Friday, July 13, 2012

‹‹እነ ዶ/ር ብርሃኑ ወደ ሀገርቤት መጥተው ፍርዳቸውን እንዲቀበሉ እናደርጋለን›› ፍትህ ሚኒስቴር

‹‹እነ ዶ/ር ብርሃኑ ወደ ሀገርቤት መጥተው ፍርዳቸውን እንዲቀበሉ እናደርጋለን›› ፍትህ ሚኒስቴር

Posted by on July 13, 2012 2 Comments
አውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) – የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 6 ቀን 2004 ዓም በሰጠው ብይን አቶ አንዱዓም አራጌ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ እና አቶ ፋሲል የኔዓለም ላይ የዕድሜ ልክ ፅኑ ዕስራት ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) 25 ዓመት፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በ18 ዓመት፣ አቶ ናትናኤል መኮንን በ18 ዓመት፣ አቶ ዘለለ ፀጋ ሚካኤል በ18 ዓመት፣ አቶ ውቤ ሮቤ በ18 ዓመት፣ አቶ ኦባንግ ሞቶ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ የወሰኑ ሲሆን፣ ሻምበል የሸዋስ ይህንዓለም 15 ዓመት፣ አቶ መስፍን አማን በ15 ዓመት፣ አቶ አበበ በለው 15 ዓመት እና አቶ አበበ ገላው በ15 ዓመት እስራት ይቀጡ ብሏል፡፡
እንዲሁም አቶ ምትኩ ዳምጤ በ14 ዓመት፣ አቶ አንዱናለም አያሌው በ14 ዓመት፣ አቶ ዮሐንስ ተረፈ ላይ የ13 ዐመት ፅኑ እስራት ያሳለፈ ሲሆን፣ የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ የነበሩት ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ እና አብይ ተ/ማሪያም የ8 ዓመት እስራት እንደተላለፈባቸው አሳውቋል፡፡ ፍ/ቤቱ ሁሉም ተከሳሾች የእስር ጊዜአቸውንን ካጠናቀቁ በኋላ ለ5 ዓመት ሁሉንም ሕዝባዊ መብቶቻቸውን እንዲነፈጉም ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በአቶ አንዱዓለም አራጌ መዝገብ በጥቅምት ወር 2004 ዓም ክስ የተመሰረተው በ24 ሰዎች ላይ ሲሆን፣ አራቱ ሰዎች ቀደም ሲል በነፃ መሰናበታቸው ይታወሳል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ፍትህ ሚኒስትር በተከሳሾች ላይ የተሰጠውን ፍርድ በተመለከተ
ከስዓት በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በፍትህ ሚኒስትር የክርክር ጉዳዮች ሚ/ር ዴኤታ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ በሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ሥም፣ እንዲሁም በጋዜጠኝነት ሽፋን ተደራጅተው ሕገመንግሰታዊውን ሥርዓት ለመናድ በሞከሩት ተከሳሾች ላይ የተሰጠው ፍርድ ትክክለኛና ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
ከተከሰሱት ሰዎች መሃል በግንባር ቀርበው ፍርዳቸውን የተቀበሉት ስምንት ሰዎች ብቻ ናቸው፤ በሌሎቹ ላይ የተሰጠው ፍርድ ተፈፃሚ የሚሆነው እንዴት ነው የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ሚ/ር ዴኤታ ብርሃኑ ፀጋዬ “ፍርድ የተላለፈባቸውና በሀገር ውስጥ የሌሉ ሰዎች ከያሉበት ሀገር መጥተው ፍርዳቸውን እንዲቀበሉ ለማድረግ መንግስት የሚጠበቅበትን ሁሉ ያደርጋል፡፡” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment