Sunday, May 11, 2014

ሙሉጌታ ዘውዴ ለሁለተኛ ጊዜ የግማሽ ማራቶን በኖርዌ ኦስሎ ከተማ አሸነፈ May 10, 2014 video


May 11, 2014
                                                                

ኖርዌ  በየአመቱ የግማሽ ማራቱን እንዲሁም የተለያየ  እሩጫዎችን ታዘጋጃለች በቅድሚያ April 25, 2014 በበርገን ከተማ   እንዲሁም በኦስሎ May 10, 2014 ተካሂዶ ነበር  በሁለቱ ሐገሮች በግማሽ ማራቱን ሩጫዎች ወጣት ሙሉጌታ ዘውዴ አሸናፊ ሆኗል  በበርገኑ እሩጫ 1.09.02 ሲጨርስ በኦስሎ ደግሞ አምስት ደቂቃ በማሻሻል 1.04.09  ሰአት ገብቷል ።

በእለቱ ውድድሩን ልዩ ከሚያደርገው ሁኔታዎች አንዱ ሙሉጌታ የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ የሆነውን የኢሳት አርማ የሚያሳይ ቲሸት መልበሱና  በኢትዮጵያ ውስጥ  የሚፈጸሙትን  የሰብአዊ  መብት ጥሰቶችን  የሚያጋልጥ ጽሁፎች  ለታዳሚው አስነብቧል ከተጠቀሱት በጥቄቱ ኖርዌ  ለአንባገነኑ የወያኔ መንግስት የምታደርገውን የገንዘብና  የተለያዩ  እገዛዎችን   እንድታቆም የሚጠይቅ ነበር  ሙሉጌታ  ውድድሩንም በአሸናፊነት  ሲያጠናቅቅ የኢትዮጵያ ህዝብ አፈናንና የነጻነት ጥማቱን የሚያሳይ እጁን በታሰረ ሰው አምሳል አድርጎ   በተሳካ ሁኔታ  አጠናቋል ።

 ድል ለኢትዮጵያ ሞት ለወያኔ እንዲሁም ለግብረ አባሮቹ 

እስክንድር


No comments:

Post a Comment