Tuesday, July 8, 2014

የሰማያዊ ፓርቲ ብ/ም/ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ በመኖሪያ ቤቱ ታገተ



የሽዋስ አሰፋ በቤቱ እንዳለ ብዛት ያላቸው የፌደራል ፖሊሶች አከባቢዉን በመክበብ ጎረቤቶቹን ካራቁ በኋላ እሱን ብቻውን ቤቱ ውስጥ በማፈን እስካሁን ድረስ ቤቱን እየበረበሩ መሆኑን ባለቤቱ አሳውቃለች፡፡
ባለቤቱ ከስራ በጓረቤቶቻቸው ተደውሎላት ወደ ቤቷ ሄደች ቢሆንም ወደ አካባቢው እንዳትቀርብ ታዛለች፡፡ በአሁኑ ሰዓት አካባቢው ላይ በርካታ ፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች ውጥረት አንግሰውበታል፡፡
ጉዳዩን እየተከታተልን እናሳውቃለን!
---------------------------------------------------



የአደይ ኣልጋነሽ ልጆች ኣደጋ ላይ ናቸው
በቅርቡ ‘በአገር ዉስጥና በዉጭ አገር ከሚገኙ አሸባሪ ኃይሎች ጋር በመተባበር ህገ መንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ አሲረዋል’ በሚል በፀረ-ሽብር ህጉ ተከሰው እስር ቤት የሚገኙት አደይ አልጋነሽ ገብሩ ሶስት ልጆቻቸው በተንከባካቢ ማጣት አደጋ ላይ ወድቀዋል።
አደይ ኣልጋነሽ የ5 ልጆች እናት ሲሆኑ ሶስቱ እራሳቸውን መምራት የማይችሉ ህፃናት ናቸው። ባለቤታቸውንና የልጆቻቸውን አባት ከ9 ዓመት በፊት በሞት ያጡ ሲሆን እነዚህን ህፃናት ጠላ በመጥመቅ ነበር የሚያሳድጓቸው። ታድያ በአሁኑ ጊዜ አደይ አልጋነሽ በ"ሽብርተኝነት" ተከሰው እስርቤት በመግባታቸውና ልጆቹን በቅርበት የሚንከባከባቸው ጧሪ በመጥፋቱ ልጆቹ ትምህርታቸውን ኣቋርጠው ለጎዳና ተዳዳሪነት ተዳርገዋል።
በፎቶው ላይ የሚታዩት ሶስቱ የአደይ አልጋነሽ ልጆች

፩) ግርማነሽ ታደሰ ዕድሜዋ 15 የትምህርት ደረጃ 10ኛ
፪) ዘነበ ታደሰ ዕድሜው 13 የትምህርት ደረጃ 7 ኛ
፫) ገብረሂወት ታደሰ ዕድሜው 9 የትምህርት ደረጃ 4ኛ ናቸው።
የኒህን ጀግና እናት ልጆች ከጎዳና ህይወት የመታደግ የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት ነው። ስለሆነም በቅርብ ቀን ልጆቹን ሊንከባከባቸው በሚችል ሰው (ሞግዚት) ስም ኣካውንት ስለሚከፈትላቸው ደጋፍ እንድታደርጉላቸው ከወዲሁ ትጠየቃላችሁ።
የጀግናዋ እናት አደይ ኣልጋነሽ ገብሩ ልጆችን ከጎዳና ተዳዳሪነት በማውጣት ህይወታቸው እንታደግ!
-------------------------------





ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ሀብታሙ አያሌው ታሰረ
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ የሆነውና በቅርቡ ሐገርና ፖለቲካ የሚል መጽሐፍ ለንባብ ያበቃው ወጣቱ ፖለቲከኛ ሐብታሙ አያሌው ዛሬ ማለዳ ከመኖሪያ ቤቱ እንደወጣ ቦሌ ፍላሚንጎ አካባቢ በፖሊሶች ተይዞ መወሰዱን የአይን እማኞች ይፋ አድርገዋል፡፡
ሐብታሙ በምን ምክንያት በፖሊሶች እንደተያዘና ወዴት እንደተወሰደ የአይን እማኞቹ ባያረጋግጡም የፓርቲው አመራሮች በአሁኑ ሰዓት ፍላሚንጎ አካባቢ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣብያ በማምራት ጉዳዩን ለማጣራት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment