Monday, July 1, 2013

ተረጋግቻለሁ ያለው ኢሕኣዴግ መታመስ ጀምሯል::



ተረጋግቻለሁ ያለው ኢሕኣዴግ መታመስ ጀምሯል::
ዳግም "ድርጅታችንን እናድን" የሚለው የቱባዎች ሮሮ ተሰማ::
አቶ በረከት ከሕወሓት ቱባ ጄኔራሎች ጋር ስብሰባ አብዝተዋል::

Image

ከባህር ዳሩ ጉባዬ በኋላ እያስተካከልኩ ነው ተረጋግቻለሁ ያለው ኢህኣዴግ መታመስ መጀመሩን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::እንደ ምንጮቹ ዘገባ ከሆነ በነባር ታጋዮች እና በድል አጥቢያ አርበኞች መካከል አዲስ ሽኩቻ የተነሳ ሲሆን የድርጅታቸውን ኢዲሞክራሲያዊነት ግልጽ በሆነ መልኩ በማሳየት የአባልነት መብታቸውን ለመጠቀም እና አስፈላጊውን ጥያቄዎች እንዲመለሱላቸው አተካሮ እንደተነሳ ታውቋል:: ጥያቄዎቻችን ለምን መልስ አያገኙም በስራዎቻችን ላይ ነባር ታጋዮች ጣልቃ ይገባሉ ህዝባዊ ጥያቄዎችን መልሰን እንገምግም የሚሉ እና ተመሳሳይነት ያለው ጥያቄዎች መነሳታቸውን ተከትሎ አቶ በረከት ስምኦን ይህንን የሚያደርጉ ካድሬዎች ተለይተው ስማቸው ዝርዝር እንዲመጣ ለኢሕኣዴግ ጽ/በት ሃላፊ ለሬድዋን ቢሮዋቸው ጠርተው እንዳዘዙት ምንጮቹ ጠቁመዋል::

መታመስ የጀመረው ኢሕኣዴግ የብኣዴን እና የደቡብ ግንባር አባላቱ እንዲሁም የተከፉ ኦሆዲዶች ውስጥ ለውስጥ እየታገሉት መሆኑን የተነገረ ሲሆን አቶ በረከት ስምኦን በድርጅታቸው ውስጥ ያለውን የካድሬዎች ማጉረምረም ተከትሎ የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ ተከትሎ በየእለቱ ከሕወሓት ጄኔራሎች ጋር ስብሰባ እንደሚቀመጡ ምንጮቹ አክለው የገለጹ ሲሆን ግንቦት ሰባት በምስራቅ አፍሪካ ገኖ ለመውጣት እየገሰገሰ ነው የሚለው ፍራቻ በማሳደሩ ዋናው መወያያ ጉዳያቸው መሆኑን ለምንሊክ ሳልሳዊ የጠቀሱት ምንጮች አቶ በረከት ዳግም የተፈረካከሰውን ድርጅት በማዳን ረገድ ጥገና መጀመራቸውን አስታውቀዋል::

No comments:

Post a Comment