Thursday, November 28, 2013

ረዳት ፕሮፌሰር ግዛቸው ሽፈራው መጻፋቸውን አስመረቁ


በዳዊት ሰለሞን

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት የኬሚካል ፕሮሰስ ኢንዳስትሪን ለሰላሳ አመታት በማስተማር በመስኩ ከፍተኛ እውቅናን ያተረፉት ረዳት ፕሮፌሰር ግዛቸው ሽፈራው ‹‹the process technology of chemical and allied industries"በማለት የሰየሙትን ቅጽ አንድ የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍ በዩኒቨርስቲው በተዘጋጀ ደማቅ ስነ ስርዓት በማስመረቅ አበርክተዋል፡፡

500 ገጾችን የያዘው ጥልቅ ምርምር የተደረገበት መጽሐፍ በኢትዩጵያዊ ባለሞያ ተዘጋጅቶ መቅረቡ የመጀመሪያው በመሆኑም ግዛቸው ከሞያ አጋሮቻቸው አድናቆትን አትርፈውበታል፡፡
ከለንደን ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ማስተርሳቸውን የሰሩት ምሁሩ ከጋናው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በኬሚካል ኢንጂነሪንግ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡የጋናውን ዩኒቨርስቲ ከመቀላቀላቸው ቀደም ብሎ ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የሶስተኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነበሩ፡፡
በተለያዩ አለም አቀፍና በአገር ውስጥ በሚገኙ ተቋማት በመስራት ለአገራቸው እውቀታቸውን ያበረከቱት ረዳት ፕሮፌሰሩ በኢትዩጵያ እውነተኛ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ይገነባ ዘንድ በሰላማዊ መንገድ በመደራጀት ያመኑበትን በአደባባይ በመግለጽ ይታወቃሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት ግዛቸው ፓርቲውን ለመጪዎቹ አራት አመታት ለመምራት ራሳቸውን በዕጩነት ማቅረባቸው ይታወቃል፡

No comments:

Post a Comment