Tuesday, March 12, 2013

Members of Semayawi Party described the 'discrimination' as an Apartheid”-

ሃገራችን ኢትዮጵያ ከየት ወደየት እየተጓዘች ነው ?

Esconder  Asefa  12.03.2013 

እዮት ይህንን አሳፋሪና አሳዛኝ ትእይንት ወገኖቻችን በሃገራቸው ላይ በዲሞክራሲ መብታቸው ተጠቅመው የመናገርም ሆነ የመሰብሰብ  መብታቸውን ተጥሶ በሃገራቸው ላይ እንደ 7ተኛ ዜጋ ሲዋከቡና ሲራበሹ ማየት በጣም አሳፋሪ ነው ታዲያ ወገን ምን እስክንሆን ድረስ ነው የምንጠብቀው ? እኔ እንደማስበው አስር ድርጅት መስርቶ ሁልጊዜ መግለጫ ከማንበብ አንድ ሆኖ ዘር ፤ ሃይማኖት ፤ ብሄር ፤ ከመለየት በአንድነት ሆነን በአፓርታይድ አገዛዝ የተገዛውን ህዝባችንን እንድንደርስለት ያስፈልጋል ያለበለዚያ እንደ ቀበሌ እድር በየመንደሩ የእንትን ፓርቲ የእንትን ፓርቲ እያላቹ  የ3000አመት ባለታሪክ የሆነችውን ሃገራችን እንዳትፈራርስ እሰጋለሁ። ለዚህ ሁሉ በደል ተጠያቂ በስልጣን ላይ ያለው ዘረኛው መንግስት ብቻ አይደለም ምክንያቱም እንደ መልካም አስተዳደር  ከወያኔ መንግስት  ጋር በሰላማዊ ትግል ሃገራችንን ነጻ እናወጣለን ብለው ለእነሱ  መሳሪያ ሆነው ተቃዋሚ ድርጅቶች ነን እያሉ  በህዝብ ላይ የሚያሾፉትም ተጠያቂ  ናቸው። ወገን እንንቃ በተለይ በውጪ የምንኖረው ኢትዮጵያኖች እባካቹ  ባይሆን ድምጹ ለታፈነው ህዝባችን ድምጽ እንሁነው እኛ ተመችቶን እንደምንኖረው ሁሉ ወገኖቻችንም ይህንን ሰላም ይፈልጉታል የነሱ መሰቃየት ለኛም እንዲሰማን ያስፈልጋል ለወገን ደራሽ ወገን ነው ስለዚህ በአንድ መንፈስ በአንድ ሃይል መነሳት አለብን። 
ቸር ያሰማን  watch the video
ድል ለኢትዮጵያኖች 
ሞት ለከፋፋዮች
እስክንድር ከኖርዌይ 

h

Members of Semayawi Party/Blue Party had booked a dinner for last night at the Wabi Shebelle Hotel, Addis Abeba, to dine with Professor Mesfin and Dr. Yakob and have a round table talk about various issues. At the last minute, they were told “you can’t eat here”. One of those, who says had already paid 300 Et.B to eat his dinner, described the ‘discrimination’ as an “Apartheid”. Well, won’t complain here now myself, if find myself discriminated. Clip below shows some of the controversies…

Monday, March 11, 2013

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም በኖርዌይ


አንጋፋው የኢሳት ጋዚጠኛ ፋሲል የኔአለም በትናትናው እለት march 09,2013 በኖርዌይ ኦስሎ የስራ ጉብኝት ባደረገበት ጊዜ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የኢሳትን ደጋፊነታቸውንና አጋርነታቸውን ለመግለጽ በኢትዩጵያ ኮሚኒቲ ተሰባስበው የእራት ግብዣ አድርገውለታል።


በዝግጅቱ ላይ በኖርዌይ የሚኖሩ በርከት ያሉ ኢትዮጵያዊያኖች ከተለያዮ ስፍራ በመገኘት ስለ ኢሳት አመሰራረትና በሃገራችን ውስጥ ስላለው የስብአዊ መብት ጥሰት ከሐገር ቤት ከሚደርሳቸው ዘገባ በመነሳት ስላለው ሁኔታና እንዲሁም የተለያዮ እርእሶችን በማንሳት በስፋት ሲወያዮ አምሽተዋል ።

