Wednesday, June 26, 2013

በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው


June 26, 2013


ከኢየሩሳሌም አርአያ
Bereket Simon is the Ethiopian Communications Ministerበዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርንት ከሚመራው ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምኦን የሚመሩት የመንግስት አካል በምስጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ። በቅርቡ በአንድ ድረገፅ ላይ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው በአገር ውስጥ እየተንቀሳቅሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ « ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤ ከግንቦት ሰባት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል» በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የፓርቲውን አመራሮች «ከሽብረተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት» ብለው ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን አስውታውቀዋል። የፓርቲው አመራሮችን ከማሰር ባለፈ «ሰማያዊ ፓርቲ በሽብርተኛ ድርጅት የሚረዳ ነው» በሚል በአገር ውስጥ የሚኖረውን የፓርቲው ቀጣይ ህልውና ለማክሰም ጭምር እየዶለቱ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ከበረከት በተጨማሪ ደብረፂዮን ይህንን ሴራ በበላይነት እየመከሩበት እንደሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ለሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ ከገዢው ባለስልጣናት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደተላከለት የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። መጀመሪያ 250.000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ፣ በማስከተል 50.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሃዋላ እንደተደረገለትና ባጠቃላይ 300.000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በዶላር ተመንዝሮ በእጁ እንደደረሰው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ገንዘቡ ከነበረከት በኩል በምስጢር የተላከ መሆኑን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚሁ መሰረት ጋዜጠኛው ለሕወሐት/ኢህአዴግ ማገልገል መቀጠሉንና በተለይ አሁን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየተሸረበ ያለው ሴራ መነሻው ይህ ሰው እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል።

“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል”

ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት


ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡



DSCN0929
ፍኖተ ነፃነት፡- ማን ነበር ያሰረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በማለዳ ቤቴ ተንኳኳ፤ ተነስቼ ከፈትኩኝ፡፡ የማላውቃቸው ሰዎች ናቸው፡፡ “ና ውጣ፤ ልብስህን ለብሰህ ውጣ” አሉኝ፡፡ እኔ እናቴ ሞታ ሊያረዱኝ የመጡ መስሎኝ “ምነው ቤተሰብ ደህና አደለም? የተፈጠረ ችግር አለ?” አልኳቸው “ዝም ብለህ ናውጣ” አሉኝ፡፡ ልብሴን ለበስኩኝና ወጣሁ፤ አንቀው መኪና ውስጥ ከተው ወደ ማዕከላዊ ወሰዱኝና 3 ወር አሰሩኝ ከዛም አንድ አመት ከ8 ወር እዋይ ማረሚያ ቤት፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- መታሰርህን ለቤተሰብ ተናግረሀል?
ወጣት ተስፋዬ:- ለማንም ሰው እንድናገር አልፈቀዱልኝም፤መስሪያ ቤቴ አልጠየቀኝም፣ ደሃዋ እናቴ ያለችው ናዝሬት ነው እሷም የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡ አባቴ አቶ ተካልኝ አስተማሪ ነበር አርባ ጉጉ ላይ ነው በ1985 ዓ.ም በነበረው ግጭት ነው የተገደለው፡፡ ማንም ሳይጠይቀኝ፣ፍ/ቤት ሳልቀርብ 23 ወር ታሰርኩ ልብስ ምግብም የሚያመጣልኝ ሰው አልነበረም፡፡ እናቴም መታሰሬን እንኩዋ አታውቅም መስሪያ ቤቴም ስኮላርሽፕ አግኝተዋል ወደ ውጪ ሃገር ሊማር ሊሄድ ነው የሚባል ነገር ስለነበረ አልጠየቁኝም፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የት ነበር ስኮላርሺፕ ያገኘኸው?
ወጣት ተስፋዬ:- የዛሬ 2 ዓመት አካባቢ የራስመስ ሙንደስን ስኮላር ሽፕ አግኝቼ ነበር፡፡ ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያና ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶክዮ ባሉ ምሁራን ሪኮመንድ ተደርጌ በጣሊያኑ ፌራሪ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ተዘጋጅቼ ነበር፡፡ እንደተፈታሁ ሄጄ ስጠይቃቸው ብዙዎቹ ጓደኞቼ በጣም ደነገጡ፡፡
በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ቅማል ተወርሬ…ባካችሁ ተውኝ… ምንም የሌለ ነገር የለም በጣም ተጎድቻለሁ፡፡ ከማረሚያ ቤት እንደወጣሁ እናቴ ጋ ስሄድ በጣም ደነገጠች፣በሕይወት ያለሁ አልመሰላትም 23 ወር ሙሉ ከቤተሰብ ስለተለየሁ ግራተጋባች ፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- በእስር ወቅት የደረሰብህ ድብደባና ማሰቃየት ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብኛል፡፡ በኤሌክትሪክ ጀርባዬ ላይ አቃጥለውኛል፣ በብልቴ ላይና በኩላሊቴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሱብኝ ሽንት ችዬ አልሸናም፣ ሽንቴን መቆጣጠርም አልችልም፡፡ ኩላሊቴንም በጣም ያመኛል፡፡ ውሃ ውስጥ እየነከሩ በጣም ደብድበውኛል፡፡ አሁን ስናገር ያመኛል ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደው ስታስበው ለእስር ያበቃህ ወይም ከመንግስት ጋር ያጋጨህ አጋጣሚ ነበር ?
DSCN0916
ወጣት ተስፋዬ:- መስሪያ ቤቴ ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ነበሩ፤ በጣም ይከታተሉኛል፡፡ በቢ.ፒ.አር ላይ ስብሰባ በተደጋጋሚ ይጠራ ነበር፡፡እኔም ሠራተኛ ላይ ተፅእኖ የሚያደርሱ ነገሮች ሲመጡ እኔ አልቀበልም በግልፅ እናገር ነበር ሠራተኛውም እኔን ይደግፋል፡፡ ከመታሰሬ ጠቂት ጊዜ በፊት ገነት ሆቴል ስብሰባ ነበረን፡፡ በዛ ስብሰባ ላይ በጣም ተከራከርኩ፤ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አቶ ፀጋዬ ማሞ የሚባሉ አሰልጣኝ፣ ከውጭ ጉዳይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና ከንግድና ኢንዱስትሪም የመጡ ነበሩ ስማቸውን የማላስታውሳቸው ባለስልጣን ነበሩ፤ እዛ ላይ ሀሳብ አንስቼ ተከራክሬ ነበር፡፡ “የሠራተኛን ሀሳብ ዳይቨርት ያደርጋል” ይሉኝ ነበር፡፡ መቼም ግን ሀሳቤን በመናገሬ ይህን የመሰለ ስቃይ ይደርስብኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ “አሸባሪ፣ ግንቦት ሰባት” እያሉ እኔ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ፍርድ ቤት ሳልቀርብ ያለምንም ፍርድ በርሜል ውስጥ ውሃ ጨምረው እያስተኙ አሰቃዩኝ፡፡

