Sunday, February 3, 2013

ኢቲቪ ለረጅም ወራት የተዘጋጀበትን ሀሰተኛ ዶኩመንተሪ ፊልም የፊታችን ማክሰኞ ሊያቀርበው ነው፡፡ ጂሃዳዊ ሃረካት በሚል የሙስሊም ኮሚቴዎች ላይ መርዙን ሊረጭ ነው፡፡ ሙስሊሙን ከክርስቲያኑ ጋር ለማጋጨት የታለመ ዶክመንተሪ ፊልም ነው፡፡

 እስክንድር አሰፋ  ከኖርዌይ
  04 02 2013 አ.አ
ETV ስራውን ትቶ ወደ መንግስት አቃጣሪነት ና የፊልም አዘጋጅና አቀናባሪ ሆኖ  መቀየሩ በጥም ያሳዝናል በጣም የሚገርመው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ ስለሚደረገው ነገር ሁሉ ጠንቅቆና  ቀድሞ የሚያውቅ  ነው ።  እንደኔ ከሆነ  ፊልሙን ወደ አሜሪካን ሀገር ሆሊውድ Hollywood ልከውት ሃሪፍ የACTION FILM በመሆን የአመቱ ምርጥ FILM  በመባል አዋርድ AWARD እነደሚያገኙበትና እንደሚሸለሙበት በእርግጠኝነት ነው ምክርሬን የምለግሳቸው ወይም ቻይና ልከውት በካራቴ ፊልም ያስቀይሩትና እኛም እንይላቸው ።  

ያለበለዚያ በሃገር ውስጥ የታየ FILM ደጋግሞ አንዴ አኬል ዳማ አንዴ ጅሃዳዊ ሐረካት በማለት ለህዝብ ማሳየት የድርጅቱንና የአቅራቢውን ገበያ መዝጋትና ተመልካች ማሳጣት ነው  ።


እኔ የሚገርመኝ ነገር ይሁሉ ድካምና የሃገሪቷን ንብረት ማውደም በማይረባ የወረደ ተንኮል ጥንሰሳ  ቀና ደፋ ማለት እና  ዜጉችን በልሆነ  በሆነ  የETV DOCUMENTERY FILM በተቀነባበረ የውሸት ውንጀላ ሰላማዊ ህዝብን  መቀመቅ ውስጥ  ለመክተትና ለማስፈራራት  የሚሰራ ሴራ ነው? የምለው  ወይም  ለ3000 አመታት ተከብራና ተሞግሳ የኖረችውን ሃገራችንን  በሌሎች ሀገር  የምናየውን የእርስ በርስ ጦርነት በአገራችንም ላይ ለመቀስቀስ የሚደረግ ደባ ነው ? 

ካዴያ ማን ነው ሃገርን በሆነ ባልሆነ በተሳሳተና የውሸት ውንጀላ ህዝብን   እያሸበረና እያስፈራራ  ያለው ? ሊወነጀል የሚገባው መንግስት ነኝ ባዮ አሸባሪው ነው  ወይስ  ህገ መንግስቱ ይከበር የእመነት ነጻነታችን ይከበር በሃይማኖት ውስጥ መንግስት ጣልቃ አይግባ እያለ በዲሞክራሲ መብቱ በመጠቀም በአደባባይ ላይ ድምጹን እያሰማ  ያለው ኢትዮጵያዊ ነው? 

እኔ የማሳስበው ነገር ቢኖር  አሁን በአለንበት ዘመን አለም በቴክኖሎጂ እድገት ጣሪያ በደረሰበት ሰአት  INFORMATION ከዳር እስከ  ዳር በአንድ ቦታ ሆነን ማግኘትም  መከታተልም  ሆነ መነጋገር  የምንችልበት ጊዜ  ነው እድሜ ለቴክኖሎጂ  ስለዚህ በሃገራችን ውስጥ ስለሚካሄደውም ሆነ ስለሚፈጠረው  ነገር እያንዳንዱን ነገር በደቂቃ ውስጥ  ምን እንደ ሆነ  ቤታችን ሆነን ማየት  የምንችልበት ዘመን ስልሆነ እውነታውን በደንብ አብጠርጥረን ስለምናውቅ   ስለሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል የምትል ወገን ሁሉ ሃገርህን  ከወደቀችበት የአፓርታይድ አገዛዝ ውስጥ መንጥቀህ ማውጣት ያለብህ አንተ ብቻ  ነህ  ። 

ያለበለዚያ ማንም ካንተ በላይ ሊደርስላት አይችልም አንተም  በጥቅማ ጥቅም  በመታለል አፓርታማ በመገንባትና የራስህን ህልውና በጥቅም ቀይረህ  ከእኩልነት በፊት የኔ ጥቅም የበልጣል በለህ ከአሸባሪው መንግስት ጋር ወግነህ  ያፈራረስካትን ሃገር  አጥተህ  ያፈራከውንም ንብረት ሳትበላው መቀበሪያክ ነው የምትሆነው እሱንም እድለኝ ከሆንክ ነው ። 

ምክንያቱም  በዚህ በተያዘው ከፋፍለህ ግዛው እና በአሸባሪነት ተግባር በመክሰስ እንዲሁም ድንበርን ለጎረቤት ሃገር መስጠት  እንዲህ ባለ አወዛጋቢ ሁኔታ ሃገራች ኢትዮጵያ አስራ አራት ቦት ከፋፍለዋት  አህጉር ከማደረጋቸው በፊት አባቶቻችን አንድነቷን  ጠብቀው ድንበርዋን አስከብረው የሰጡንን ሃገራችንን ኢትዮጵያ  በአንድነት ሆነን እጅ ለእጅ ተያይዘን ብንነሳ  የተሻለ ይመስለኛል    እማማ ኢትዮጵያ መከበሪያ፤መኩሪያ፤መደሰቻ፤ዞሮ መግቢዬ ናት እንጂ አሁን እንደምናየው መዋረጂያ መረገጭያና መሳደጃ አትሆንም የትውልድ ብልሹ እንዳንሆን  መጠንቀቅ ያስፈልገናል ።

 ሃገራችን ኢትዮጵያ የቢሄር ብሄረሰቦች  እኩልነት የሚከበርባት ሃገር ፡ ሃገራችን ኢትዮጵያ የሃይማኖት ነጻንት የሚከበርባት ሀገር  እንጂ በአንድ ብሄር የበላይነት በጦር በመሳሪያ የምትገዛበት ሀገር አይደለችም አትሆንምም ። ቸር ያሰማን  

ድል ለ ኢትዮጵያ ህዝብ 
ኢትዮጵያ ለዘልአለም በነጻነቷ ተከብራ  ትኑር  
   ትኖራለችም 

 እስክንድር አሰፋ  ከኖርዌይ 









No comments:

Post a Comment