Wednesday, June 5, 2013

ዘረኛው የወያኔ ስርአትን በህዝብ ሰላማዊ አመፅ እንዴት መገርሰስ ይቻላል?


የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ ሰላማዊ አመፅን በተመለከተ በአለም አቀፍ ደረጃ ከታወቁ የሰላማዊ አመፅ ማሰልጠኛ ኮሌጆችና ተቋማት ጋር በመተባበር የስልጠና ፕሮግራሞችን ነድፎ ለአባላቶቹ የተሳካ ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል:: ንቅናቄው የተሳካ የህዝብ ሰላማዊ አመፅ በአባላቶቹ ተሳትፎ ብቻ የሚከናወን ሳይሆን የሁሉንም ህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያካተተ መሆን እንዳላበት ጠንቅቆ ያውቃል:: ይህ ታላቅ ሰላማዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ስኬታማ እንዲሆን ህዝቡ የሰላማዊ አመፅን ፅንሰ ሃሳብን በሚገባ መረዳትና ተግባራዊነቱም እንዴት መሆን እንዳለበት እንዲሁም የሚወሰዱ ጥንቃቄዎችን በሚገባ ማወቅና መለየት ይኖርበታል:: ስለሆነም ንቅናቄው ነፃ የሰላማዊ አመፅ አጫጭር የስልጠና ፕሮግራሞችን አዘጋጅቶ እያካሄደ ይገኛል::

ስልጠናውን እንዴት መቀላቀል ይቻላል? ስልጠናውን ለመከታተል 3 መሰረታዊ ቅድመሁኔታዎችን ማሟላት ያስፈልጋል::

1. ከሚቀርቧቸውና ከሚያምኗቸው የቅርብ ወዳጆችዎና ጓደኞችዎ ጋር በመሆን : ቢያንስ አስር አባላትን ያካተተ የራስዎን ቡድን ያቋቁሙ::
2. ሰላማዊ አመፅን መሰረት በማድረግ ከአባላትዎ ጋር ጠለቅ ያለ ውይይት በማካሄድ የቡድንዎን አላማ: ራእይ : እንዲሁም ተግባራትን በመወሰን ዝርዝር መመሪያዎችን ይንደፉ::
3. ከላይ የተዘረዘሩትን 2 ጉዳዮች ከፈፀሙ በኋላ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄን በድህረገጽ በፌስቡክ በኢሜልና በስልክ አድራሻዎቻችን ያግኙ::

ከተዘጋጁት የስልጠና ፕሮግራሞች መካከል:

1.መሰረታዊ የሰላማዊ አመፅ ፅንሰ ሃሳብና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታው
2. የሰላማዊ አመፅ ስኬታማነት በኢትዮጵያና መሰናክሎቹን እንዴት ማጥበብ ይቻላል
3. የሰላማዊ አመፅ ስትራቴጂ ታክቲክና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች
4. በህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የተሳታፊውን ደህንነት ለመጠበቅ ከመቀላቀል በፊት ሊደረጉ የሚገቡ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችና ዝግጅቶች
5. በህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የሰልፉን ሰላማዊነት ጠብቆ እስከመጨረሻው ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ስነልቦናዊና ስልታዊ እውቀቶችን ማወቅና መለየት
6. በህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የሚከሰቱ ማንኛውም ክስተቶችን ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ በሰአቱ ለማሳወቅ የሚቀርፁ እንዲሁም በቀጥታ በተለያዩ የሚዲያ ድህረገፆች ላይ የሚያስተላልፉ መሳሪያዎች አጠቃቀምና የቀረፃ ቴክኒኮች

እንዲሁም:-

1. መሰረታዊ የኢንተርኔትና የፌስቡክ አጠቃቀም
2. ከወያኔ የኦንላየን ሃከሮችና ስፓዮች እራስን እንዴት መከላከል ይቻላል
3. በፌስቡክና በኢሜል የሚደረጉ ሚስጥራዊ የመልክት ልውውጦች

No comments:

Post a Comment