Saturday, March 22, 2014

የኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የአሜሪካ ጉዞ ተስተጓጎለ



የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ስኬታማና በቀጣይነትም ሀገራቸውን መምራት የሚችሉ ወጣት መሪ ተብለው መመረጣቸውን ተከትሎ ከአሜሪካ መንገስት በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ለሶስት ሳምንታት ጉብኝት ወደ አሜሪካ ሊያደርጉት የነበረው የበረራ ፕሮግራም በህወሓት/ኢህአዴግ ተስተጓጎለ፡፡

ትናንት ሌሊት በረራ ለማድረግ ወደቦሌ ኤርፖርት አምርተው የነበሩት ኢንጅነር ይልቃል፣ ስፍራው ደርሰው ፓስፖረታቸውን ቸክ ለማድረግ ለጠየቃቸው አካል (የህወሓት/ኢህአዴግ አሽከር መሆኑ ነው) ሲያሳዩ ተቀብሎ ፓስፖርታቸውን መሐል ለመሐል ሊቀደው ችሏል፡፡ በመቀጠልም ‹በተቀደደ ፓስፖርት› አትሄድም በማለት ጉዞውን ሊያስተጓጉለው ችሏል፡፡ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል ነው ነገሩ፡፡

የዚህ ጉዞ ሙሉ ወጭ የተሸፈነው በአሜሪካ መንግስት ነው፡፡ ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው የሊቀመንበሩ ጉዞ መደረጉ አይቀርም፡፡ ይህ የኢህአዴግ ድርጊት ግን ምን ያህል እንደወረዱ እንደሚያሳይ ነው የመረጃ ምንጫችን የጠቆመው፡፡

ኢንጅነር ይልቃል ለአሸናፊነት የበቁት ‹‹የአሁኑ ወጣት የአፍሪካ መሪና ወደፊትም ለአገራቸው መሪ ሊሆኑ የሚችሉ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ጥሩ ስራ የሰሩ መሪዎች መካከል በተደረገ ውድድር በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት›› መስፈርቱን አሟልተው በመገኘታቸው ነው፡



No comments:

Post a Comment