Monday, February 24, 2014

(ዜና ድንቅ) የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት የጸረ ግብረሰዶም ህጉን ፈረሙበት!

የኡጋንዳ ፓርላማ ፣ አንዳንድ ግብረሰዶማዉያንን እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ እስራት ለመቅጣት ያሳለፈውን ህግ፣ ፕሬዚዳንት እንዳይፈርሙበት፣ ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ከአንዳንድ የሰብ አዊ መብቶ ድርጅቶች ግፊት ቢደረግባቸውም፣ ዛሬ ፈርመውበታል።
አስቀድሞ ፓርላማው ግብረሰዶማዊ የሆነው ሰው ከህጻናት ጋር ሲፈጽም ከተገኘ ወይም ኤች አይ ቪ እንዳለበት እያወቀ ድርጊቱን ከፈጸመ በሞት ይቀጣ ሲል ህግ ቢያወጣም፣ ፕሬዚዳንቱ ፣ የሞት ቅጣቱ ካልቀረ አልፈርምም ሲሉ ቆይተዋል። በኋላ ቅጣቱ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት ተቀየረ። በዚህ መካከል የኡጋንዳ ሳይንቲስቶች “ግብረሰዶማዊነት የተፈጥሮ ጉዳይ ነው፣ ወይም በፍላጎት የሚፈጸም?” የሚለውን አጥንተው እንዲነግሯቸው ፕሬዚዳንቱ አዘዙ። ሳይንቲስቶቹም “ምንም እንኳን ግብረሰዶም መፈጸም በሽታ ነው ማለት ባይቻልም፣ በተፈጥሮ የሚመጣ ሳይሆን ሰዎች ፈልገውና ተለማመደው የሚያደርጉት ነው” ሲሉ ነገሯቸው።
አሁን በቃ ልፈርም ነው ሲሉ በመናገራቸው ወዲያው ፕሬዚዳንት ኦባማ “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ” አይነት መልክት ላኩባቸው፣ እሳቸውም “እሺ የአሜሪካ ሳይንቲስቶች፣ ነገሩ የተፈጥሮ ነው (ሰዎች ግብረሰዶማዊ ሆነው ነው የሚወለዱት) የሚለውን ነገር መጥተው ለኔና ለሳይንቲስቶቼ ያስረዱን” ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። ይህን ካሉ ቀናቶች አለፉ። እንግዲህ መጥቶ ያስረዳቸው የለም ማለት ነው። ዛሬ ህጉን ፈርመዋል። በኡጋንዳ ግብረሰዶማዊነት እስከ 10 ዓመት በ እስር ሲያስቀጣ፣ ነገሩ የተፈጸመው ከህጻን ጋር ከሆነ እስሩ እስከ ዕድሜ ልክ ይሆናል። በነገራችን ላይ በዚህ ህግ መሰረት ግብረሰዶም ፈጻሚዎች አይቶ ለፖሊስ ያልጠቆመም እንዲሁ እስር ይጠብቀዋል። (ዜናውን ዴይሊ ቢስትና አልጀዚራ ዛሬ አወሩት – ድንቅ መጽሔት ተረጎመው)

No comments:

Post a Comment