Tuesday, August 14, 2012

ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳዉ የተገደለዉ በመንግስት እጅ ነዉ ተባለ


ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳዉ የተገደለዉ በመንግስት እጅ ነዉ ተባለ



Rate This

Image
ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳዉ
የኢህአፓ ድምፅ የሆነዉ ፍኖተ ህብረት ሬድዮ በነሐሴ 5/2004 ዘገባዉ ለሕዝብ ይፋ እንዳደረገዉ የጀርመን ድምፅ የአማርኛ ፕሮግራም ባልደረባ በመሆን ለረጅም ጊዜ ያገለገለዉ ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳዉ ሐምሌ 7 ቀን 2004 ዓ.ም የደረሰበት እና ለህልፈተ ሕይወት የዳረገዉ ከባድ የመኪና አደጋ ድንገተኛ ሳይሆን ሆን ተብሎ በመንግስት የደህንነት ሰዎች የተቀነባበረ የግድያ ሴራ ነዉ ብሏል ፡፡
ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳ ሐምሌ 6/2004 በወንድሙ የምረቃ በዓል ላይ በሐዋሳ ዩንቨርሲቲ ተገኝቶ በማግስቱ ማለትም በሐምሌ 7/2004 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በሚመለስበት ሰዓት በመንገድ ላይ የመንግስት የደህንነት አካላት አስቁመዉ ማንነቱን ከጠየቁ በኃላ “አንተ ነህ የምታስቸግረን” በማለት ዝተዉበት ነበረ ያለዉ የፍኖተ ሕብረት ዘገባ ዝዋይ ለመድረስ 40 ኪሎሜትር ሲቀረዉ አንድ ከባድ የጭነት መኪና ሆን ብሎ በመግጨት ጋዜጠኛዉን ለሞት ዳርጎታል ብሏል፡፡
ከአደጋዉ በኃላም ለምርመራ በሚል ሰበብ ጋዜጠኛዉ የህክምና እርዳታ እንዳያገኝ የመንግስት የደህንነት ሐይሎች ያስተጓጎሉት ሲሆን ፤ በመጨረሻም ጋዜጠኛዉ ሊሞት ችሏል ሲል ዘገባዉ ጠቁሟል፡፡
የጋዜጠኛዉን መኪና የገጨዉ ከባድ መኪና ታርጋ አልነበረዉ ሲል የጠቆመዉ የፍኖተ ህብረት ዘገባ ይህ የወያኔ ሴራ ለመሆኑ አንዱ አመላካች ነዉ ብሏል፡፡
በመጨረሻ የወያኔ መሪዎች ለአፈናና ግድያ ያሰለጠኑዋቸዉ ደህንነቶች በአደባባይና በስዉር የሚፈፅሙትን ግድያ ለማስቆምና ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ ህዝቡ በመተባበር መንቀሳቀሰ እንዳለበት በዘገባዉ ተጠቁሟል፡፡

No comments:

Post a Comment