Friday, August 3, 2012

ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት አደንዛዥ ዕፅ ወደ ለንደን ለማስገባት ስትሞክር ተያዘች

ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት አደንዛዥ ዕፅ ወደ ለንደን ለማስገባት ስትሞክር ተያዘች

ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- “ካናቢስ”የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ ወደ ለንደን ለማስገባት ስትሞክር የተያዘች አንዲት ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት  የ33 ወር እስራት ተፈረደባት።
እንደ አሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባ፤በዋሽንግተን የኢትዮጵያኤምባሲ ውስጥ  የምትሠራው አመለወርቅ ወንድማገኝ    የተባለች ዲፕሎማት፤ የዲፕሎማቲክ ከለላዋን በመጠቀም 56 ኪሎ ግራም የሚመዝንካናቢስ-  በሄትሮን አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ለንደን ለማስገባትስትሞክር ነው የተያዘችው።

ጉዳዩን ሲከታተለው የነበረውና በምዕራብ ለንደን የሚገኘው  የአይስወርዝ ክራውን ፍርድ ቤትም ተከሳሿ ዲፕሎማት በ ዕጽማዘዋወር የቀረበባትን ክስ አምና በመቀበሏ በ33 ወራት እስራት እንድትቀጣ ውሳኔ አሳልፏል።

የ36 አመቷ አመለወርቅ ከአዲስ አበባ ከመነሳቷ በፊት አንድ ሰው 3 ሻንጣዎችን አድርሽልኝ ብሎ እንደሰጣት ተናግራለች።  በሻንጣዎች ውስጥ ያለው ስጋና ቅመማቅመም መስሎአት እንደነበርም ገልጻለች።

No comments:

Post a Comment