
ህዝባዊ ሀይሉ ” ለተራ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስንል በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት የሃገሪቱን ውድ ልጆች በከንቱ የሚማግድ ጀብደኛ እንቅስቃሴ አናደርግም። በውሸት ተስፋ ህዝብን አንመግብም። አይናችንን ከዋናው የኢትዮጵያና የህዝቧ ጠላት ከሆነው ከወያኔ ላይ አንስተን በሌሎች ወያኔን እቃወማለሁ በሚሉ ሃይሎች ላይ አንተክልም። ከወያኔ ሌላ ወደ ጎን የምንዋጋው፣ የምንጨቃጨው አታካራ የምንገጥመው ምንም ሃይል አይኖርም። ወያኔን ለመምታት ህዝባዊ ሃይሉ የጨበጠው ቡጢ ወገኖቻችን በፍቅር ለመጨበጥ የሚዘረጉ ጣቶች እንዳሉት በጸረ ወያኔ ዴሞክራሲያዊ ትግሉ ከልባቸው ለመተባበር ለሚፈልጉ ሃይሎች ሁሉ ግልጽ እናደርጋለን።” ሲል አትቷል።
በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል አመራሮች ላይ መንግስት የመግደል ሙከራ ማድረጉና መክሸፉ ይታወሳል። በቅርቡ ደግሞ ከአመራሩ ጋር ለመደራደር ጥያቄ ማቅረቡና ንቅናቄው ውድቅ ማድረጉ ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment