Friday, July 13, 2012

አዲስ አበባ በወታደሮች ተጨናንቃለች; መስጊዶች የአደጋ ጊዜ አዛን (ጥሪ) እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ በወታደሮች ተጨናንቃለች; መስጊዶች የአደጋ ጊዜ አዛን (ጥሪ) እያደረጉ ነው

Posted by on July 14, 2012 1 Comment
አውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) – በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር አሁን እኩለ ሌሊት አልፏል፡፡ ኮልፌ በሚገኘው እፎይታ መስጊድ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ነው፡፡ ይህንኑ ተከትሎ የአዲስ አበባ መስጊዶች በአደጋ ጊዜ የሚደረገው ‹‹የአዛን ጥሪ›› በማድረግ ህዝበ ሙስሊሙ ወደ መስጊድ እንዲሰባሰብ ጥሪ እያደረጉ ነው፡፡
ሙስሊሞቹም ለጥሪው አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ‹‹ተክቢራ›› የሚባለውን ድምጽ እያሰሙ ወደ መስጊዶች እየጎረፉ ነው፡፡ ሆኖም የፌደራል ፖሊስ መንገድ በመዝጋት ህዝበ ሙስሊሙን ለመበተን እየሞከረ ነው፡፡ አውራምባ ታይምስ በስልክ ያነጋገራቸው አንድ የሀይማኖቱ አባት ‹‹የቁርዓንን ቅዱስ ጥሪ በፖሊስ አይቆምም፤ ወደ ቤትም አንገባም ብለዋል›› እኒሁ አባት እንዳሉት ከተማዋ በርካታ ቁጥር ባላቸው ታጣቂዎች ተጨናንቃለች፡፡
ቀጣይ ተጨማሪ ዘገባዎችን ይዘን እንቀርባለን

No comments:

Post a Comment