Wednesday, March 26, 2014

ትግራይ ከአንድ ፋብሪካ እንደወጣ ሳሙና"

Abraha Desta
አብርሐ ደስታ
ዛሬ አንድ ታሪክ ያስታወሰኝ አስተያየት አነበብኩ። በ97 ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ። በኢህአዴጎችና ቅንጅቶች መካከል የነበረ ክርክር እከታተል ነበር። የማናቸው ደጋፊ ወይ ተቃዋሚ አልነበርኩም። አንድ ሲኔራችን ነበር። ሁሌ ወደ ዶርማችን እየመጣ ስለነዚህ የቅንጅት መሪዎች መጥፎ ታሪክ ይነግረናል፤ ለትግራይ ህዝብ መጥፎ አመለካከት እንዳላቸው (እንዲህ አደረጉ፣ እንዲህ አሉ እያለ)፣ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት የነበሩና ወንጀለኞች መሆናቸው ወዘተ።
በተደጋጋሚ ሲተርክልን የልጁ ዓላማ ግራ ገባኝና "እስቲ ይሄ ተናገሩት ወይ አደረጉት የምትለውን አምጣውና አሳየኝ" አልኩት። "እሺ አሳየሀለሁ" ብሎ በዛው ጠፋ (ቢያንስ ወደ ዶርማችን እየመጣ አይዋሽም)። ከተወሰኑ ቀናት በኋላ "ይሄ አብርሃ የሚሉት ተከታተሉት፣ ቅንጅት ይመስለኛል" ብሎ ለሌሎች ተማሪዎች (የህወሓት አባላት) እንደተናገረ ሰማሁ። ተጠራጠርኩት። ለካ ልጁ የህወሓት ሰላይ ነበር።
የህወሓት ሰላዮች (ሦስተኛ ደረጃ ሰላዮቹ) ያልሆነ ወሬ ሆን ብለው ለህዝብ ይበትናሉ። የተቃዋሚ መሪዎች ያልተናገሩት ነገር ።። "እንዲህ ተናገሩ" እያሉ አሉባልታቸው ይነዛሉ፤ የፖለቲከኞች ስም ለማጥፋትና በህዝብ እንዲጠሉ ለማድረግ። በ97ቱ ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም "ፀረ ትግራይ ህዝብ" አስተያየት እንደሚሰጡ በካድሬዎች ይነገረን ነበር። እኔ እንኳ ልምድ ስላገኘሁ ካድሬዎቹ የሚናገሩት አላምናቸውም።
"ፕሮፌሰር መስፍን መቐለ መጥተው 'የትግራይ ህዝብ ከአንድ ፋብሪካ እንደወጣ ሳሙና ነው' ብለው ሰደቡን" እያሉ የተሳሳተውን መረጃ በሰፊው ለህዝብ ተበተነ። ከምርጫው በኋላ ፕሮፌሰር መስፍን በትክክል የተናገሩትን ነገር እንዲነግረኝ ለአንድ ካድሬ ጓደኛዬ ጠየኩት። መጀመርያ ህወሓቶች ተዘጋጅተው፣ ተደራጅተው ቅንጅቶች የጠሩትን ስብሰባ ለመረበሽ ገቡ (የነገረኝ ካድሬ ከረብሻው አዘጋጆች አንዱ ነበር)። ስብሰባው ተረበሸ (ልጁ "ቅንጅቶች ሰራንላቸው" አለኝ)።
በተደራጀ መልኩ ስብሰባ መረበሽ የህወሓቶች ስትራተጂ መሆኑ በደንብ አውቃለሁ። ምክንያቱም በነ ገብሩና አረጋሽም በ2002 ምርጫ ቅስቀሳ ቅንብሩ ተስርቷል። "ፕሮፌሰሩ ምን ነበር ያሉት?" ብዬ ደግሜ ጠየኩት። "ቃል በቃል አላስታውሰውም ግን 'የትግራይ ህዝብ ከአንድ ፋብሪካ እንደወጣ ሳሙና አንድ ሊሆን አይችልም' የሚል መልእክት ነበረው" አለኝ። "ታድያ ለምን የትግራይን ህዝብ ተሳደቡ አላቹ?" ጠየኩት። "ፖለቲካ ነዋ፣ ሽማግሌው ግን ሰራንለት! የት አባቱ!" ጨመረ።
ህወሓቶች ያልተባለውን መጠምዘዝ ይወዳሉ። ባለፈው ቅዳሜ ከዉቅሮ ህዝብ ሲንነጋገር "ወላጆቻችን የታገሉለት ዓላማ በህወሓት መሪዎች ተጠልፎ ለስልጣን ሆነዋል። ወላጆቻችን መስዋእት የከፈሉት ለስልጣን ሳይሆን ለነፃነት ነው። ህወሓቶች በሰማእታት ስም እየነገዱ ነው። (ወለድና ንነፃነት እምበር ንስልጣን አይተቃለሱን። ሕድሪ ሰማእታትና ተጨውዩ እዩ። ቃልሲ ህዝቢ ትግራይ ዒላምኡ ንክወቅዕ መንእሰይ ትግራይ ንዴሞክራሲ ክቃለስ አለዎ)።" የሚል መልእክት ያለው አስተያየት ሰጠን። ህወሓቶችም "ዓረናዎች ሰማእታትና ሲያንቋሽሹ ዋሉ፤ እንከሳቸዋለን!" እያሉ በስፒከር ለህዝብ ሲያውጁ አመሹ። ሊከሱን አይችሉም። ምክንያቱም እንደዛ አላልንም። ይህ የሚረዳው በአደራሹ የነበረ ህዝብ ብቻ ነው። የነሱን ብቻ የሚሰማ ሰው ግን በመረጃው ለግዜው ሊደናገር ይችላል።
እናም ስም ማጥፋት ስራቸው ነው። ፕሮፌሰር መስፍን "የትግራይ ህዝብ ከአንድ ፋብሪካ እንደወጣ ሳሙና አንድ ሊሆን አይችልም" ስላሉ ምንድነው ችግሩ? "ለትግራይ ህዝብ 'ሳሙና' ብለው ሰደቡት" ያስብላል??? እኛም (ለምሳሌ እኔ) የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ አይደሉም፤ ህዝብ አንድ ዓይነት አመለካከት ወይ አስተሳሰብ ሊኖረው አይችልም ... እያልን ኮ ነው። ይህ ደግሞ ትክክል ነው።
ህወሓቶች ግን የትግራይ ህዝብ በሙሉ የትግራይ አሽከር እንደሆነ ያስባሉ። ይህ ንቀት ነው። እያንዳንዱ የትግራይ ዜጋ የራሱ እምነትና አመለካከት አለው። ምናልባት ፕሮፌሰር መስፍን የተናገሩት የህወሓት ሰላዮች እንደሚነግሩን "የትግራይ ህዝብ ከአንድ ፋብሪካ የወጣ ሳሙና ነው" የሚል ከሆነ ፕሮፌሰሩ ከህወሓቶች ጋር ተመሳሳይ አረዳድ አላቸው ማለት ነው። ህወሓቶችም'ኮ "በመለስ መሬት ዃዂቶ (አቃቅማ) አይበቅልም" ሲሉን "ሁሉም የትግራይ ሰው እንደ የአንድ ፋብሪካ ሳሙና አንድ ዓይነት አመለካከት ሊኖረው ይገባል" እያሉን ነው። ስለዚህ ህወሓቶች ራሳቸው ለሚናገሩትና ለሚያደርጉት ነገር በፕሮፌሰር ስለተነገረ ብቻ እንደ ስድብ መቁጠር ያስተዛዝባል።
ህወሓት ትውልድን እየገደለ ያለ ይመስለኛል። እንዴት ነው ትውልድ የሚገደለው? ትውልድ አስተሳሰብ ነው። የአንድን ትውልድ አስተሳሰብ ከተገደለ ትውልዱ ተገደለ ማለት ነው። አስተሳሰብ እንዴት ይገደላል? ወጣቶች የራሳቸው ፖለቲካዊ (ይሁን ሌላ) አመለካከት፣ አረዳድ፣ አስተሳሰብ እንዳይኖራቸው፣ እንዳያራምዱ ከተከለከሉ አስተሳሰባቸው ተገደለ ማለት ነው። አስተሳሰናቸው ከተገደለ ትውልዱ ተገደለ ማለት ነው።
ትውልድን ላለመግደል ወጣቶች (አዲሱ ትውልድ) በራሱ መንገድ፣ የራሱን አስተሳሰብና ራእይ ሰንቆ መጓዝ አለበት። የፈለገውን አስተሳሰብ የመከተል ነፃነት ሊኖረው ይገባል። ነፃነቱ ከሌለው አስተሳሰቡ አይኖርም። አስተሳሰቡ ከሌለ ለውጡ፣ እድገቱ አይኖርም። ለውጡ ካልመጣ የተፈለገውን ልማት አይኖርም። ልማት ማምጣት ያልቻለ ትውልድ የተበደለ ነው። ስለዚህ ህወሓት ስልጣንን ላለመልቀቅ ሲል ትውልድን መግደል የለበትም።
