Tuesday, February 26, 2013

ኢትዮጵያዊቷ ወ/ሮ ትግስት ሱዳን ስደተኛ ካምፕ ነዋሪ የሆኑት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ታፍነው ተሸጠው ዛሬ ሲና የሚገኙት የድረሱልን ጥሪ!


የህብር ራዲዮ  እሁድ የካቲት 17 ቀን 2005 ፕሮግራም

<<ኢትዮጵያዊቷ ወ/ሮ ትግስት ሱዳን ስደተኛ ካምፕ ነዋሪ የሆኑት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ነው ታፍነው ተሸጠው ዛሬ ሲና የሚገኙት።አጋቾቻቸው የጠየቁትን ገንዘብ ካልተሰጠ ገድለው ኩላሊታቸውን ፤ልባቸውንና ሌላ የፈለጉትን አካላቸው ይሸጡታል።
ሰሞኑን የአንዲት ሌላ ኢትዮጵያዊ ሞት መርዶ መጥቷል። የወይዘሮዋን ነፍስ አድነን ከህጻናት ልጆቻቸው ጋር እናቀላቅላቸው።ሕይወት እናትርፍ ጊዜ የለንም>>
ወ/ሮ ሰብለ ደምሴ የሚኒሶታ ነዋሪ ሲና በርሃ በአጋቾች እጅ የሚገኙትን ኢትዮጵያዊ አስመልክተው የሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ 
(ሙሉውን ያዳምጡት)

<< ባለቤቴ አሁንም በሲና በርሓ አጋቾች እያሰቃዩዋት ነው እባካችሁ ከነ ሰብለ ጋር ተባበሩ....እኔ እዚህ ሱዳን ስደተኛ ካንፕ ጥላ የሄደቻቸውን ልጆች ይዤ ተቀምጫለሁ እዚያ ይደበድቧቸዋል፤ዘቅዝቀው ያሳድሯቸዋል...>>አቶ መልካሙ ባዮ ከሱዳን ስደተኙች ካንፕ ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ ።

እስክንድር አሰፋ 
ከኖርዌይ
26,02,2013

No comments:

Post a Comment