DSCN0917
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደዚህ ያሰቃዩህ ምን አይነት ምንም አይነት መረጃ ሳያገኙ ነው?
ወጣት ተስፋዬ:- እኔን ጥፋተኛ የሚያስደርግ ምንም መረጃ አላገኙም፣ እኔን አስረው ወደ መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ ይደውሉ እንደነበር ይነግሩኝ ነበር፡፡ የኢሜይል አድሬሴንም ተቀብለው በርብረዋል ግን ምንም አላገኙም፡፡ እኔ ከማንም ጋር ሊንክ የለኝም ኢሜሌ ላይ የስኮላር ሺፕ መልዕክት ካልሆነ በስተቀር ምንም የለውም፡፡ በመስሪያ ቤቴ ሪሰርቸር ነበርኩ፣ በሶሲዮሎጂ ነው የተመረኩት፡፡ ሉሲ የተገኘችበት ሣይት ላይ አፋር፣ ጋምቤላ ብዙ ሳይቶች ሰርቻለሁ፡፡ ከአለቆቼ ጋር ያለኝ ግንኙነት ሰላማዊ ነው እነሱ ናቸው ስኮላርሽፕ ሪኮመንድ ያደረጉኝ፡፡ አንደኛው ፕሮፌሰር 25 ዓመት ሙሉ እዚህ አገር ሰርቷል ፣ አርዲን ያገኘው እሱ ነው፡፡ ሄነሪ ጊልበርት ይባላል እሱም ሪኮመንድ አድርጎኛል፡፡ እኔ በጣም የሚቆጨኝ ደሃዋ እናቴ አረቄና ጠላ ሸጣ ነው ያስተማረችኝ ምን ብዬ ልንገራት እንደዚህ አትጠብቀኝም ከበደኝ፣አሁን እሷ የምትሰጠኝ ምግብ ራሱ ደምደም አለኝ….(ረጅም ለቅሶ)፡፡ ልጄ በደህናው አይደለም የጠፋው ሞቷል ወይም መኪና ገጭቶታል ብላ ነበር የምታስበው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የከመታሰርህ በፊት ፖለቲካ ተሳትፎ ነበረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- 1997 ዓ.ም የቅንጅት ደጋፊ ነበርኩ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ በ97 የነበረው ሁኔታ ስንት ሰው አለቀ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነበር ታውቃላችሁ ምንም የምናደርገው ነገር አልነበረም ፡፡ በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን መያዝ እንደማይቻል ተረዳሁኝ፡፡ ከ1997 ዓ.ም በኋላ የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አልሆንኩም፡፡

ከዚህ በኋላ ከምንም ነገር የተገለልኩ ሆኛለሁ፡፡ አንድ ብርጭቆ ሳትሰብር አሸባሪ ስትባል አስብ እንግዲህ አንድ ብርጭቆ እንኳን ሰብሬ አላውቅም ባለኝ እውቀት እንደውም ለእውቀት ነው የምጓጓው እውቀቴን አሳድጌ አገሬን ለመለወጥ ነው የማስበው እኔን ምንም የሚመለከተኝ ነገር የለም አሸባሪም ግንቦት ሰባትም አይደለሁም ፡፡ ስትደበደብ፣ስትሰቃይ ያላደረከውን አድርጌያለሁ ትላለህ በርሜል ውሃ ሞልተው ይከቱሃል ያሰቃዩሃል፡፡ አያሳዝንም ይሄ? እንዴት አድርጎ እዚህ አገር ይኖራል? 23 ወር ሙሉ አስረው ማሰቃየታቸው ሳያንስ የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል፡፡ እኔ ግን ከዚህ በላይ ሞት የለም ብዬ ነውየነገርኳችሁ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- አሁን የት ነው የምትኖረው?
ወጣት ተስፋዬ:- መኖሪያ የለኝም … (ረጅም ለቅሶ)

