህ ዜና - የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር /የፎቶ ምንጭ - ፋይል/


ሰሎሞን አባተ



ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ውስጥ ...

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
 
የኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባልነት መመረጥ ካስመዘገበቻቸው የምጣኔ ኃብት እና ማኅበራዊ ስኬቶች በአካባቢውና በምክር ቤቱ ምሥረታ ላይም ከተጫወተቻቸው ሚናዎቿ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አምባሣደር ጥሩነህ ዜና አስታውቀዋል፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ   
 
በሌላ በኩል ደግሞ ምርጫው በወቅቱ ያስደነገጠው መሆኑንና ምናልባትም ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዟን እንድታሻሽል ግፊት ማሣደሪያ አጋጣሚ ሊሆንም እንደሚችል የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ሞላ አመልክተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment