Saturday, August 10, 2013

ሙስሊም ወገኖቻችን፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር በምናደርገው ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!! ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መግለጫ


ነሐሴ 3 2005 ዓ.ም.
በእስልምና እምነት እጅግ በደማቅ ሁኔታ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ የሆነው ኢድ አልፈጥር ለ1434ኛ ጊዜ ነሐሴ 2 ቀን 2005 ዓ. ም. በመላው ዓለም በደስታ ሲከበር ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ግን ለዚህ አልታደሉም። በእለቱ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የኢድ ሰላታቸውን ሰግደው ወደ የመኖሪያ ቤቶቻቸው ሲመለሱ ለድብደባ በሠለጠኑ የወያኔ ወታደሮች አሰቃቂ ሰቆቃ ተፈጽሞባቸዋል። በዚህ እለት በአዲስ አበባና እና ሌሎች ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች በርካታ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ አሁን ሕፃናት የወያኔ የጥይት ሰለባ ሆነዋል፤ ከዚያ እጅግ አሰቃቂ ግድያና ወከባ ያመለጡት ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአስር ሺዎች የሚገመቱ ሙስሊሞች በዓሉን ያሳለፉት በወያኔ ማጎሪያዎች ውስጥ በሕመምና በረሀብ እየተሰቃዩ ነው።
ይህ ለምን ሆነ?
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ጥንቃቄ የተሞላበት ተቃውሞ ሲያካሄዱ አንድ ዓመት አልፏቸዋል። እጅግ ጨዋ በሆነ መንገድ ላቀረቡት የመብት ጥያቄ በታላቁ በዓል ቀን ወያኔ የእንቢታ ምላሹን ወራዳ በሆነ መንገድ ሰጥቷል። ወያኔ ለሰላማዊ ተቃዉሞ ያለውን ንቀት እናቶችን፣ ሕፃናትንና አረጋዊያንን ጭምር በመደብደብ አሳይቶናል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሕይወታቸው ላለፈ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖቻችን ሕመም ይጋራል። በባለጌ የወያኔ ወታደሮች የተገደለየ፣ የተረገጡ፣ በቆመጥ የተደበደቡ፣ የተሰደቡ፣ የተተፋባቸው ወገኖቻችን ሁሉ ሕመማቸውን ችለው፤ እልሃቸውን ውጠው ለመረረ ትግል እንዲዘጋጁ ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የደረሰው በደል በሁላችን ላይ የደረሰ ጥቃት፣ በደል ነው። የሙስሊም ወገኖቻችን የመብት ጥያቄ የኢትዮጵያዊያን ተበዳዮች ሁሉ ጥያቄ ነው። እነዚህ ጥያቄዎች በወያኔ አገዛዝ ሥር ምላሽ አያገኙም። ስለሆነም ተባብረን ኢትዮጵያችንን ከወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝ ነፃ አውጥተን ሁላችንም የነፃነት አየር የምንተነፍስባት አገር እናድርጋት ዘንድ ዛሬውኑ የጋራ የትግል ጉዞ እንጀምር።
“ሙስሊም ወገኖቻችን ሆይ! እልሃችሁን ውጣችሁ፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር ለሚደረግ ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!” በማለት ግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ

ሰማያዊና አንድነት ፓርቲ የትላንትናውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ሲያወግዙ ሽመልስ ከማል ግን ተገቢ ነው አሉ


ሰማያዊና አንድነት ፓርቲ የትላንትናውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ሲያወግዙ ሽመልስ ከማል ግን ተገቢ ነው አሉ Shemeles Kemal says the attack on peaceful Ethiopian Muslims was appropriate, but Semyawi & UDJ parties denounce the use of force.

የፀረ ሽብር አዋጁ ካልተቀየረ ማንንም አይምርም”


የመንግስት ስልጣን ገደብ ቢኖረው ኖሮ ሚኒስትር ዲኤታው ፍ/ቤት ይቆሙ ነበር - ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ናፍቆት ዮሴፍ “ሰማያዊ ፓርቲ፣ ግንቦት ሰባት እና አክራሪዎች ጋብቻ ፈጽመዋል” በሚል የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ መናገራቸውን የተቃወሙት የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፤ “የፀረ ሽብር አዋጁ ካልተቀየረ ማንም አይምርም፣ የመንግስት ስልጣን ገደብ ቢኖረው ኖሮ ሚኒስትር ዴኤታው ፍ/ቤት መቆም ነበረባቸው” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በህዝብ ስም የተቋቋመ ስለሆነ የመንግስት ድክመቶችንና ክፍተቶችን እንዲያስተካክል መታገል ስራው ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ መንግስት የህዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ መፈረጅ ይቀናዋል፤ ይህ ግን ከትግላችን አያግደንም” ብለዋል፡፡

“ከሁለት ወር በፊት የህዝብ ችግሮችና ጥያቄዎች ናቸው ብለን በሰላማዊ ሰልፍ ያሰማናቸው ጥያቄዎች አልተመለሱም” ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሁለተኛውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ “ኢትዮጵያ ከአገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ ገና አልገባችም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ገና የስልጣን ባለቤት አልሆነም” ያሉት ኢንጂነሩ፤ እነዚህ ነገሮች እውን እንዲሆኑ በምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና አግኝቶ በሰላማዊ መንገድ የሚታገልን ፓርቲ ከአሸባሪዎች ጋር ጋብቻ ፈጽሟል በማለት መወንጀል የአገዛዝ ባህሪ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡ አሸባሪ የሚለው ቃል ትርጉሙን ስቷል የሚሉት ኢ/ር ዘለቀ፤ የፀረ ሽብር አዋጁ እስካልተቀየረ ድረስም ማንንም ከመፈረጅ የሚያግድ ነገር የለውም ብለዋል።

PM Hailemariam Dessalegn advised anti democratic movement advocates


ሐይለማሪያም ደሳለኝ እውነት በሰው ምስል አስመስለው ቻይናዎች ለወያኔ መጠቀሚያ እቃ እንዲሆን  የሰሩት ሰው መሰል ረቦት  በቀቀን ነው ።አንድም ቀን የራሱን ሐሳብና ስራ ሰርቶ የማያውቅ በግ ነው በጣም አሳፋሪና ወኔ የሌለው አሻንጉሌት ነው
ለማንኛውም እናተም ከፋና ጋር ደረገውን ቃለ ምልልስ ስሙትና ተነጋገሩበት  መልካም ሰንበት





እስክንድር

Friday, August 9, 2013

Two Ethiopian journalists held for a week without charge

Darsema Sori (left) and Khalid Mohammed have been detained without charge. (Bilal Communication)
Darsema Sori (left) and Khalid Mohammed have been detained without charge. (Bilal Communication)
Nairobi, August 9, 2013--The Committee to Protect Journalists is concerned about the arrest and week-long detention without charge of two journalists working for Radio Bilal, a station that has provided extensive coverage of ongoing anti-government protests staged by Ethiopian Muslims.
On August 2, security officials in the capital, Addis Ababa, arrested Darsema Sori outside his home and detained Khalid Mohammed as he headed to work, Radio Bilal Chairman Mohammed Hassen told CPJ. The journalists were taken to court the next day and remanded into custody while police continued their investigations, local journalists said. The next court hearing is expected to take place on August 14, Mohammed Hassen said.
Darsema, senior editor for the station, worked on two current affairs programs, "Life in Ethiopia" and "Let us Discuss." Khalid is the station's news editor.
Radio Bilal, an online radio station with offices in Washington, Johannesburg, and Addis Ababa, has provided extensive coverage of the affairs of Ethiopia's Muslim community, including an ongoing series of peaceful mass demonstrations against alleged government interference in religious affairs, according to CPJ research. Ethiopian authorities have sought to silence the protests by arresting protesters, community leaders, and independent reporters, and shutting down news outlets, according to international news reports and CPJ research.
Repeated calls to government spokesman Shemelis Kemal were left unanswered.
"The arrests of Darsema Sori and Khalid Mohammed appear to follow a pattern of Ethiopian authorities cracking down on independent journalists and news outlets involved in disseminating news about the Muslim protests taking place in the country," said CPJ East Africa Consultant Tom Rhodes. "Trying to silence independent views and accounts of this national issue will not solve the ongoing dispute and instead will further the sense that the government has something to hide."
Darsema was also a columnist for the now-defunct Ye Muslimach Guday (Muslim Affairs) magazine, local journalists told CPJ. Ye Muslimach Guday journalists, Chief Editor Yusuf Getachew has been imprisoned since February 2013, and Managing Editor Solomon Kebede since July 2012, both on vague anti-state and terrorism charges in retaliation for articles critical of government policy on religious affairs, according to CPJ research. The paper has not published since July last year and two of its editors, Senior Editor Akemel Negash and Copy Editor Isaac Eshetu, have fled into hiding, local journalists said.
  • For more data and analysis, visit CPJ's Ethiopia page.

AMHARIC NEWS August 8,2013 , WATCH THIS ETV LIAR

 



Ethiopian Muslims attacked by government forces during Eid al-Fitr celebrations in Addis Ababa








Ethiopian Muslims attacked by government forces during Eid al-Fitr celebrations in Addis Ababa


Ethiopian Muslim were attacked by Government forces during Eid al-Fitr celebrations in Addis Ababa. According to the video The Muslims were close to there house when there where attacked by the Government Forces. The attack was involved women alderman and kids too.