ስለ ፕሮፌሰር መስፍንና ዶ/ር መረራ ጉዲና በትግራይ ብዙ ስም የማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶ ነበር። አሁን እኔ ስለ ፕሮፌሰር መስፍን በመፃፌ ብቻ "አብርሃ ፀረ ትግራይ ህዝብ ስለሆነው ፕሮፌሰር መስፍን ጥሩ ነገር ይፅፋል። ከነሱ ጋር በማበር የትግራይን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ጥረት ያደርጋል" ብለው የተለመደውን ወሬ መበተናቸው አይቀርም። ስራቸው ስለሆነ ችግር የለውም።
ስለ ዶ/ር መረራም "ደርጋውያን ጠላቶቻችን ..." እየተባለ ይሰበካል። ባለፈው የዉቅሮ ስብሰባችን ሳይቀር "ዓረና ከደርግ ጠላቶቻችን እነ ዶ/ር መረራ ጋር አብሮ እየሰራ ትግራይን ለመጨቆን ተነስቷል" እያሉ ህዝብን ያደናግሩ ነበር። ግን'ኮ የአንድ ሰው ስብእናና ፖለቲካዊ አቋም መገምገም ያለብን በድሮ ህይወቱ ሳይሆን ባሁኑ አመለካከቱ ነው። ለመረጃ እንዲሆነን ግን ዶ/ር መረራ ደርግ አልነበረም። የመኢሶን አባል ነበር። በደርግ ግዜ እኛ የትግራይ ተወላጆች ከደረሰን ግፍ ባልተናነሰ ዶ/ር መረራም ብዙ ግፍና እንግልት የደረሰበት ሰው ነው።
ሁሉም የደርግ ባለስልጣናት ወንጀሎኞች ናቸው ማለት አይቻልም (ሁሉም የህወሓት ባለስልጣናት ጨቋኞች ናቸው ማለት እንደማይቻል ሁሉ)። ግን የደርግ ስርዓት ወንጀለኛ ነው፤ የህወሓት ስርዓትም ጨቋኝ ነው። እንዲህ ሁኖ የደርግ ባለስልጣናት አሁን ስልጣን መያዝ አልነበረባቸውም ብዬ ባልልም ደርግ የትግራይን ህዝብ ጠላት ነበር ካልን የደርግ ኢሠፓ አባል የነበረ ፖለቲከኛ ዶ/ር መረራ ሳይሆን በህወሓት/ኢህአዴግ ዉስጥ ያሉ እነ አቶ ገብረዋህድ (በሙስና የታሰረው)፣ አባዱላ ገመዳ፣ ኩማ ደመቅሳ ... ወዘተ ናቸው።
ህወሓት የአራት ኪሎ ቤተመንግስትን ለመቆጣጠር ሲቃረብ ከኦነግ ጋር ለመስራት ፈልጎ ነበር። ግን ኦነግ የህወሓት አሻንጉሊት ሁኖ የሚያገለግል መስሎ አልታየም። እንደውጤቱም ህወሓት ኦነግን አባሮ የደርግ ወታደሮች (በጦርነት የተማረኩ) አሰባስቦ ኦህዴድን መሰረተ። ስለዚህ ደርጎች የት ናቸው ያሉት? ብለን ሳናጣራ ንፁሓን ሰዎችን መንካት ተገቢ አይደለም። በደርግ ግዜ በሓላፊነት የነበረ፣ የተመዘገበና የሚያስጠይቅ ወንጀል ከሌለው፣ አቋሙ ካስተካከለ ሓላፊነት ቢሰጠው ችግር የለብኝም።
የማልደግፈው ነገር ቢኖር የደርግ ኢሠፓ አባል የነበረ፣ በሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል ሳይኖረው በሀገሩ በሰላም እየኖረ የነበረ ሰው ፖለቲከኛ ሲሆን (ወደ ተቃዋሚ ድርጅቶች ከገባ በኋላ) የደርግ አባል እንደነበርና የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው ተብሎ ይነገረናል። አንድ ሰው የደርግ ይሁን የህወሓት ወንጀል ካለው በሕግ ይጠየቅ፣ አለበለዝያ ግን በፖለቲካ የመሳተፍ መብቱ ሊከበርለት ይገባል። ፖለቲከኛ ስለሆነ የባልፈው ታሪኩ እየመዘዝን የማጥላላት ዘመቻ የምንከፍትበት ከሆነ ግን ችግር ነው።
ህዝብ ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት አለው። የህወሓት ሰላዮችም የተዛባ መረጃ ከመስጠት ታቀቡ። ሁሉም በግዜው ይጋለጣልና።

Sunday, March 23, 2014

ወላይታ ሶዶ ነፃነት አልባዋ የማፊያ ካድሬዎች ከተማ!!


እነ ዳንኤል ተፈራ ከምሽቱ ስድስት ሰዓት ተለቀቁ

ከወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የእስርና እንግልት ማብራሪያ
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራና ድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ በደቡብ ቀጠና በወላይታ ዞንና በሲዳማ ዞን አዋሳ ከተማ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የፓርቲውን የትግል ስትራቴጅክ ዕቅዶች ላይ ማብራሪያ፣ ደንብና ፕሮግራም ለመስጠት እንዲሁም የስራ ጉብኝት ለማድረግ በ 12/07/06 ወደ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተገኝተው ነበር፡፡ በ13/07/06 ደግሞ ከሶዶ ከተማ ስራ አስፈፃሚና ከወረዳ አመራር አባላት ጋር የፓርቲያችንን ደንብ፣ ፕሮግራምና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስመልክቶ የተሰናዳው ውይይት ላይ ለመታደም ከ32 በላይ አመራሮችም ተገኝተው ነበር፡፡

ቅዳሜ በ 13/07/06 ዓ.ም ከአባላት ጋር ባለው ዕቅድ መሰረት የፓርቲያችንን ህጋዊ ሰነዶችን ለወረዳና ለዞን አመራሮች ለመስጠት፣ ቀጣዩን ሀገራቀፍ ምርጫ አስመልክቶ መረጃ ለመለዋወጥ ምርጫችን የነበረው የፓርቲያችን አባል የሆነውና ወጣ ብሎ ፀጥታ የሰፈነበት ግቢ ነበር፡፡ ይህንን ለማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት ነበረን፡፡ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የፖለቲካ ደንብና ፕሮግራማቸውን ለዞንና ለወረዳ አመራሮች ለማስጨበጥ ፈቃድ እንደማያስፈልግ ጠንቅቀን እናውቅም ነበር፡፡

በተለይም ሃለማሪያም ደሳለኝ በሞግዚትነት ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ወላይታ ሶዶ ነፃነት አልባ ከተማ እንደሆነች ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ወላይታ በካድሬ ተወጥራለች፡፡ ዝርዝሩን በቀጣይ እንደምናቀርብ ቃል እየገባን ለአሁን በእኛ ላይ የደረሰውን በቅንጭቡ እንደሚከተለው ለኢትዮጵያ ህዝብና ለታሪክ እናቀርባለን፡፡