በመጀመሪያም በኖርዌይ የኢትይዮጵያ ኮሚኒቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ቢትወደድ ጸጋዬ የእንኳን ደህና መጣህ ንግግርና በፌብርዋሪ10.2013 በተሳካ ሁኔታ ለተጠናቀቀው የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ በማውሳት ኢሳት ለኢትዮጵያኖች አይንና ጆሮ እንደሆነና መደገፍ የሚገባው ድርጅት እንደሆነ የሚገልጽ የድጋፍ ንግግር አድርገው የኖርዌይ ኢትዮጵያኖች ለኢሳት ያላቸውን ድጋፍና በአንድ እግሩ ለማቆም ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች ጋር ተባብሮ ለመስራት ያላቸውን አጋርነት በመግለጽ በህዝቡ ስም ዝግጅቱን ከፍተዋል።

ጋዜጠኛ ፋሲልም ከተለያዮ ታዳሚዎች የቀረቡለትን ጥያቄዎችንም በተገቢው ሁኔታ በስፋት በማብራራት ለታዳሚዎቹ ሲገልጽ አምሽቷል በተለይ ሃገር ቤት ሆነው ስልክ የሚደውልሏቸውን ወጣቶች ያላቸውን የፖለቲካ ብቃትና በእድሜአቸውም ማነስ እያነጻጽረ ምን ያህል ወጣቱ በፖለቲካ ብቃት መጎልበቱን በማድነቅ ለታዳሚዎቹ ሲያጫውታቸው አምሽቷል።

በመጨረሻም ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ታዳሚዎችን በእርሱና በኢሳት የስራ ባልደረቦቹ ስም አመስግኖ ወደ ተዘጋጀለት ማረፌያ በክብር ተሸኝቷል። ከዛም በጠዋት ወደ ሚኖርበት ሆላንድ አምስተርዳም ከተማ አቅንቷል።


ጋዚጠኛ ፋሲል የኔአለም በኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ እንደ ተላለፈበት ይታወሳል

http://www.rnw.nl/africa/article/exiled-ethiopian-journalist-convicted-terrorism



እስክንድር አሰፋ ከኖርዌይ

ማርች 10.2013

 

Saturday, March 9, 2013

አለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ 2013 በኦስሎ ኖርዌይ ንግስት ሶኒያ በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ተከብሮ ዋለ


በኦስሎfolketeateret በተባለው አዳራሽ በኖርዌጅያን የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 12.00 በዓሉ የተጀመረ ሲሆን በዓሉንም አስመልክቶ የኖርዌይ ንግስት የሆኑት ሶንያ ሃራልሰን የእንኳን አደረሳችሁ የደስታ መግለጫ በማስተላለፍ በአሉን የከፈቱ ሲሆን በመቀጠልም የተለያዩ የሴቶች ማህበራትን ወክለው የመጡ እንግዶች እንዲሁም ትውልደ ፓኪስታኒ የሆነችው  የባህል ሚንስትርዋ ሃዲያ ታጂክ ጨምሮ በየተድርጅታቸውን በማስተዋወቅ ንግግር አድርገዋል።

 በየመሃሉም አስተማሪና አዝናኝ የሆኑ የሙዚቃና የዳንስ ዝግጅቶች ተካሂደዋል። በመጨረሻም የምሳ ግብዣ ተደርጎ የጠዋቱ ፕሮግራም በ14፡00 ሰዓት የተጠናቀቀ ሲሆን።

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሴቶች ክፍልም በበአሉ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በአዳራሹ ውስጥ ለታደመው ታዳሚ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሴቶች የሰብአዊ መብት እረገጣና ጭቆናን የሚገልጹ የተለያዩ በራሪ ወረቀቶችን በመበተንና መፈክሮችን በመያዝ በሀገራችን ውስጥ ባለው የመንግስት ብልሹ አስተዳደር ምክንያት ሴቶች ለከፍተኛ ችግር እየተዳረጉ መሆኑንም አሳይተዋል።

በተጨማሪም ምሽት 18፡00 ላይ በነበረው የሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቀደም ብሎ በመገኘት የሻማ ማብራት ስነስርዓት የተደረገ ሲሆን በስነስርዓቱም ላይ በድርጅቱ የሴቶች ክፍል ሊቀመንበር ወ/ዘሮ ገነት የእንኳን አደረሳችሁ የመክፈቻ ንግግር ካሰሙ በኋላ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ ዳዊት መኮንን አጭር ንግግር አድርገዋል።

