Wednesday, February 26, 2014

ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላ (ምን አለሽ መቲ) እና ጋዜጠኛ ደረጀ ሐ/ተወልድ ኦስሎ ገቡ

ቅዳሜ March 01, 2014  ኢሳት የኔ ነው ምሽት በኦስሎ ዝግጅት ላይ በእንግድነት የተጋበዙት ጋዜጠኛ መታሰቢ ቀጸላ(ምን አለሽ መቲ) ከለደን እና ደረጀ ሐ/ተወልድ ከአመስተርዳም ዛሬ እሮብ Feb 26,2014 Oslo ገብተዋል።ባሳለፍነው ቅዳሜ Feb 22,2014 በተመሳሳይ ፕሮግራም ሲዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በተዘጋጀው ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ በመገኘት ዝግጅታቸውን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁት  ወገኖቻችን የመጨረሻ ጉዞአቸውን ወደ ኖርዌይ በማቅናት ዛሬ ከሰአት በኋላ በኖርዌ ሰአት አቆጣጠር 15;30 በሰላም ገብተዋል። የኖርዌ ኢሳት ኮሚቴ ተወካዩችም ተወዳጆቹን ጋዜጠኞች በሰአቱ አይሮፕላን ማረፊያ ድረስ በመሄድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።


  እስክንድር አሰፋ /ኖርዌ

No comments:

Post a Comment