Thursday, October 25, 2012

በኖርዌይ የሚኖሩ የኢትዮጵያውያ ስደተኞች ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ




 በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግስት በህዝብ እያደረሰ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።

በሰልፉ ላይ ከተለያዩ የኖርዌይ ፓርቲዎች እና ድርጅቶች ተወክለው የመጡ እንግዶች በየተራ ባደረጉት ንግግር በሰብአዊ መብት ረገጣ የሚታወቀውን የኢህአዴግን መንግስት የኖርዌይ መንግስት መደገፉን እንዲያቆምና በስደተኞች ላይ ያለውን አቋም እንዲያስተካክል ጠይቀዋል ።

እንዲሁም በወቅቱ የነበረውን ዝናብና ቅዝቃዜ በመቋቋም ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያ መንግስትን የሚያወግዝ መፈክር በማሰማት ክፍተኛ ተቃውሟቸውን  ገልጸዋል ።
 በዚው እለት ምሽትም የስደተኛው መሐበር  ኮሚቴ በጠራው ስብሰባ ላይ በመገኘት ሰደተኛው ወደፊት ስላለው ሁኔታና
መሐበሩን ለማጥናከር በሚያስችል ሁኔታ መክሮና ተጨማሪ የኮሚቴ አባል በመምረጥ ስብሰባውን በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር አጠናቋል።


No comments:

Post a Comment