የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት የዋልደባ ገዳምን ለማፍረስ የተሰማሩ የወያኔ ቡል ዶዘር መኪኖችን ሙሉ ለሙሉ አጋየ።
ይህንን ተከትሎም መላው የአካባቢው ምዕመናን ለኢ.ሕ.አ.ግ ሰራዊት ያላቸውን አድናቆት እየገለጹ ይገኛሉ።
የአርበኞች ድምጽ፡ ቀድሞም ለሕዝቡና ለሀገሩ ሕልውና ሲል ውድ ሕይወቱን ቤዛ እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ከወያኔ መከላከያ፤ የፖሊስና ልዩ ሃይል ታጣቂዎች ጋር እልህ አስጨራሽ የሆኑ አውደ-ውጊያዎችን በመፈጸም የወገን ጥቃት መላሽነቱን በማረጋገጥ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።አናሳው የወያኔው ቡድን የገዳሙን ሕልውና መፈታተን ከጀመረበት እለት አንስቶ ከሃገሬው እስከ ውጭ ሀገር የሚኖረው መላው ኢትዮጵያዊያን ምዕመናን የገዳሙን ሕልውና ለማስጠበቅ በጸሎት፣ በተቃውሞና ከዚህም ባለፈ የአካባቢውን ምዕመናን በስርዓቱ የማፈኛ ጣቢያዎችን በአስፈጻሚ የዳኝነትና የፖሊስ አባላት ላይ ቁርጠኝነት እርምጃዎችን እየወሰዱ ቢሆንም አምባገነኑ የወያኔው ቡድን ከጀመረው የጥፋት ተልዕኮ ሊታቀብ አለመቻሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ይንን ተልዕኮ በአካባቢው ተሰማርቶ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም ወያኔ ገዳሙን ለማፍረስ ባሰማራባቸው ቡል ዶዘር መኪኖች ሙሉ ለሙሉ በማጋየት ለወራት ያህል አንጀቱ እያረረ የቆየውን የመላው ሕዝብ ክርስትያን ምዕመናን እምባ በማበስ ግንባሩን የሕዝብና የሀገር ተቆርቋሪነቱን ማስመስከሩ እንደቻለ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ባለፈው ሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም በወያኔ ተሽከርካሪ ዶዘር መኪኖች ላይ የፈጸመውን የማጋየት እርምጃ ተከትሎ መላው የአካባቢው ምዕመናን ለግንባሩ ሰራዊት ያለውን አድናቆት እየገለጸ ከመሆኑም ባሻገር ከግንባሩ ጎን በመሰለፍ ይህን ታሪክ አውዳሚ ስርዓት ለማስወገድ ከፍተኛ የሆነ ወኔና መነሳሳትን ፈጥሮልናል ሲሉ ብዛት ያላቸው ወገኖች እየገለጹ ይገኛሉ።
የኢሕአግ ሰራዊት የዋልድባ ገዳም ለማፍረስ በተሰማሩ ዶዘሮች ላይ በወሰደው የማጋየት እርምጃ የተነሳ ለዚሁ የማፈረስ ተልዕኮ የተሰማሩ ሹፌሮች በሁኔታው ተደናግጠው በመሸሻቸው ስራው ተቋርጦ እንደሰነበተም ለማወቅ ተችሏል።
በዚህ መሰረት ከፍተኛ ድንጋጤ የገባው የወያኔ ቡድን ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት የተወሰደበትን እርምጃና ኪሳራ በአፀፋ ለመመለስ በጀመረው እርምጃ ቁጥራቸው አራት የሚደርሱ የገዳሙ አባቶችን ጨምሮ ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች አፍኖ ለጊዜው ወደ አልታወቀ እስር ቤት እንደወሰዳቸው የምንጮቻችን መረጃ ይጠቁማል።
አናሳውና ጠባቡ የወያኔ ቡድን ከዚህ ቀደም የሕዝቡን የተቃውሞ ስሜት በመገንዘብ ብዛት ያለው የጦር ሰራዊት በገዳሙ ዙሪያ ያከማቸ መሆኑ ሲታወቅ ሰሞኑን ዳግም በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት የተወሰደበትን የጥቃት እርምጃ ተከትሎ ተጨማሪ ጦር ወደ አካባቢው በማጓጓዝ ላይ መሆኑን የአይን እማኞች አረጋገጡ።
እንደ ምንጮቻችን መረጃ ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በዋልድባ ገዳም ላይ እየታየ ያለው ውጥረት ከምንጊዜውም በላይ እየበረታ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀው የአካባቢው ምዕመናንም ወያኔ ከዚህ እኩይ ተግባሩ ካልተቆጠበና የታሰሩት የገዳሙ አባቶችና የአካባቢው ነዋሪዎችን እስካልፈታ ድረስ የጀመሩትን ተቃውሞ እንደሚገፉበትና መላው ኢትዮጵያዊያን ከጎናቸው እንዲሰለፉ ጥሪ እያደረጉ መሆኑን የምንጮቻችን መረጃ ያመለክታል።
