Tuesday, May 6, 2014

በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላለፉት ቀናት ሲያካሂዱ የነበረውን የረሀብ አድማ ዛሬ በፕ/ር መስፍን ወልደማርያም አማላጅነት እንዲያቆሙ ተደረገ


ፕ/ር ለእስረኞቹ፣ ስርዓቱ የያዙትን መንገድ እንደማይረዳው እና እንዲህ አይነት ትግል የሚሰራው መጀመሪያ የሰብዓዊነት ትርጉም እና ክብር የሚገባው ስርዓት ሲኖር እንደሆነ አስረድተው እስር ቤት ውስጥ ሆነው ከሚታገሉ ወጥተው እንዲታገሉ በመምከር ቢያንስ አሁን ምግብ እንዲወስዱ አሳምነው ይዘውት የመጡትን ቸኮሌቶች እንዲመገቡ አድርገዋል፡፡ 

6 የሰማያዊ ፓርቲ አመራር እና አባላት ላለፉት ሁለት ሳምንታት ያለምንም ክስ በእስር እየማቀቁ ሲሆን በርካቶችም ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸል ፡፡ በተለይ ወጣት ዮናስ ከድር ፈተና እንዳይፈተን ከመከልከሉም በላይ በደረሰበት ከፍትኛ ድብደባ መንቀሳቀስ እንደማይችል መዘገቡ ይታወሳል፡፡ 


(በፎቶው ላይ የምታዩት የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ በረሀብ አድማው ምክንያት ታሞ ከሆስፒታል መልስ በፖሊስ ጣቢያው በር ላይ እጁ በካቴና እንደታሰረ ፕ/ር መስፍን ሲያነጋግሩት

No comments:

Post a Comment