
አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ደግሞ በምክትል ሊቀመንበርነት መርጧል ።
ጉባኤው ዛሬ ካካሄደው የንቅናቄው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ጋርም ሰባት የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አባላትን ጨምሮ 15 የንቅናቄው ስራ አስፈፃሚ አባላትን መርጧል ።
በዚህም መሰረት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝንና አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ጨምሮ አቶ ሬድዋን ሁሴን ፣ አቶ መኩሪያ ሀይሌ ፣ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ፣ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ፣ አቶ ዓለማየሁ አሰፋ ፣ አቶ ደሴ ዳልኬና አቶ ተስፋዬ በልጂጌ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ተደርገው ተመርጠዋል ።
እነዚህ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አባላትን ለሚያካትተው የደኢህዴን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ደግሞ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ፣ አቶ መለሰ ዓለሙ ፣ ወይዘሮ ሙፍሪያት ካሚል ፣ አቶ ታገሰ ጫፎ ፣ አቶ ደበበ አበራና አቶ ሳኒ ረዲ በአባልነት ተመርጠዋል ።
በጉባኤው በአጠቃላይ 250 አባላትን በባህር ዳር ከተማ በሚካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ የተመረጡ ሲሆን ፥ ከነዚህ መካከልም 45ቱ የምክር ቤቱ አባላት ናቸው ።
No comments:
Post a Comment