1. 32 የሚሆኑ አንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን አመራሮች የተሰባሰቡት ከላይ በገለፅነው አላማና ህገ መንግስታዊ መብታችንን ተጠቅመን ቢሆንም ለውይይት ቅድመ ዝግጅት ስናደርግና ውይይቱን ለመጀመር ስንዘጋጅ መታወቂያ የሌላቸው ከ 8-10 የሚሆኑ ጡንቻቸው የፈረጠመ ግለሰቦች እንደ ኮማንዶ ለውይይት የተገናኝበትን የአባላችንን ጊቢ ሰብረው በመግባት የያዝናቸውን የፓርቲ ሰነዶች፣ ሳምሰንግ ጋላክሲ ስልኮችና ያገኙትን ሁሉ ዘርፈው ሂደዋል፤ አመራሮችን ደብድበዋል፡፡

2. እነዚሁ ደብዳቢዎች ታርጋ ቁጥር በሌላቸው ሞተሮች በመታጀብ ፖሊስ ይዘው በመምጣት ፕሮግራማችንን ለማደናቀፍ በሃይልና በጉልበት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደውናል፡፡

3. ፖሊስ ጣቢያውም እኛን የደበደቡንንና ንብረታችንን የቀሙንን ሲቢል ለባሽ ካድሬዎች በመልቀቅ የአንድነት ፓርቲ 20 አመራሮችን የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሻለቃ ላሊሼ ኦሌ ቢሯቸው አስገብተው ችግሩን እንደሚቀርፍ አመራር ካነጋገሩንና ቃላችንን ከተቀበሉ በኋላ ሞባይሎቻችንን በመንጠቅ እንድንታሰር አድርገዋል፡፡

4. የእስሩ ሰዓት ከቀኑ 5፡00 ጀምሮ ነው፡፡ እንድ ቀፋፊና አስቀያሚ ማጎሪያ ውስጥ ካስቀመጡን በኋላ ከምሽቱ 2፡00 ላይ ህገወጥ ስብሰባ አድርጋችኋል በማለት ቃል ስጡ የሚል ምዝገባና ህገ ወጥ ስብሰባ እንዳደረግን እንድንመሰክር ለማስገደድ ቢሞክሩም እኛ መብታችንን እንደተጠቀምን እንጂ እነሱ እንደተረጎሙት ህገ ወጥ ስብሰባ እንዳላደረግን ሀቁን ስንነግራቸው እንዲሁም ሀሰትን ከመቀበል መታሰር እንደሚቻል የአንድነት አባላት ቁርጠኛ እንደሆንን ሲያውቁ ግራ ተጋብተው የበላይ አካል እስከሚያረጋግጥላቸው ጠብቀው ከእኩለ ለሊት በኋላ (ከምሽቱ 6፡30) በኋላ በእስር ላይ የቆዩ ከ20 በላይ ከፍተኛ አመራሮች እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ ይሄ የሆነው ለመፍታት ታስቦ ሳይሆን ከወረዳ የመጡ አባላት ማደሪያ ቦታ እንዲያጡና ለአደጋ እንዲጋለጡ በማሰብ ነው፡፡

5. ስንታሰር ከተዘረፉ ሞባይሎች ውጭ በፖሊስ ጣቢያ አዛዡ ተይዞ የነበረው የታሳሪዎች ሞባይል ባልታወቀ ነገር ተነክሮ ከአገልግሎት ውጭ ተደርጓል፡፡ ሞባይላችን የተነከረውና ከጥቅም ውጭ የተደረገው በኬሚካል ይሁን በሌላ ነገር አልተረጋገጠም፡፡ የማንኛችንም ሞባይል ግን ከጥቅም ውጭ ሁኗል፡፡ ይሄ የሆነው የፖሊስ አዛዡ አቶ ላሊሼ ቢሮ የታሰረ ሞባይላችን ነው፡፡

ነገ ምን እንደሚገጥመን ማወቅ አይቻልም፡፡ ያረጋገጥነው ነገር ቢኖር ወላይታ ሶዶ ነፃነቷን የተነፈገች፣ በታርጋ አልባ ሞተሮች የምትታመስና ምንም ዋስትናና ህግ የሌለባት ከተማ መሆኗን ነው፡፡ ስለዚህ ነፃነት አልባዋ ወላይታ ነፃ መውጣት አለባት!!!

የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን አመራር አባላት ከምሽቱ 9፡00 ሠዓት
ሶዶ ከተማ

Saturday, March 22, 2014

የኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የአሜሪካ ጉዞ ተስተጓጎለ



የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ስኬታማና በቀጣይነትም ሀገራቸውን መምራት የሚችሉ ወጣት መሪ ተብለው መመረጣቸውን ተከትሎ ከአሜሪካ መንገስት በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ለሶስት ሳምንታት ጉብኝት ወደ አሜሪካ ሊያደርጉት የነበረው የበረራ ፕሮግራም በህወሓት/ኢህአዴግ ተስተጓጎለ፡፡

ትናንት ሌሊት በረራ ለማድረግ ወደቦሌ ኤርፖርት አምርተው የነበሩት ኢንጅነር ይልቃል፣ ስፍራው ደርሰው ፓስፖረታቸውን ቸክ ለማድረግ ለጠየቃቸው አካል (የህወሓት/ኢህአዴግ አሽከር መሆኑ ነው) ሲያሳዩ ተቀብሎ ፓስፖርታቸውን መሐል ለመሐል ሊቀደው ችሏል፡፡ በመቀጠልም ‹በተቀደደ ፓስፖርት› አትሄድም በማለት ጉዞውን ሊያስተጓጉለው ችሏል፡፡ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል ነው ነገሩ፡፡

የዚህ ጉዞ ሙሉ ወጭ የተሸፈነው በአሜሪካ መንግስት ነው፡፡ ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው የሊቀመንበሩ ጉዞ መደረጉ አይቀርም፡፡ ይህ የኢህአዴግ ድርጊት ግን ምን ያህል እንደወረዱ እንደሚያሳይ ነው የመረጃ ምንጫችን የጠቆመው፡፡

ኢንጅነር ይልቃል ለአሸናፊነት የበቁት ‹‹የአሁኑ ወጣት የአፍሪካ መሪና ወደፊትም ለአገራቸው መሪ ሊሆኑ የሚችሉ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ጥሩ ስራ የሰሩ መሪዎች መካከል በተደረገ ውድድር በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት›› መስፈርቱን አሟልተው በመገኘታቸው ነው፡



BREAKING NEWS: Semayawi party chairman barred from boarding flight to the US.

March 21, 2014
(9:05 PM EST) Update: Semayawi Party Chaiman, Eng Yilkal Getnet was barred from boarding his flight to the United States on Friday, March 21, 2014 at Addis Ababa airport. He was scheduled to fly to the US to attend a fellowship program of the Young African Leaders Initiative of the United States State Department. Eng. Yilkal was told to see a TPLF supervisor by airport crew right before boarding time where he was told he would not be flying. His luggage was unloaded from the plane and he stayed at the airport for more than 3 hours thereafter questioned by TPLF agents. He has returned back to his home after 2:00am local time Saturday.
Semayawi Party
———————————————
(9:00PM EST) Eng. Yilkal Getnet, Chairman of the Blue Party (semayawi party) was barred from boarding a plane to the US by TPLF (Ethiopian government security) agents at Bole Airport tonight, March 21, 2014.
Eng. Yilkal was coming to the US as a fellow under “Young African Leaders Initiative” of the United States govt.
Eng. Yilkal’s luggage were unloaded from the plane and he stayed at the airport for more than 3 hours questioned by TPLF thugs.
Stay tune for more updates…
Semayawi party chairman barred from boarding flight
Eng. Yilkal Getnet, Chairman of the Blue Party (semayawi party)