በመቀጠልም በወ/ሪት ሔለን ንጉሴ በዓሉን አስመልክቶ አለም አቀፍ ይዘቱንና ጠቀሜታውን በመግለጽ እንዲሁም በአገራችን በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ከፍተኛ ችግር አንስተው ይህንን ችግር ለመፍታት በሀገራችን ውስጥ ያለውን ብልሹ አስተዳደር በማስወገድ ለዲሞክራሲና ለፍትህ እንዲሁም ለሴቶች እኩልነት ከሚታገሉ ድርጅቶች ጋር በመወገን መታገል እንዳለብን የገለፁ ሲሆን ወ/ሮ ሥርጉት ሰው መሳይ አራዊት የተሰኘ ሴቶች እህቶቻችን በአረብ ሀገር የሚደርስባቸውን ግፍ የሚገልጽ ግጥም አቅርብዋል።
በአጠቃላይ ፕሮግራሙ በተሳካ ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑን በመግለጽ በፕሮግራሙ ላይ ከጎናችን ተገኝተው                                       ድጋፋቸውን ለሰጡን ወንድሞቻችን ሁሉ ምስጋና አቀርባለሁ።           


ድል ለኢትዩጵያ ሴቶች
 ብርሃን ለኢትዮጵያ

መሰደድ ይብቃ                                                                    

                                                                                   ሄለን ንጉሴ ከኖርዌይ
                                                                                     
                                                                                     ማርች 8 2013                   

Tuesday, March 5, 2013

በውጪ አገር ያሉትን አባቶች ያጋልጣል የተባለ ትንሽ መጽሐፍ ተሰራጨ


  • ቤተ ክህነቱ ይህንን ያደረገው ዕርቁ የፈረሰው በውጪዎቹ ችግር መሆኑን ለማጠየቅ ነው፤
  • የደጀ ሰላም ምንጮች “ቤተ ክህነታዊ ሐረካት” ብለውታል። 

(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 26/2005 ዓ.ም፤ ማርች 5/2013/ PDF)፦ በስደት የሚገኙነትን አራተኛው ፓትርያርክ ጨምሮ በውጪ አገር ያሉ አባቶችን ስሕተት፣ ጥፋትና ዕርቀ ሰላሙን ማፍረስ የሚያትት እንዲሁም ፓትርያርኩ ከሥልጣን የወረዱት ተገደው ሳይሆን በራሳቸው ፈቃድ መሆኑን የሚያትት ባለ 52 ገጽ አነስተኛ መጽሐፍ ታትሞ በመሰራጨት ላይ ነው።


ይኸው በአቡነ ማቲያስ ዕለተ ሲመት ጀምሮ መሰራጨት የጀመረው መጽሐፍ በብዙዎች አባባል የቤተ ክህነቱ “ጂሐዳዊ ሐረካት” የተሰኘ ሲሆን አዲስ ተሿሚው ፓትርያርክ ይቀጥላል ሲሉ ተስፋ ከሰጡት የዕርቅ ሒደት ተቃራኒ ሆኖ ተገኝቷል። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም “ዶኩመንታሪ” ፊልም እንዲሰራበት ኮሚሽን ተከፍሎበታል በሚባለው በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዕርቁን በጉጉት ይጠብቅ የነበረውን ምእመን ለማሳመን ረብጣ ብር እየፈሰሰ ነው።  

ይህንን አጭር መጽሐፍ/ ዶኩመንት ለመመልከት ይህንን ይጫኑ።

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

Monday, March 4, 2013

የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል


 (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

“አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” እነ ስብሃት
“የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን” እነ አባይና አዜብ

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።
በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን « የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።
የሕወሐት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ፥ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ሕወሐት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
በተያያዘም « ጉባኤ ይጠራ» በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።
የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን…በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።

ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ



የአሜሪካዊው አስከሬንና አሟሟት ሊመረመር ነው

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (http://www.goolgule.com/)
የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ከበባ ከገደላቸው ንጹሃን ዜጎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የአቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን አደባባይ በማውጣት ለህዝብ እያሳዩ ደስታቸውን ሲገልጹ የተመለከቱ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ክፉኛ መበሳጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጋምቤላ የደረቁን ወቅት ወይም በጋውን በወንዞች ዳር ውሃ ተንተርሶ መኖር የተለመደ ነው። ከቋሚ የመኖሪያ ቀዬ ወደ ወንዝ ዳርቻ በመሄድ አድኖ መመገብና አሳ አስግሮ ዕለትን ማሳለፍ የባህል ያህል ነው። በአገሬው ልምድ መሰረት ከቋሚ መኖሪያቸው ወደ ውሃ ዳር የሚሄዱት ወንዶች ሲሆኑ ጉዞውም የሚደረገው በቡድን ነው።Gambella
በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን ያመራሉ። በቡድን ወደ አብሌን ያመሩት ሰዎች ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባቸው። ተኩስ ተከፈተ። ለጊዜው ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉ እንዳሉ ለተጎጂዎቹ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ።
ሰዎቹ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አብሌን ተቀምጠው ኑሯቸውን እየገፉ ሳለ በድንገት የተከበቡት በጥቆማ እንደሆነ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። “አቶ ኡሞት ኡዶል እና ሌሎች መሳሪያ የታጠቁ አብሌን ታይተዋል” የሚል ጥቆማ የደረሰው ኢህአዴግ፤ ሰራዊቱን ሰዎቹ በቋሚነት ወደሚኖሩበት ጎክዲፓች በመላክ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ፣ በማሰርና፣ በመግረፍ ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ እንዲያሳዩ አስገደዱ።
አቶ ኡሞት በዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ የነበሩ ሲሆን የአሜሪካ ዜግነትም አላቸው። ኢህአዴግ ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ በክልሉ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ አጥብቀው በግልጽ የሚቃወሙ ሰው መሆናቸውን የሚያውቋቸው ይናገራሉ። አቶ ኡሞት ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ ህዝብን የሚያስተባብሩና ለዓመጽ የሚያነሳሱ ናቸው በሚል ኢህአዴግ ቢወነጅላቸውም ውንጀላውን በማስረጃ ማቅረብ እንደማይችል እነዚሁ ክፍሎች ይገልጻሉ። ስለተፈጸመው ግፍ የተሞላበት ግድያና ከግድያው በኋላ ስለተከናወነው “አረመኔያዊ የእንስሳ ተግባር” ሲያስረዱ በቁጣ ነው።
በተጠቀሰው ቀን ቤተሰቦቻቸውን ቀበሌያቸው ድረስ በመሄድ በመግረፍና በማስፈራራት ወደ አብሌን ለከበባ በጠቋሚ የመጡት የመከላከያ አባላት ሰዎቹን እንደተመለከቱ ተኩስ ከፈቱ። በድንገት የተከበቡትና ዛፍ ሥር ተቀምጠው የነበሩት አንዳችም ጥያቄ ሳይቀርብላቸው በጥይት የተደበደቡት ሰዎች የአልሞት ባይ ተጋዳይ ትግል ቢያደርጉም አልሆነም። ተደራጅቶ በሶስት የወታደር ካሚዮን ከባድ መሳሪያ ታጥቆ የመጣው ሰራዊት ጨፈጨፋቸው። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንደተናገሩት ወዲያው ህይወታቸው ካለፈው ስድስት ንጹሃን መካከል አቶ ኡሞት መሞታቸው ሲታወቅ የሰራዊቱ አባላት አውካኩ፤ በደስታ ጨፈሩ። አስከሬኑንን ጭነው ፉኙዶ ወደሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ በመሄድ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ደስታቸውን አበሰሩ።
አስከሬን በመኪና በመጫን ከተማ እየዞሩ ደስታቸውን ገለጹ። በማግስቱ በጋምቤላ ከተማ ስታዲየም አስከሬኑን ህዝብ እንዲመለከተው ታዘዘ። ህዝብ ስታዲየም ተገኝቶ የአቶ ኡሞትን አስከሬን እንዲሳለም፣ ኢንቨስተሮችም ያለስጋት የመሬት ነጠቃቸውንና “ልማታቸውን እንዲቀጥሉ”፣ መሞታቸውን አይቶ ሕዝቡ እንዲያምንና ሞራሉ እንዲጎዳ የተላለፈው ውሳኔ ባልተጠበቀ ሁኔታ ተስተጓጎለ። ለጎልጉል መረጃውን ያስተላለፉ እንዳሉት አቶ ኡሞት አሜሪካዊ መሆናቸው ሲታወቅ ማዕከላዊ መንግስት ከአዲስ አበባ አስቸኳይ ትዕዛዝ አስተላለፈ። አስከሬኑን ባስቸኳይ እንዲቀብሩ መመሪያ ሰጡ። ሁሉም ነገር በመመሪያው መሰረት ተጠናቀቀ። የአቶ ኡሞት አስከሬን ባልታወቀ ቦታ ተቀበረ። አስከሬኑንን ለማየት በግዳጅ ተሰባሰበው ህዝብም ምንም ነገር ሳይመለከት ወደ ቤቱ ተመለሰ። ሁኔታውን ተከትሎ በተፈጠረ አለመረጋጋት የኢህአዴግ ሠራዊት በጎክ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የጋምቤላ ተወላጆች በተለይም ወንዶችን እያሠሩና እያሰቃዩ እንደሆነ ከሥፍራው የደረሰን ዜና ያረጋግጣል፡፡
የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት ጉዳዩን ለአሜሪካ መንግስት እንዳሳወቀና የአሜሪካ መንግስት ጉዳዩን ከስር መሰረቱ ጀምሮ እንደሚመረምረውና እስከ መጨረሻው የመንግሥት አካል እንደሚደርሱ ማረጋገጡ ታውቋል። ኢህአዴግ አቶ ኡሞትን የገደለበትን ምክንያት በማስረጃ ማቅረብ እንደሚጠበቅበትም አስታውቀዋል። አቶ ኡሞት የሚጠረጠሩበት ድርጊት እንኳን ቢኖር በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ መጠየቅ እየተቻለ እንዲገደሉ መደረጋቸው ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ የሚከራከሩላቸውና ጉዳያቸውን ይፋ ያደረጉት ክፍሎች ይናገራሉ።
በወቅቱ ህይወታቸው ያለፈው ንጹሃንና የደረሱበት ያልታወቀው ሰዎች ስም ዝርዝር ከስፍራው የደረሰን ሲሆን እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
  1. ጎጎ ኦቻላ
  2. ቻም ኦቻላ
  3. ዑከች አቻው
  4. አኳይ ኦሞት
  5. ኦሞት ኦባንግ
  6. አጂባ አኳይ
  7. ኦሞት ኡጁሉ ኦጎታ
  8. አንበሳው ኡጁሉ
  9. ቱወል ኦሎክ
  10. ኦችዋል ኦባንግ
  11. ኦዋር ቻም
  12. ኒሙሉ አጎሌ
  13. አብራች ኒሙሉ
  14. አኩኔ ኦሞት
  15. አግዋ ቻም
  16. ኦዋር ኒግዎ አጋክ
  17. ኦሞት ኡዶል (አሜሪካዊው)

