Sunday, December 2, 2012

የአዜብ-በረከት የተንኮል እቅድ


መለስ ዜናዊ የስልጣን እድሚያቸውን ለማራዘም ከተጠቀሙባቸው ዘዴዎች አንዱና ዋናው “የትግራይ ህዝብ የሥርዓቱ ልዩ
ተጠቃሚ”እንደሆነ አድረገውበካድሬዎቻችው በኩል ያለመሰልቸት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ማካሄድ ነበር። ይህ ዘዴ የትግራይ ህዝብ
ተጠቃሚ፤ የኢትዮጲያ ህዝብ ግን የበይ ተመልካች ሆኖ እንዲሰማውአድርጎታል። አቶ መለስ “ነፃሚድያ”ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚቻልሁኔታ ስላጠፉትና የኢትዮጵያ ህዝብም የሳቸውየፕሮፓጋንዳ ሰለባ ስላደረጉት እሳቸውየሚናገሩት እና የሚያወሩት እውነት ይሁን ውሸትለማወቅ ይቸገራል። ያ ውሸት ተደጋግሞ ሲነገረውውሸቱን እውነት ነው ብሎ ይቀበለዋል። አቶ መለስ ኢኮኖሚህ 11 በመቶ አድጓል እያሉነጋ ጠባ ሲወተውቱት፣ ከአመት ወደ አመት ኑሮው እየከፋ፣ ጉልበቱ በረሀብ እየደከመ የሄደው ወገን ውሸቱን እውነት አድርጎ ከመቀበልውጪሌላ አማራጭየለCም።

መለስ የትግራይ ህዝብ አጋዥ አጣ እንጂ በምን አይን እንደሚያያቸውጠንቅቀውያውቃሉ። መለስ እና ኢትዮጵያ እሳትና ጭድ
መሆናቸው ጎልቶ የወጣው በተለይ የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት አክሽፈው፣ የኢትዮጵያ መሬቶችን ለኤርትራ አሳልፈውለመስጠት ባለ
አምስት ነጥብ የሰላም እቅድ የሚል የማጭበርበርያ እቅድ ነድፈው እሱን ለመተግበር ደፋ ቀና ሲሉ በነበረበት ወቅት ማለት ነው!
ቀጥሎም ከመተማ እስከ ጋምቤላ ያለውን እጅግ ለም መሬት ያላንዳች ሀፍረት ለሱዳን እጅ መንሻ ሲያደርጉ፣ ሰውየው ኢትዮጵያን
በሁሉ መንገድ ለማዳከም ቆርጠው የተነሱ እንደሆኑ ታወቀ። ባለፈው አመትም ቢሆን የሻቢያ ሰራዊት በተደጋጋሚ የኢትዮጵያን ድንበርጥሶ፣ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አስሮ፣ ያገሬውን የቀንድ ከብቶች፣ በጎችና ፍየሎች እንደልቡ ዘርፎ ሲወስድ፣ መለስ “ሻቢያ ግልጽ ጦርነትእስካልከፈተብን ድረስ፣ በትንንሽ ትንኮሳዎች ተታለን ዋናውጠላታችን የሆነውን “ድህነትን” ከመዋጋት ወደኋላ አንልም” ሲሉ በኢትዮጵያህዝብና ሀገራዊ ሉዓላዊነት ሲያሾፉ ተስተውለዋል።

መለስ ከክልሎች ሁሉ የሚፈሩት እና ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግለት የሚሹ ቢኖር የትግራይን ክልል ነው። የትግራይ ህዝብ አመፅ ማለትበሰራዊቱ ውስጥ ያለው ወታደርም አመፀ ማለት ነው። ያ ደግሞ የመለስ የስልጣን እድሜ ያሳጥረዋል። ያ አደገኛ ሁኔታ እንዳይከሰትነበር አቶ መለስ ቴዎድሮስ ሐጎስን የክልሉ የበላይ ጠባቂ ያደረጉት። ኤርትራዊውቴዎድሮስ ሐጎስ ከፊሎቹ ወንድሞቹ የሻብያ ተዋጊዎችስለነበሩ፣ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ስትከፈት እና መቀሌ የሚገኘውየአይደር የህፃናት ት/ቤትን በቦምብ ሲደብደብ፣ ቁጣውንበሰልፍ የገለፀውየመቀሌ ነዋሪ ህዝብ ከጠየቃቸውጥያቄዎች አንዱ “ቴዎድሮስ ሐጎስን” እንዲባረርለት ነበር። አቶ መለስ ደግሞ እራሱአስጊ ሁኔታ ውስጥ ቢኖርም፣ ፈራ-ተባ ከማለት ውጪ፣ ከኤርትራ ጋር የወገነውን ጠ/ሚኒስቴር ደፍሮ ከስልጣን ሊያባርር የሚችልየህወሓት ኃይል ስላልነበር፣ ቴዎድሮስ ሐጎስን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አውጥቶ ወደ ኃያሉና ታማኙ የፖሊት ቢሮ አባል አድርጎሾመው። ያቺን የመቀሌ ህዝብ ክስ ለመበቀል ነበር ቴዎድሮስ ሐጎስም በምርጫ97 ጊዜ“ትግሬ ወደ መቀሌ፣ ዕቃ ወደ ቀበሌ” የምትልመርዝ በቅንጅት ስም አዲስ አባባ ሆኖ የረጫት። የኢትዮጵያ ህዝብሙሉ ድጋፍ የነበረውቅንጅት ለዘር ግጭት ትንኮሳ የተበተነችውንመርዝ ተጠያቂው ቅንጅት እንዳልሆነ በሚድያ ወጥቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለመግለጽ ተደጋጋሚጥያቄ ቢያቀርብምሚዲያውንየተቆጣጠረውበረከት ስምኦን ግን የቅንጅትን ጥያቄ ሊያስተናግድ ቀርቶ አመራሩን እንዳለ በጅምላ ዘብጥያ እንዳወረዳቸውየትናንቱትውስታ ነው።

ዛሬ መለስ የሉም። ያሉት የአቶ መለስ ባለሟሎች ናቸው። በረከት ስምኦን፣ ሳሞራ ዮኑስ፣ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ እና ሌሎች የኤርትራ ዝርያያላቸውሰዎች ዋናውን የስልጣን ቁልፍ ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር በመሆን አቶ ሀ/ማርያም ደሳለኝን አንደ ጋሪ ፈረስ ከፊት አስቀድመውእየተጓዙ ይገኛሉ። ፍርሃት እናጭንቀት የሞላበት ጉዞ እንደሆነ ግልጽ ነው። “ያለን አማራጭመለስ ሲጠቀምበት የነበረውን ስልትመጠቀም አለብን” እንደሚሉ ልዩ ትምህርትን አይጠይቅም። አንደኛና ዋነኛውደግሞ የትግራይ ህዝብ ከቀሪውወገኑ ጋር እንዳያብርአሁንም ተነጥሎ የሚመታበት መንገድ መዘየድ የግድ ይላል። ይህን ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ የተመደበችው ደግሞ አዜብ ሆናለች።

         “መለስ ትግራይን በኢንዱስትሪ ለማልማት የ5 አመት እቅድ ነድፎ ነበር” - አዜብ መስፍን

አዜብ ኢህአዴግ ወይም ራስዋ በምትቆጣጠረውቴሌቭዥን ሰሙኑን ታይታ ነበር። ጋዜጠኛዋን ያነጋገረቻች ኤፈርት ቢሮውስጥ ቢሆንም፣
አዜብ ግን አሁንም ሀዘን ላይ የተቀመጠች እንደሆነች ተመልካች እንዲያውቅላት የምትሻ ትመስላለች። ድምጽዋ በልቅሶ የጎረነነ
ታስመስለዋለች። “መለስ ትግራይን በኢንዱስትሪ ለማበልጸግ የአምስት አመት እቅድ ጽፎ ነበር!” አለች አዜብ በጎረነነ ድምጽ።
አሃ!ጨዋታ እዚህ ላይ ተጀመረ።

መለስ እሱ ራሱ አልፎ አልፎ ሲናገር እንደተደመጠው ወደ ክልል ወርዶ ጣልቃ ልግባ እንኳ ቢል ጊዜ እና አቅሙእንደሌለው፣ እሱ
የተወጠረው፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ጉዳዮች፣ በአፍሪቃ ቀንድ ፖለቲካ (ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ ወዘተ) ከዛም አልፎበአፍሪቃናበጥቂቶችና በበለፀጉ የዓለም መሪዎች ስብሰባ (G-8 እና G-20) ላይ እየተገኘ በንቃት መሳተፍን እንደሆነ ደጋግሞ ይገልጽ ነበር።

