እስክንድር አሰፋ
ከኖርዌ
ከኖርዌ
ሠላም የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበር በኖርዌይ ቅዳሜ ሰኔ(juni)22,2013 ባደረገው የባህል ምሽት በኖርዌ ኦስሎ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖችን ያሳተፈ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ግጥሞች፤ጥያቄና
መልስ፤ ሙዚቃ፤ አዝናኝ ቀልዶችና አስተማሪ ዝግጅቶች በተለያዩ እህቶችና ወንድሞች የቀረበ ሲሆን አቶ ዳምጠው አየለ በሚደነቀው ድምጸ መረዋ ዝግጅቱን
ሲያደምቅ ወንድማችን እንዳለ ጌታነህ ደግሞ በዛ ተአምረኛው ጣቶቹና ድምጹ ክራር በመጫወትና በማንጎራጎር እንዲሁም የዝግጅቱ መሪ ፍቅሬ የተደበቀውን
ታለንቱን በመጠቀም ፕሮግራሙን በመምራት የተሳካ ምሽት እንዲሆን አድርገውታ።
በዝግጅቱም ላይ የተለያየ የሐገር ባህል ምግብና መጠጥ የቀረበ ሲሆን ዝግጅቱ ከመጀመሩ በፊት በቅርቡ ህይወታቸው በሰው እጅ በማለፉ ያጣናቸውን የእህቶቻችንን መሪር ሃዘን በማሰብ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት የተደረገ ሲሆን ችግሩንም ለመፍታት እንዴት አድርገንና በምን መልኩ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እንስጥ በሚለው አነጋጋሪ ሁኔታ ላይ መክረው ቀጣይ የሆኑ ፕሮግራሞችን በመቀየስ ችግሮች በጋራ እንዲፈቱ ለማድረግ እቅድ አውጥተው ዝግጅቱን በኖርዌ ሰአት አቆጣጠር 17፡30 ተጀምሮ በ22፡00 ሰአት አጠናቀዋል።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
ቸር ያሰማን
watch this video part one
part two
No comments:
Post a Comment