Saturday, February 8, 2014

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ቴክኒክና ሞያ ማሰልጠኛ ማእከል በጋዜጠኝነትና በኮምፒዩተር ትምህርት ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ተማሪዎች በሰርትፍኬት አስመረቀ፣






ይሀው በትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል ከህዳር 1 እስከ ጥር 24/2006 ዓ/ም ለተከታታይ ሰዎስት ወራት የተካሄደ ስልጠና። ሰልጣኞቹ በጋዜጠኝነትና በኮምፒዩተር ሞያ ብቁ የሆነ እውቀትና ችሎታ ቀስመው እንዲወጡ አላማ ያደረገና። በጨበጡት አቅምም ድርጅቱ በሚያካሂደው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል እንደሆነ ማእከሉ ገልፀዋል፣
     በምረቃው ወቅት የተገኘው የድርጅቱ ሊቀመንበር ታጋይ ሞላ አስገዶም ለተመራቂዎች ሽልማት ከሰጠ በኃላ ባሰማው ንግግር። ይህ ሲሰጥ የቆየው የስልጠና ትምህርት የመጀመርያ እንዳልሆነና በየግዜው ሲካሄድ እንደነበረ ከገለፀ በኋላ። ሞያውን ለማስጨበት ጥረት ላደረጉ አሰልጣኖችና ተማሪዎችም። እንኳን ፍሬያችሁን ለማየት አበቃቹህ ሲል ገልጸዋል፣ 
     ተጋይ ሞላ አስገዶም በማስከተል ወደ ህዝቡ ትክክለኛና ጥራት ያለው መረጃ ለማቅረብ፤ የስርዓቱን ፀረ ህዝብ ተግባሮች ለማጋለጥና አጠቃላይ የድርጅታችን ፖለቲካዊ ስራዎች በብቃት ለማስፈፀም ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው በማስታወስ ቀጣይ ለሚያደርጉት የስራ እንቅስቃሴም የተሳካ እንዲሆንላቸው ተመኝቶላቸዋል፣  
     ጥር 25 2006 ዓ/ም በተካሄደው የምረቃ ስነ-ስርዓት  የተገኘውና  ስልጠናውን ከሰጡ አስተማሪዎች እንዱ የሆነው ታጋይ ኣስመላሽ ሃይሉም። ተማሪዎቹ በስልጠናው ወቅት ላሳዩት ተሳትፎ በማድነቅ። ለሰልጣኞቹ እንኳን ለዚሁ የምረቃ ቀን ኣደረሳችሁ ብለዋል፣


    በመጨረሻ! የተማሪዎቹ ተወካይ በምረቃው ግዜ ተሳታፊዎች ለነበሩ እንግዶችና ተማሪዎች እንኳን ለዚሁ የምረቃ በአል አደረሰን በማለት። ሰልጣኞቹ ትምህርቱን ለመጨበጥ ያሳዩት ጥንካሬ ድርጅቱ በሰጣቸው ስራ ላይም ደግመው ማሳየት እንደሚችሉ ቃል ገብተዋል፣
    የተከበራቹህ ተመልካቾቻችን የምረቃው ስነ-ስርዓት ሙሉውን ይዘትና ልዩ ፕሮግራም በቅርብ ቀን እናቀርበዋለን፣  

No comments:

Post a Comment