ለእምነቱና ለሃይማኖቱ ቀናኢ የሆነው መላው የጎንደር ማህበረሰብ በአምባገነኑ የወያኔ ቡድን ገዥ ቡድን የተቃጣበትን እምነትን የማፍረስ ተልዕኮ ለመቋቋምና ለመከላከል ቁርጠኛ ሆኖ ታጥቆ ከተነሳ ወራቶችን እያስቆጠረ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ከዚህ የተከፋ ሕዝብ ጎን በመቆም ሰሞኑን ለወሰደው እርምጃ አድናቆትን እየገለጹ ከመሆናቸውም በላይ ወደፊትም ይህን የተቀደሰ ተግባሩን አጠናክሮ በመግፋት ከጎናችን ሊቆም ይገባዋል ሲሉ እነዚህ የማህበረሰብ አባላት ለግንባሩ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርም በበኩሉ ከሕዝቡ የቀረበለትን ጥሪ በጸጋ ተቀብሎ ወደፊትም ተመሳሳይ የሆነ ወታደራዊ እርምጃዎችን ከመውሰድ እንደማይቆጠብ ግንባሩ ያለውን ወገናዊነት እየገለጸ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ በአካባቢው እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የኢሕአግ ሰራዊት እየታየ ያለው የሕዝብ መነሳሳት ስሜት በተደራጀ መልክ እንዲቀጥልና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ የመጣው ሕዝባዊ አመጽ ለፍሬ ይበቃ ዘንድ የግንባሩ ሰራዊት ተነስ! ታጠቅ! ዝመት! የሚለውን ወቅታዊ የትግል ጥሪ በራሪ ወረቀት በማይጸብሪ፣ በአድርቃይ እና በዛሪማ አካባቢዎች ላይ እያሰራጨ መሆኑ ታወቀ።
በመላ ሀገሪቱ ላይ እየተሰራጨ የሚገኘው የኢሕአግ የትግል ጥሪ በራሪ ወረቀት ዋና አላማ የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔ ላይ ያለው ጥላቻ ግልጽ ቢሆንም ሕዝብ እንደ ሕዝብ እጅ ለእጅ በመያያዝና በመደጋገፍ በወያኔ አፋኝና ቀፍዳጅ ስርዓት ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር መነሳት መታጠቅና መዝመት ብቸኛ መንገድ መሆኑን ግንባሩ ስላመነ ነው።
በዚህም መሰረት ሰሞኑን በዚሁ የዋልድባ ገዳም አካባቢዎች በተለይም በማይጸብሪ ፣በአድርቃይና ዛሪማ በተባሉ አካባቢዎች ይኽው የግንባሩ ወቅታዊ የሀገር አድን ጥሪ በራሪ ወረቀት እየተሰራጨ መሆኑን በአካባቢው የሚገኙ የግንባሩ የጦር አዛዥ ሰሞኑን ባደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚንቀሳቀሰው እና ሰሞኑን ወታደራዊ ጥቃት የፈጸመው የግንባሩ ሰራዊት አዛዥ በላከልን መረጃ ጨምሮ እንደገለጸው የወያኔ ቡድን ሰሞኑን የደረሰበትን ከፍተኛ ውርደትና ሽንፈት በሕዝብ ላይ ለመበቀል እንደተዘጋጀና ብዛት ያለው ሰራዊትም እያጓጓዘ መሆኑን ጠቅሶ ይህን ቅርስ አውዳሚና ሕዝብን ገዳይ የሆነውን ቅጥረኛ የወያኔን ሰራዊት የተለመደውን የሽንፈት እና የውርደት ካባ ለማልበስ የኢሕአግ ሰራዊትና ሕዝቡ ከመቸውም በላይ መደጋገፍ እንዳለባቸው ለመቀስቀስና ለማደራጀት ሲባል በራሪ ወረቀቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተበተነ መሆኑን የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ ያደረሰን መረጃ ጨምሮ ገልጿል።
የአድርቃይ፣ የማይጸብሪና የዛሪማ አካባቢ ነዋሪዎችም በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ለሕዝብና ለሀገር የቆመ መሆኑን ከመቸውም በላይ በተግባር ያረጋገጥንበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ካሉ በኋላ ወደፊትም ግንባሩ በወያኔ ጦር ላይ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች የተለመደውን ሕዝባዊ ድጋፍ ከማድረግ እንደማይቆጠቡና ውስጥ ለውስጥ ለመደራጀት በዚሁ የጥፋት ተልዕኮ በሆነው የወያኔ ጦር ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ከአካባው የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ አምባገነንና አናሳው የወያኔ ቡድን ከጀመረው ሰይጣናዊ አባዜ ካልተቆጠበና በእምነት አባቶችና ምዕመናን ኢትዮጵያዊያን ላይ የጀመረው የማዋከብና የእስር ዘመቻውን ካላቆመ ወደፊት የሚንቀሳቀሰው የሕዝብ አመጽና ተቃውሞ ከመቸውም ጊዜ የበለጠ መሆኑን ነዋሪዎች ከመግለጻቸው በላይ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወቅታዊ የትግል ጥሪ በራሪ ወረቀቶችን በመላው የጎንደር አካባቢዎች ለማዳረስ እነዚሁ የአድርቃይ፣ የማይጸብሪና የዛሪማ ወጣቶች በመረባረብ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
No comments:
Post a Comment