Thursday, January 31, 2013

ቤተ ክህነት የአዲሱን ፓትርያርክ ምርጫ የሚቃወሙትን እንደምትከስ አስፈራራች



(ደጀ ሰላም፤ ጥር 20/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 28/2013/ PDF)፦ ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥሰላማዊ የሽግግር ጊዜውን ለማደናቀፍ የሚገኙ ቡድኖችን፣ የመገናኛ ብዙኅንና ግለሰቦችን የመንበረፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ማስጠንቀቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል የስድስተኛውን ፓትርያርክአሿሿም በሚመለከት ሕገ ደንብ ወጥቶ ምርጫውን ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ውስጥ መሆኑንየሚያውቁ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኅን፣ ከውስጥ አፍራሽ ኃይሎች የሚቀበሉትን ፀረ ሰላምና ከእውነትየራቀ አሉባልታ ከድረ ገጽ ያገኙ በማስመሰልና ምንጮቻችን እያሉ በውጭና በአገር ውስጥ ያለውንምዕመናን እያወናበዱ በሚገኙት ላይ ቤተ ክህነት ክስ መመሥረቷን የዘገበው ጋዜጣው መግለጫውንየሰጡት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሳይሆኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስመሆናቸውን አብራርቷል።


የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የተጠቀሙባቸው ቃላት በርግጥ ጉዳዩ የቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ሌላ አስመስሎታል። “ፀረ ሰላም፣ ማደናቀፍ፣ አፍራሽ ኃይሎች” የሚሉትን ቃላት በቤተ ክህነት ሳይሆን በቤተ መንግሥት አደባባይ ሲነገር ስለምናውቃቸው አሁንም ማስጠንቀቂያው የማን ነው የሚለውን እንድንጠይቅ ያደርገናል። ማስፈራራት ግን መልስ አይደለም። ግዴላችሁም ልብ መግዛት ይሻላል። ለማንኛውም የዚህን ዜና ዝርዝር ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል።       

ቸር ወሬ ያሰማን አሜን

No comments:

Post a Comment