Twenty Oromo people dead in outburst of ethnic violence in Manasibu and Odaa



At least 20 people died this weekend in an outburst of violent ethnic clashes on the border of the Benishangul region and the region of Wallagaa, Oromia, in West of Ethiopia: armed militia of the Gumuz ethnic group have been attacking and killing unarmed Oromo civilians. Although the Ethiopian government has deployed its police forces, they remain witness to the raging killings, instead of stopping the killers.

The ongoing armed attacks started last Monday night in the Manasibu district, according to different independent sources in the field. Conflicts have been reported in Odaa, Daleti, Fadun Fardosi, Gunfi, and Badessa, forcing thousands of Oromo families to flee their homes.
Almost five years ago, in May 2008, another outburst of ethnic violence claimed the lives of more than 400 Oromo people. The Gumuz militia attack on the unarmed civilian Oromos caused the death of hundreds and many more injuries and displacement of hundreds to people, and destruction of houses and properties. Hundreds of Oromos were subjected to horrific and barbaric killings. The militia is said to be so heavily armed that the local police themselves had to flee along with the civilians. The relevant government body and armed forces were bystanders watching the massacre of the unarmed and defenseless Oromos.

The Oromo and Gumuz peoples have lived together as good neighbours for centuries. They are culturally intermingled and share valuable social, political and economic set-ups. But ever since it came to power, the TPLF/EPRDF regime has applied the outdated ‘divide and rule’ policy to weaken peoples’ struggles for freedom and justice by sowing seeds of disharmony among friendly neighbouring peoples
The TPLF regime’s track record of the past 22 years of rule is full of such intrigues that instigated bloody conflicts among peoples in Ethiopia . As a result of TPLF’s machinations Oromo and Sidama, Oromo and Somali, Oromo and Gedao, Anywak and Nuer, Oromo and Amhara, Oromo and Oromo, now Oromo and Gumuz and several other people have clashed. As a result thousands of innocent lives were lost, tens of thousands of people were displaced and their houses and properties were destroyed in the past 22 years..