Saturday, July 7, 2012

በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ያደመ ቁት ‹‹የኢትዮጵያ ቀን›› በዳላስ

በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ያደመ ቁት ‹‹የኢትዮጵያ ቀን›› በዳላስ

Posted by on July 7, 2012 0 Comment
አውራምባ ታይምስ (ዳላስ) – የኢትዮጵያዊያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ለ29ኛ ጊዜ በዳላስ ቴክሳስ እየተከበረ ይገኛል፡፡ ትናንት አርብ ደግሞ የዚሁ ፕሮግራም አንድ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ቀን በድምቀት ተከብሯል፡፡
አውራምባ ታይምስ ያነጋገራቸው የፌስቲቫሉ ተሳታፊዎች ‹‹ኢትዮጵያዊያን ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ለአገራቸው አንድነት በጋራ የቆሙበት ልዩ ክስተት ነበር›› ሲሉ ገልጸውታል፡፡
አንጋፋዎቹ ድምጻዊያን ማህሙድ አህመድ እና ጸሐዬ ዮሐንስ የተገኙበት ይህ ደማቅ ዝግጅት በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በስቴዲዮሙ ውስጥና ከስቴዲዮሙ ውጪ ሆነው አክብረውታል፡፡

No comments:

Post a Comment