እስክንድር አሰፋ
ኦስሎ
14.07.2013
ሐገራችን ኢትዮጵያ በአንባገነኑ የወያኔ መንግስት በፍትህ መጓደል እና መዛባት ምክንያት ያለምንም ወንጀላቸው ዜጎች መብታቸውን በጠየቁ በየእስር ቤቱ ለሃያ ሁለት አመታት ሲሰቃዩና ሲገድሉ ኖረዋል እየኖሩም ነው። እንዲሁም እንግልቱ ሲበዛባቸው ሐገራቸውንና ቀያቸውን ትተው እግሬ አውጪኝ በማለት በአረብ ሐገራት በአውሮፓ እንዲሁም በአሜሪካ ተበትነው ይኖራሉ።
ከዛም አልፎ ተርፎ በየሄዱበት ሐገር ሰርተው ለመኖር
መከራቸውንና ስቃያቸውን ሲበሉ ይታያል፤ ሌሎችም እንዲሁ ያላደላቸው በበረሐና በባህር
ላይ ህይወታቸውን የሚያጡ ንጹሐን ኢትዮጵያዊያንን ቤቱ ይቁጠረው ። ለዚህ ሁሉ በደል ተጠያቂው ገዢው የወያኔ መንግስት ነው ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ
ለሁለት አስር ዓመታት በወያኔ የግፍ እና የጭቆና ስርዓት ውስጥ የኖረበት ጊዜ በቃኝ በማለት ለነጻነቱ እና ለዲሞክራሳዊ መብቱ መከበር
ሲል ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በቋንቋ እና በጾታ ሳይለያይ በወያኔ ስርዓት ላይ የተቃውሞ ድምጹን ማሰማት ይጠበቅበታል::
ግፍ፣ መከራ፣እና ስቃይ ይበቃል ማለት አለበት።
ለሐገራቸውና ለህዝባቸው በግንባር ቀደምትነት የሚሰዉ ጀግኖች ልጆች ዛሬም አሏት ስለዚህ አሁን በሐገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለጀመሩት ሰላማዊ ትግል ጊዜ ሳናጠፋ ልዩነታችንን ወደኋላ በመተው ጋሻ እንሁናቸው። እንዲሁም በውጪ ሆነው ከሚንቀሳቀሱ ሐይሎች ጋር በመሆን እንደ አስፈላጊነቱ የሚጠበቅብንን ሐገራዊ ድርሻ መወጣት ይኖርብናል።
ስለዚህ የተጀመረውን ትግል ከመሪዎቻችን ጎን በመቆም ግብ ላይ በማድረስ ወያኔን በምድረ ኢትዮጵያ ዳግመኛ እንዳያንሰራራ አድርገን በማስወገድ እኛንም ከስደት ሐገራችንንም ከውርደት እና ከውድቀት የምናድንበት ጊዜው አሁን ነው። ኢትዮጵያ እጆቿን ዘርግታ ትጣራለች ድምጻቸው ለታፈነውና መብታቸው ለተረገጠው ወገኖቻችን አለንላችሁ እንበላቸው። በወያኔ ስርአት መገዛት በቃ ብያለሁ!!!! እናንተስ?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኑር
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
No comments:
Post a Comment