Monday, January 14, 2013

በሃገራችን ውስጥ እውነት እና እምነት ክጠፋ 21 አመታት ማስቆጠሩን ያውቁ ኑርዋል ?

እስክንድር  አሰፋ   ከኖርዌይ
14.01.2013


በሃገራችን ውስጥ እውነት እና እምነት ክጠፋ 21 አመታት አስቆጥሮአል ምክንያቱም የኢትዮጵያ  መንግስት ተብዩው አንዴ በቤተ ክሪስቲያኑ እንዲሁም በእስልምና ጉዳይ ላይ እጁን በማስገባት አንዳንድ  አባት ተብዩዎች ማህተባቸውን አውልቀው ሲጥሉና ሌሉችም  ጥለውት ከተሰደዱበት  ሃገር ላይ እንዴት ተብሎ ነው እውነት እና እምነት አለ ተብሎ የሚነገረው ። እንዲህም ሲባል ሁሉንም አያጠቃልልም ለምሳሌ ሙስሊም ወንድሞቻችን ዲናችንን አናስደፍርም ለእምነታችን እንሞታለን  በማለታቸው  ከላይ ታች ሲዋከቡ እና ሲደበደቡ ከዛም የከፋ ነገር ሲደርስባቸው እያየን ነው አንዳንዶችም እምነታችንን ለሆዳችን አሳልፈን አንሰጥም በማለት  ይሄው አንድ አመት አለፋቸው።  ስጋቸው በእስር ቢሰቃይም መንፈሳቸው ግን ከአምላካቸው ጋር በደስታ ይፈንድቃል፣፥ እንዲሁም የዋልድባ አባቶቻችንም ተጠቃሽ  ሲሆኑ   እነ እስክንድር ነጋ  ፥ አንዷለም  አራጌ ፥ርዮት አለሙ ፣  በቀለ ገርባ  እንዲሁም ሌሎችም  በመልካም ስራቸው አለም እያደነቃቸውና እያከበራቸው በማን አለብኝ ባዩ እና  አሸባሪው መንግስት ግን ተወንጅለው በእድሜልክ በቃሊቲ እስር ቤት እንዲማቅቁ  ተደርገዋል ፥፥ እኔ  እንደማስበው ከሆነ አንዳድ የቤተ ክሪስቲያን አባቶች  ተብዬዎች ቅስናውን እንደ ስራ አይተውት እንጂ አምላካቸውን አምነውበት  የዘላለምን ህይወት እናገኝበታለን ህዝቡንም እናገለግላለን  ብለው የገቡበት አይመስለኝም ምክንያቱም በቤተ ክሪስቲያኗ መናወጥ ምንም አይነት የመቆርቆር ስሜት እንኳን  አይታይባቸውም ይባስ ብለው ከእምነት  በፊት የስኳር ምርት ይቅደም የሚሉ ናቸው  ካዲያ እነዚህ ምናቸው ነው መንፈሳዊ አባቶች የምንላቸው  አምላክ ይቅር ይበላቸው ። ይሄን ሁሉ ያስወራኝ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ። ወንድማችን ተመስገን ደሳለኝ ስለ አስታራቂ ሽማግሌዎቹ አምታችና አወናባጅ  ስራቸው ያስነበበውን መጣጥፍ አንብቤ ነው ፣፣በእለተ ሃሙስ ጥር 2 ቀን 2005 ዓ.ም በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ ይመሩ ከነበሩት ሽማግሌዎች ውስጥ የተዘጋጀ ሦስት ሰዎች ያሉት አንድ ቡድን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝቶ ነበር።  ጉዳዩም እንዲህ ነው  በተጠቀሰው ቀን አንዱአለምን ጠርተው አናግረውታል ፣ እስክንድር ነጋን ዘለውታል። ለምን ?   ሌላው አስገራሚ ጉዳት ደግሞ የሽማግሌ ቡድኑ ለሙስሊም መሪዎች ,, የመጣነው አንዱአለምን ፈልገን ነው ፣እናንተን እግረመንገዳችንን ሰላም እንበላቹ ብለን ነው,, ሲሏቸው  ለአንዱአለም ደግሞ የዚህን ግልባጭ ምክንያት ሰተውታል ። ካዲያ ወገን ይህንን አይነት ማምታታትና መቀላመድ ምን ለመፍጠር ነው  ? ለነገሩስ የታወቁ ናቸው በምርጫ 97 ጊዜ ቅንጅቶችን ማወናበዳቸው ይታወቃል ። ከዛስ  ደግሞ አንዱን ታራሚ ለይቶ መጠየቅ አንዱን መዝለል ይህንንስ ምን  ይሉታል ?    አስገራሚ ነገር ነው  ባይታደሉት ነው እንጂ እራሳቸው ከአምላካቸው ጋር እርቅ አድርገው የበደሉትን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀው ለዘላለም የሚድኑበትን ስራ እየሰሩና  ቀሪ ጊዜአቸውን  ንስሃ  እየገቡ መኖር  ይሻላቸዋል  ብዩ አምናለው  ለማንኛውም  እግዚአብሄር በቸርነቱ ሃገራችንን ያስባት  ቸር ያሰማን ። 

የታሰሩትን ወንድሞቻችንን እግዚአብሄር በቸርነቱ ይጎብኛቸው 

ኢትዮጵያን ለዘላለም ተከብራ ትኑር


http://www.zehabesha.com/archives/15924






No comments:

Post a Comment