አንጋፋው
የኢሳት ጋዚጠኛ ፋሲል የኔአለም በትናትናው
እለት march
09,2013 በኖርዌይ
ኦስሎ የስራ ጉብኝት ባደረገበት ጊዜ በኖርዌይ
የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የኢሳትን ደጋፊነታቸውንና
አጋርነታቸውን ለመግለጽ በኢትዩጵያ ኮሚኒቲ
ተሰባስበው የእራት ግብዣ አድርገውለታል።
በዝግጅቱ ላይ በኖርዌይ የሚኖሩ በርከት ያሉ ኢትዮጵያዊያኖች ከተለያዮ ስፍራ በመገኘት ስለ ኢሳት አመሰራረትና በሃገራችን ውስጥ ስላለው የስብአዊ መብት ጥሰት ከሐገር ቤት ከሚደርሳቸው ዘገባ በመነሳት ስላለው ሁኔታና እንዲሁም የተለያዮ እርእሶችን በማንሳት በስፋት ሲወያዮ አምሽተዋል ።
በመጀመሪያም
በኖርዌይ የኢትይዮጵያ ኮሚኒቲ ተወካይ የሆኑት
አቶ ቢትወደድ ጸጋዬ የእንኳን ደህና መጣህ
ንግግርና በፌብርዋሪ10.2013
በተሳካ
ሁኔታ ለተጠናቀቀው የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ
በማውሳት ኢሳት ለኢትዮጵያኖች አይንና ጆሮ
እንደሆነና መደገፍ የሚገባው ድርጅት እንደሆነ
የሚገልጽ የድጋፍ ንግግር አድርገው የኖርዌይ
ኢትዮጵያኖች ለኢሳት ያላቸውን ድጋፍና በአንድ
እግሩ ለማቆም ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችም ሆነ
ግለሰቦች ጋር ተባብሮ ለመስራት ያላቸውን
አጋርነት በመግለጽ በህዝቡ ስም ዝግጅቱን
ከፍተዋል።
ጋዜጠኛ
ፋሲልም ከተለያዮ ታዳሚዎች የቀረቡለትን
ጥያቄዎችንም በተገቢው ሁኔታ በስፋት በማብራራት
ለታዳሚዎቹ ሲገልጽ አምሽቷል በተለይ ሃገር
ቤት ሆነው ስልክ የሚደውልሏቸውን ወጣቶች
ያላቸውን የፖለቲካ ብቃትና በእድሜአቸውም
ማነስ እያነጻጽረ ምን ያህል ወጣቱ በፖለቲካ
ብቃት መጎልበቱን በማድነቅ ለታዳሚዎቹ
ሲያጫውታቸው አምሽቷል።
በመጨረሻም ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ታዳሚዎችን በእርሱና በኢሳት የስራ ባልደረቦቹ ስም አመስግኖ ወደ ተዘጋጀለት ማረፌያ በክብር ተሸኝቷል። ከዛም በጠዋት ወደ ሚኖርበት ሆላንድ አምስተርዳም ከተማ አቅንቷል።
ጋዚጠኛ ፋሲል የኔአለም በኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ እንደ ተላለፈበት ይታወሳል ።
http://www.rnw.nl/africa/article/exiled-ethiopian-journalist-convicted-terrorism
ማርች
10.2013
No comments:
Post a Comment