Tuesday, May 6, 2014

UDJ Andinet Party Protest Rally in Addis Abeba 6 May ,2014





ADDIS ABABA - Thousands of supporters of Ethiopia's leading opposition party Unity for Democracy and Justice (UDJ) or Andinet called for the unity of the Ethiopian people in a bid to remove the despotic and anti-Ethiopia ruling party.
Leading the crowd with slogans is vocal opposition figure Habtamu Ayalew, foreign relations chief of UDJ. The charismatic Habtamu has been a fearless force whose inspiring messages unify the youth by transcending ethnic and religious lines.

Protesters called for the release of all political prisoners, journalists as well as prisoners of conscience, a call that has so far fallen on deaf ears of the highly corrupt and hopelessly brutal regime that has misruled Ethiopia for the last 23 years (Better video clips pending).

በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላለፉት ቀናት ሲያካሂዱ የነበረውን የረሀብ አድማ ዛሬ በፕ/ር መስፍን ወልደማርያም አማላጅነት እንዲያቆሙ ተደረገ


ፕ/ር ለእስረኞቹ፣ ስርዓቱ የያዙትን መንገድ እንደማይረዳው እና እንዲህ አይነት ትግል የሚሰራው መጀመሪያ የሰብዓዊነት ትርጉም እና ክብር የሚገባው ስርዓት ሲኖር እንደሆነ አስረድተው እስር ቤት ውስጥ ሆነው ከሚታገሉ ወጥተው እንዲታገሉ በመምከር ቢያንስ አሁን ምግብ እንዲወስዱ አሳምነው ይዘውት የመጡትን ቸኮሌቶች እንዲመገቡ አድርገዋል፡፡ 

6 የሰማያዊ ፓርቲ አመራር እና አባላት ላለፉት ሁለት ሳምንታት ያለምንም ክስ በእስር እየማቀቁ ሲሆን በርካቶችም ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸል ፡፡ በተለይ ወጣት ዮናስ ከድር ፈተና እንዳይፈተን ከመከልከሉም በላይ በደረሰበት ከፍትኛ ድብደባ መንቀሳቀስ እንደማይችል መዘገቡ ይታወሳል፡፡ 


(በፎቶው ላይ የምታዩት የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ በረሀብ አድማው ምክንያት ታሞ ከሆስፒታል መልስ በፖሊስ ጣቢያው በር ላይ እጁ በካቴና እንደታሰረ ፕ/ር መስፍን ሲያነጋግሩት

Monday, May 5, 2014

Aid as a means of repression Ethiopians in Odda ,Norway April 29,2014




https://www.youtube.com/watch?v=X7r7eu3qa3E

ESAT Special Ethiopian Libration Day 05 May 2014

 
የአርበኞችን 72ተኛ አመትን ቀን በማስመልከት የተዘጋጀ ልዩ ዝግጅት ኢሳት ይዞላችሁ ቀርቧል ሊንኩን ጫን በማድረግ ይመልከቱ
 እግረ መንገዳችሁንም ኢሳትን በሁለት እግሩ እንዲቆም የእናንተን ድጋፍ ይሻልና አለንልህ በሉት!!

           የኢትዮጵያኑች እውነተኛ ሚዲያ ኢሳት
                                         
                      እስክንድር

http://ethsat.com/video/esat-special-ethiopian-libration-day-05-may-2014/

Sunday, May 4, 2014

አንድነት ፓርቲ ያካሄደው ሠላማዊ ሠልፍ


አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ እሁድ፤ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓም «የእሪታ ቀን» በሚል አዲስ አበባ ውስጥ የተቃውሞ ሠላማዊ ሰልፍ አካሄደ። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተለያዩ ብሶቶችን የሚያንፀባርቁ መፈክሮች፥ የተሰሙበትና አልባሳትም የታዩበት እንደነበር የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል።

ሰልፈኞቹ፤ መንግሥት የመብራት፣ የስልክ፣ የውሃና ሌሎች የመሰረተ-ልማት አቅርቦቶችን እንዲያሻሽልና መልካም አስተዳደርን እንዲያሰፍን ጠይቀዋል። የታሰሩ ጦማሪያን፣ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱም አሳስበዋል። የአንድነት ፓርቲ ፕሬዚዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው በሰልፉ ላይ ባሰሙት ንግግር፤ ባለፉት ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች፣ ዩኒቨርስቲዎች እና ትምህርት ቤቶች፤ የተካሄደዉ የግድያ የድብደባ እና የእስራት እርምጃዎችን «ግዙፍ የሠብዓዊ መብት ጥሰቶች» ሲሉ በጥብቅ አዉግዘዋል።


በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ አዲስ አበባን የጎበኙት የአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ኢትዮጵያ ለሲቪክ ማኅበራትና ለጋዜጠኞች የተሻለ ነፃነት እንድትሰጥ መጠየቃቸዉ እና ባለፈዉ ሳምንት ማለቂያ የታሠሩት የድረ-ገፅ ጸሀፍትና ጋዜጠኞች ጉዳይም እንዳሳሰባቸዉ መግለፃቸዉ ይታወቃል። ጋዜጠኞች በህትመት፤ በኢንተርኔትም ሆነ በትኛዉም ዓይነት መገናኛ ብዙሃን የሚያከናዉኑት ኅብረተሰቡን እንደሚያጠናክር፤ እንደሚያነቃቃና ፤ለዴሞክራሲም መጠናከርና ድምፅ ሊሆን እንደሚችልም ኬሪ መግለፃቸዉ ይታወሳል። 

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተለያዩ ብሶቶችን የሚያንፀባርቁ መፈክሮች እና አልባሳትም የተሰሙበትና የታዩበት እንደነበር የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል። ሠልፉን በቦታው ተገኝቶ የተከታተለው ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሮ ልኮልናል።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማጫወቻውን ይጫኑ። 
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ


አንድነት ፓርቲ እሪታ ቀን ብሎ ባዘጋጀው ተቃውሞ ሰልፍ ከተሰበሰቡት ፎቶዎች ሚያዚያ 26, 2006

አንድነት ፓርቲ እሪታ ቀን ብሎ ባዘጋጀው ተቃውሞ ሰልፍ ከተሰበሰቡት ፎቶዎች ሚያዚያ 26, 2006

Thursday, May 1, 2014

አቶ አንዷለም አራጌ በቃሊቲ እስር ቤት ከሌሎች እስረኞች በተለየ ሁኔታ እሱ ላይ ብቻ ትኩረት ተደርጎ መብቱ በመጣሱ፤ እንዲሁም በተፅእኖና ክልከላ ሰለባ በመሆኑ ከትላንት ጀምሮ የረሃብ አድማ ላይ መሆኑን ቃሊቲ የሚገኙ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለጹ


የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ም/ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረውና ‹‹ሽብርተኛ›› በሚል የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት አቶ አንዷለም አራጌ በቃሊቲ እስር ቤት ከሌሎች እስረኞች በተለየ ሁኔታ እሱ ላይ ብቻ ትኩረት ተደርጎ መብቱ በመጣሱ፤ እንዲሁም በተፅእኖና ክልከላ ሰለባ በመሆኑ ከትላንት ጀምሮ የረሃብ አድማ ላይ መሆኑን ቃሊቲ የሚገኙ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለጹ፡