Please
find the links beneath for 47 pages SMNE’s report written in Amharic
entitled: “‘The New Tele’ (Ethio Telecom) and Information Network
Security Agency (INSA): TPLF/EPRDF’s Intelligence Network”. In Amharic
“አዲሱ ቴሌ” እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ)፡ የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ከሚያካሂዳቸው በርካታ ተግባራት በተጨማሪ ላለፉት ወራት የህወሃት/ኢህአዴግ
አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያካሄደውንና ሊያካሂድ ያሰበውን የስለላ ተግባር ሲመረምር ቆይቷል፡፡ በተለይም ዘመናዊ
ቴክኖሎጂን በመጠቀም አዲሱ ቴሌን (ኢትዮ ቴሌኮምን) ከዋንኛው የስለላ መ/ቤት ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት
አገልግሎት በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል NISS (National Intelligence and Security
Service) እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ወይም በእንግሊዝኛው (Information Network
Security Agency (INSA) - ኢንሳ ጋር በማጋባት ስለላውን በምን ዓይነት መልኩ ለማካሄድ እንዳሰበ
የሚያትት ባለ 47 ገጽ ግርድፍ ዘገባ አቅርበናል፡፡
“አዲሱ ቴሌ” እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ)፡ የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ በሚል ርዕስ የቀረበው
ይህ መረጃ በኢትዮጵያችን የተካሄደውንና በመካሄድ ላይ ያለውን የአፈና መዋቅር በጥቂቱ የሚያወሳ ነው። ዘገባው
የህወሃት/ኢህአዴግ የደኅንነትና የአፈና ተቋማት ከቴሌኮም አገልግሎት ጋር እንዴትና ለምን እንደተቆራኙ፣ የምዕራብ
አገራት የቴሌኮም ቴክኖሎጂ የተገፋበትን ምስጢር፣ አዲሱን ቴሌ ከአገር ወዳዶች በማጽዳት የህወሃት/ኢህአዴግን
ፖለቲካና ስውር አጀንዳ ማስፈጸም ይችላሉ ተብለው ለታመነባቸው ክፍሎች ወይም የአገዛዙ “ቁሶች” እንዲዛወር
የተደረገበትን ምክንያት፣ በፖለቲካ ድርጅቶችንና ኃላፊዎች እንዲሁም መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች (መያዶች) ላይ
የሚካሄደውን ስለላ በመጠኑ ለማሳየት ጥረት ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም ይህንን የስለላ መረብ በመጣስ ሕዝባችን ትግሉን በምን ዓይነት መልኩ ማከናወን እንዳለበትና እንዴት የመረጃ ጫካ ውስጥ በመግባት መደበቅ እንደሚቻል የተወሰኑ ሃሳቦችን ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡
No comments:
Post a Comment