Friday, February 7, 2014

Breaking - Ethiopia: Senior Official of the opposition UDJ, Asrat Tassie, detained in Addis Abeba

Image
Ethiopian opposition party UDJ senior official Asrat Tase has been arrested today for writing article that criticized a recent ETV documentary that accuses several Ethiopian journalists and opposition figures as terrorists. The court ordered Ato Asrat to appear in court next week. 

Also EPRDF is Ready to detain 5 of UDJ Officials.
የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት አባልአቶ አስራት ጣሤ ታሰሩ::
ኢህአዴግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱ ተጋለጠ
#Ethiopia #EPRDF #UDJ #Justice
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ፣ በክስ ሂደት ላይ የነበረው የአኬልዳማ ዶክመንተሪ በድጋሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መታየቱን ተከትሎ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ከፃፉት አስተያየት ጋር በተያያዘ “ዘለፋ አዘል ጽሑፍ” ጽፈዋል በሚል ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ በተላለፈባቸው መሰረት በዛሬው እለት በፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የተገኙ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ለ7 ቀን ታስረው በቀጣዩ ሳምንት እንዲቀርቡ በማለት የእስር ትዕዛዝ ወስኖባቸዋል ፡፡

ኢህአዴግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱ ተጋለጠ ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ 4 አመራሮችና አባላት እንዲታሰሩ ኢህአዴግ ወስኗል፤ የክስ ቅድመሁኔታዎች በፍርድ ቤት መጠናቀቃቸውን ታውቋል፡፡

ኢህአዴግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱን የፍትህ ሚ/ር ምንጮች አጋለጡ፡፡ ምንጮቹ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት በኢህአዴግ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ክስ እንዲከፈትባቸውና እንዲታሰሩ የተወሰኑት የአንድነት አባላት በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም የመጀመሪያው ዙር ክስና እስር በ4 አመራሮችና አባላት ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡


No comments:

Post a Comment