Tuesday, July 23, 2013

አገር እንደ ዳቦ


አገር እንደ ዳቦ

አገር እንደ ዳቦ እየተቆረሰ፣
ከሰላ ተበልቶ ጅቡቲ ደረሰ፣
ጅቡቲ ተበልቶ ኤርትራደረሰ፣
ኤርትራ ተበሌቶ ወልቃይት ደረሰ፣
በወልቃይት በኩል ጉምዝን ተሻግሮ ጋምቤላ ደረሰ፣
ለጎራሽ(ለጠላት) እንደያመች እየተገመሰ።
አገር እንደ ዳቦ እየተቆረሰ፣
ዳር ዳሩ ተበልቶ መሃል ተደረሰ።
ይህ ተላላኪ እንግዳ አስተናጋጅ እየተጣደፈ፣
ኢትዮጵያን ለማጥፋት
እየሸነሸነ አገር ለማስበላት፣
በክልል፣በጎሳ ቆራሽ አሰለፈ።

የውጭ ወራሪ ሌላ መንገድ ቢያጣ፣
አገሩን ለመያዝ(ለመግዛት) መለስ ብሎ መጣ።
ከሰሃራ በታች ከሱዳን ባሻገር፣
ከኬንያ ወዲህ በኢትዮጵያ ድንበር፣
መሬትና ቦታ መግዛት ካማራችሁ፣
እርካሽ ነጋዴ ኢህአድግ(ወያኔ) አለላችሁ።
ጣሊያንና እንግሊዝ ከአምሳ ዓመት በዃላ ከኢትዮጵያ በወጡ፣
ኢህአዳግን ፈጥረው እንደገና መጡ፣
በዲሞክራሲ ስም ከፋፍለው ሊግጡ።

በርካሽ ሸምተው በውድ ሊሸጡ፣
ያገር ውስጥ ነጋዴ መድረሻ ሊያሳጡ።
በስመ ፈላሻ፣በስመ ሎተሪ ሕዝብን እያሶጡ፣
መለስ ቀለስ ብለው ለመበተን መጡ።
ጥንትም ሰሜኑ ነው መግቢያና መውጫቸው፣
ወደ መሃል አገር መረማመጃቸው።

ኢራን፣ ሕንድ፣ ቻይና፣ ቱርክና እሩስያ፣
አውሮፓ አሜሪካ፣ሳውዲና ሉቢያ፣
በቅርጫው ገብተዋል በነጻው ገበያ፣
ወግድ ባይ በሌላት በኢትዮጵያ።
ያገሬ ደሃ ሕዝብ አትቀበላቸው፣
ከልማት ባሻገር ሌላ ግብ አላቸው።

ለውስጡ ተነፍጋ ለውጭ የቀረበች፣
እየተገመሰች፣እዬተቆረሰች፣
ኢትዮጵያ አገራችን ክብ ዳቦ ሆነች፣
በዚህ ከቀጠለ ሙልሙል ትሆናለች።
ያለም ነጋዳዎች ካለፈው ተማሩ፣
ሕዝብ ስልጣን ሲይዝ በባዶ እንዳትቀሩ፣
ከወያኔ ጋራ አትፈራረሙ አትደራደሩ፣
የሱ ብቻ አይደለም የዘጠና አምስት ሚሊዮን ሕዝብ ነው አገሩ።

No comments:

Post a Comment