Wednesday, March 12, 2014

In the Name of Democracy: Land Grabbing and Genocide in Ethiopia Full video

“በዴሞክራሲ” ስም የሚደረግ የመሬት ነጠቃና የዘር ማጥፋት ወንጀል በኢትዮጵያ

አይነቱ የመጀመርያ የሆነ የውይይት መድረክ የካቲት 27 2006ዓም/March 6, 2014/ በኦስሎ፣ ኖርዌይ ከተማ ተደረገ። Frontline Club Oslo በተባለ ድርጅት አማካኝነት በኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ስም እየተካሄደ ያለውን የመሬት ነጠቃ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል በተመለከተ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን አካላት በመጥራት ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። በስብሰባውም ላይም 
በውይይቱ ላይ አራት የተለያዩ አካላት ንግግር አድርገዋል።
የውይይቱ የመጀመሪያ ተናጋሪም አቶ አብዱላሂ ሁሴን ሲሆኑ እርሳቸውም የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ልዩ አማካሪና የኦጋዴን ቲቪ ቻናል ሃላፊ ሆነው ሰርተዋል። ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ሲሰሩ በነበሩበት ወቅት ያሰባሰቡትን መረጃ በቪድዮ የተደገፈ ዶክመንተሪ በዚህ ስብሰባ አቅርበዋል። የቀረበው ቪድዮ በክልሉ ፕሬዝዳንት እና በክልሉ ባለስልጣናት፣ ፖሊሶችና የጸጥታ አካላት መካከል የተደረጉ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን አካቷል። በክልሉ እየተደረገ ያለውን ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ማሰርን፣ ማሰቃየትን፣ ግድያን እና በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እና ስቃይ ራሳቸው የጸጥታ ኃይሎች የሰጡትን ምስክርነት ዶክመንተሪው አካቷል። በመንግሥት ወታደሮችና ፖሊሶች አማካኝነት በክልሉ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ወንጀሎች ዶክመንተሪው በማስረጃነት የሚያሳይ በመሆኑ በቀጣይነት ሄግ ለሚገኘው አለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ አቶ አብዱላሂ አመልክተዋል።
በመቀጠል ንግግራቸውን ያደረጉት እውቁ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር የሆኑት የተከበሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ ሲሆኑ የኖርዌይ ህዝብና መንግስት ለኢትዮጵያውያን ብሎም ለአጠቃላይ ሰብዓዊነት እያደረጉ ያለውን አስተዋጽዖ በማድነቅ ንግግራቸውን ጀምረዋል። በግጭትና በተለያዩ የፖለቲካ ቀውሶች ምክንያት በዓለማችን ተጠቂ ህዝቦች ካንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የመሰደዱ ሁኔታ የተለመደ መሆኑን በማመልከት ብዙ ስደተኞች ወደ ኖርዌይ የሚመጡበት ምክንያት አገሪቷ ሃብታም እና የበለጸገች ስለሆነች ብቻ ሳይሆን የአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እና ለሰብዓዊነት ክብር ቅድሚያ በመስጠቷ መሆኑን አቶ ኦባንግ አመልክተዋል።
ሙሎውን ዘገባ ከቪዲዮ ይከታተሉት




Sunday, March 9, 2014

Female activists arrested following anti government protest in Ethiopia

Semaywi Party women members and supporters arrested following the women protest against injustice during women's great run in Addis Ababa today March 09, 2014.



በሴቶች ነፃነት ቀን በሚከበርበት ወቅት የኢህአዲግ አምባገነን ስርዓት ተቃውሞ አሰምታችኋል በሚል የሰማያዊ ሴቶችንና አብረዋቸው የነበሩትን ሁሉ አስሯል፡፡ እጅግ አስገራሚው ክስተት ደግሞ የኢህአዲግ ሴቶች ሊግ ፣ የሴቶች ፎረም(ኢህአዲግ የሚያዘው) እና አገዛዙ ያስተባበራቸው በርካታ ማህበራት በነፃነት ሩጫውን ያሻቸውን እያሉ ሲያጠናቅቁ ነፃነትን እንፈልጋለን ፣ ፍትህ ናፈቀን ፣ የህሊና እስረኞች ይፈቱ ፣ ኑሮ መረረ ፣ ሴቶችን በማስፈራራት አምስት ለአንድ መጠርነፍ ይቁም እና የመሳሰሉትን የተቃውሞ ድምፅ ያሰሙ የነበሩ ሰላማዊ ታጋዮች መታሰራቸው ነበር፡፡ በዚህም የኢህአዲግ ስርዓት በሴቶች ቀን የሴቶችን መብት እንደማያከብር በይፋ አረጋግጧል ፤ ሀሳባቸውን በነፃነት መግለፃቸው ወንጀል ሆኖ አፍኗቸውል፡፡ 

ከስር የምታዩት ምስሎች የኢህአዲግ ደህንነቶችና ፖሊሶች ሴቶችን እየለቀሙ ሲያፍሱና ሲይዙ ያሳያል

ድል ለኢትዮጵያ ሴቶች 
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

Semayawi Party- Ethiopia's photo.