ታድያ ዛሬ ወ/ሮ አዜብ ከነበረከት ስምኦን ጋር ሆነውየጠነሰስዋትን ተንኮል ይዘውወደሚድያ በመቅረብ መለስ ትግራይን የኢንዲስትሪማእከል ለማደረግ መጽሀፍ ጽፏል ብለው አረፉት። መለስ ለትግራይ ልዩ የእንዲስትሪ ራእይ ቢኖራቸው ምነው 21 አመት ሙሉ ስልጣንላይ በነበሩበት ጊዜ አልተገለፀላቸውም? ይቺ ራእይ የአዜብ እና የበረከት “ትግራይን የማጥመድ ራእይ” እንጂ፣ እንደተባለው የልማትራእይ ሊሆን ፈጽሞ አይችልም። ደፋርዋ አዜብ አክላም “የኔ ኃላፊነት የመለስን ራእይ እውን ማድረግ ነው”ካለች በኋላ የEFFORT(ትእምት) ኩባንያዎች ዘንድሮ ከ16.5 ቢልዮን ብር በላይ የሚገመት ምርትና አገልግሎት ለገበያ ለማቅረብ እቅድ ተይዟል አለች።ለሲሚ ጀሮ እንዲጥም ግን አዜብ ከሁሉ አስቀድማ “የህዝብ ንብረት” ስትል የገለጸችውን ኤፈርት ባለፈው አመት ብቻ 376 ሚልዮን ብርበግብር ለመንግስት ገቢ አድርጓል አለች። ዋናውጥያቄ ደግሞ “የህዝብ ንብረት” ከሚሉ ቃላቶች ጋር ይሆናል። እውነት ኤፈረት የህዝብነውን? ከሆነ ታድያ ለምን በድብቅ በአንድ ቤተሰብ ቁጥጥር ስር ዋለ? የህዝብ ከሆነ ህዝቡ የማኔጅመንት ቦርድ አቋቁሞ በየጊዜውለምንየኤፈርት ገቢና ወጪአንዲያውቅ አልተደረገም?ከወ/ሮ አዜብ በፊት ኤፈርትን በሥራ-አስኪያጅነት ይዞ የነበረውየመለስ ታማኝ ካድሬ አባዲ ዘሞ (የአሁኑ በሱዳን የወያኔ አምባሳደር)መሆኑ ይታወሳል። ከአባዲ ዘሞ በፊት ኤፈረትን በመዳፉ አስገብቶ ይቆጣጠረው የነበረውሽማግሌውስብሃት ነጋ ነበር። ታድያ በሱ ጊዜበውጭየሚገኙ የህወሓት ደጋፊዎች መሃል ኤፈረት የህዝብ ነውከተባለ ለምን ኦዲት አይደረገም የሚልጭቅጭቅ ተነስቶ ኦዲት መደረግ
አለበት የሚሉ አሽንፈውየውጭአዲተር ቀጥረውወደ መቀሌ ይልካሉ። ወደ ኤፈረት ዋና ጽ/ቤት ያመራውየሂሳብ አካውንት መርማሪደግሞ ሽማግሌውን አግኝቶ ለምን እንደመጣ ሲነገረው፣ ስብሃት ነጋ ኃይለ-ቃል በተሞላበት አንደበት “በል ሌላ ችግር ሳይከተልህወደመጣህበት ቶሎ ተመለስ!” ብሎ አሰናበተው።

ወ/ሮ አዜብ ደግሞ ከኤፈርት የሚዘርፉት ገንዘብ አልበቃ ብሏቸውየትግራይን ህዝብ ከተቀረውወገኑ ጋር ለማጋጨት ድርጅቱን የፖለቲካመሳሪያ አድረገው ለመጠቀም እየተንቀሳቀሱ ያሉት። እዚህ ላይ አንዳንድ ተንኮሉ ያልገባቸውወገኖቻችን የአዜብን ቃል እንዳለ በመውሰድይኸው“እነኚህ ዘረኞች ትግራይን ለማልማት እንጂ” ቀሪውየኢትዮጵያ አካል ምናቸውም እንዳልሆን ነውየሚያሳየውእያሉ በጽሁፍሳይቀር ብሶታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ይኽም ማለት የነ በረከት/አዜብ አደገኛና ከፋፋይ ስትራተጂውጤትማ ሁኗል ማለት ነው።ምክንያቱም እነሱም ያቀዱት ፕላን ቢኖር፣ ተቃዋሚ ከሚባሉት ክፍሎች በኩል የሚሰነዘረውን አስተያየት ቀንጭቦ በመውሰድ፣ መልሰውለትግራይ ህዝብ “ይኸውእኛ ትግራይን በኢንዲስትሪ እናበለፅጋለን ስንል፣ ትምክህተኞችና ነፍጠኞች ግን ያንተን እድገት እየተቃወሙትይገኛሉ። እነዚህ ኃይሎችን ነውመፍራት ያለብህ። መድረክም ይሆን ሌሎች ተቃውሚዎች ጠላቶችህ መሆናቸውን ላንድ አፍታም ቢሆንመዘንጋት የለብህም!” እያሉ ህዝቡን ይበልጥ በወገኑ ላይ እንዲጠራጠር፣ ለውጥ ፈላጊ እንኳ ቢሆንም “ከማላውቀውመልአክ የማውቀውሰይጣን ይሻለኛል” ወደሚል ድምዳሜ እንዲደርስ ይገደዳል።

 ስለዚህ ወ/ሮ አዜብ ተናገረች ተብሎ እስዋን አምኖ፣ ነገሮችን በሰከነ አእምሮሳያጤኑ ወደ ድምዳሜ እና ወደ ማውገዝ መጓዝ የተቃዋሚውን ጎራ ትግል እንደሚጎድውና ይባስ ብሎ የገዢውን አካል እንደሚያጠናክር
ከወዲሁ መታወቅ ይኖርበታል።

ኢትዮጵያ በልጆችዋ የተባበረ ሃይል ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!

ጋሻ ለኢትዮጵያውያን
ህዳር 14 2005
ሲያትል ዋሽንግተን

No comments:

Post a Comment