Monday, July 8, 2013

16ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአውሮፓ መንፈሳዊ ጉባኤ በኦስሎ ኖርዌ ተካሄደ


ከሰኔ 28 እስከ 30 2005 . ለሶስት ቀን በተደረገው መፈሳዊ ጉባኤ በርካታ ምእመናኖች እና አባቶች ከተለያየ የአውሮፓ  እና ካናዳ  እንዲሁም መምህር ዘላለም ወንድሙና ዲ.ምንዳዩ ብርሃኑ   ከኢትዮጵያ  በመገኘት አርብ በኖርዌ ሰአት አቆጣጠር  በ10፡ 00 ሰአት በድምቀት ተከፍቷል  ። 
በአባታችን አቡነ ኤልያስ ምረቃ ጉባኤው ሲከፈት በዝግጅቱ ላይ የተለያየ መንፈሳዊ ትምህርቶች በተለያዩ አባቶች   ልዩ ዝግጅቶች አውደርአይ ስነ ጽሁፍ እና የሎተሪ ሽያጭ  ሲቀርብ  በትምህርቱም ጣልቃ በ ዲ.ምንዳዩ ብርሃኑ እና በዘ. ወንገላዊት መንፈሳዊ መዝሙሮች ቀርበዋል ።
እንዲሁም የጉተንበርግ መዘምራን ፤የኦስሎ መዘምራን፤ አባቶች   በተሰጣቸው ሰአት ወረብ ያቀረቡ ሲሆን ወንድም እንዳለ ጌታነህ ክራር በመደርደር ና በመዘመር  ህጻናትም የሚያስደንቅ መዝሙሮችን  አቅርበዋል ።
በዝግጅቱም ላይ ከተለያዩ ምእመናኖች ምስክርነት ሲቀርብ  በመጨረሻም የራራሳችንን ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት የሚያስችል የገንዘብ ማሰባሰቢያ giro በመበተን ህብረተሰቡ የሚችለውን እንዲያዋጣ መልእክቱ  እንዲደርሰው በማደረግ በመጨረሻ በአባታችን በአቡነ ኤልያስ  መልእክት አዘል ንግግር  እና ጸሎት ፕሮግራሙ በሶስተኛው ቀን እሁድ በ 18፡ 30 ሰአት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋዋል ።

No comments:

Post a Comment