Wednesday, March 20, 2013

አማርኛ በቻይና ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሊሰጥ ነው


አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2005 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) በቤጂንግ  የውጭ  ትምህርቶች ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ  ቋንቋን ማስተማር የሚያስችለውን ስምምነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር ስምምነት ገብቷል ። ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ስምምነቱን ባለፈው ሳምንት
ተፈራርመዋል። በስምምነታቸው መሰረትም አማርኛ  ቋንቋ ከሚቀጥለው መስከረም ወር  ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው  መሰጠት ይጀመራል ።የአዲስ  አበባ  ዩኒቨርሲቲም የቻይና  ቋንቋ  ስልጠና  ፕሮግራሙን  ወደ መጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ይሆናል ።
የትምህርት መርሃ ግብሩን ለመጀመርም ዛሬ  አዲስ አበባ  ላይ  የስምምነት ፊርማ ይፈፀማል ።

No comments:

Post a Comment