ወጣት ተስፋዬ ተካልኝን ለመርዳት የምትፈልጉ አንባብያን ከፍኖተ ነፃነት መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡




Monday, June 24, 2013

ሰላም የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበር በኖርዌይ ቅዳሜ june 22,2013 የስነ ጽሁፍ ባህል ምሽት

እስክንድር አሰፋ
ከኖርዌ
ሠላም የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበር በኖርዌይ ዳሜ ሰኔ(juni)22,2013 ባደረገው የባህል ምሽት በኖርዌ ኦስሎ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖችን ያሳተፈ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ግጥሞች፤ጥያቄና መልስ፤ ሙዚቃ፤ አዝናኝ ቀልዶችና አስተማሪ ዝግጅቶች በተለያዩ እህቶችና ወንድሞች የቀረበ ሲሆን አቶ ዳምጠው አየለ በሚደነቀው ድምጸ መረዋ ዝግጅቱን ሲያደምቅ ወንድማችን እንዳለ ጌታነህ ደግሞ በዛ ተአምረኛው ጣቶቹና ድምጹ ክራር በመጫወትና በማንጎራጎር እንዲሁም የዝግጅቱ መሪ ፍቅሬ የተደበቀውን ታለንቱን በመጠቀም ፕሮግራሙን በመምራት የተሳካ  ምሽት  እንዲሆን አድርገውታ።

በዝግጅቱም ላይ የተለያየ የሐገር ባህል  ምግብና መጠጥ የቀረበ ሲሆን ዝግጅቱ ከመጀመሩ በፊት በቅርቡ ህይወታቸው በሰው እጅ  በማለፉ ያጣናቸውን የእህቶቻችንን መሪር ሃዘን በማሰብ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት የተደረገ ሲሆን ችግሩንም ለመፍታት እንዴት አድርገንና በምን መልኩ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እንስጥ በሚለው አነጋጋሪ ሁኔታ ላይ መክረው ቀጣይ የሆኑ ፕሮግራሞችን በመቀየስ ችግሮች በጋራ እንዲፈቱ ለማድረግ እቅድ አውጥተው ዝግጅቱን በኖርዌ ሰአት አቆጣጠር 17፡30 ተጀምሮ በ22፡00 ሰአት አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም  ትኑር
    ቸር ያሰማን 
watch this video       part one
part two
                                                                                  
                                                                                      
                                                                             
                                                      





አንድነት የፀረ-ሽብር አዋጁን ለማሰረዝ የ1ሚ. ሰዎችን ፊርማ ያሰባስባል


አንድነት የፀረ-ሽብር አዋጁን ለማሰረዝ የ1ሚ. ሰዎችን ፊርማ ያሰባስባል
 ዶ/ር ነጋሶ የመጀመሪያው ፈራሚ ሆነዋል
“የአገሩን በሬ በአገሩ ሰርዶ እንጂ በውጭ ተቋማት መተማመንይቅር” - ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማሪያም
አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ከትላንት በስቲያ በይፋ የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ የፀረ-ሽብር አዋጁን ማሰረዝ ዋነኛ አላማው እንደሆነ ገለፀ፡፡ ለዚህ ዓላማውም የአንድ ሚሊዮን ሰዎችን የድጋፍ ፊርማ (ፒቲሽን) በዕለቱ ማስፈረም የጀመረ ሲሆን የመጀመሪያው ፈራሚ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሆነዋል፡፡ ፓርቲው የፀረ-ሽብር ህጉን ለማሰረዝ ከሚንቀሳቀስባቸው ምክንያቶች አንዱ ህገ-መንግስቱን በእጅጉ የሚጥስና የኢትዮጵያን ዜጐች በማጥቃት የሚጀምር በመሆኑ ነው ብሏል - የህዝባዊ ንቅናቄው ኮሚቴ በሠጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡

ፓርቲው “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል የጀመረው የሶስት ወር ንቅናቄ የአንድ ሚሊዮን ህዝቦችን ድምፅ በማሰባሠብ የአገሪቱን ዜጐችና ተቋማትን በማጥቃት፣ በሀይማኖት ጣልቃ በመግባት፣ ከአባትና እናት የተወረሠን ንብረትና ሀብት በሽብርተኝነት ስም የሚገፈውን አዋጅ ለማሰረዝ ጥረት እናደርጋለን፤ ወደ ክስም እንሄዳለን” ብሏል፡፡ “ይህ ማለት ግን ኢትዮጵያ ካላት ተፈጥሯዊ ሀብትና መሠል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የፀረ-ሽብር ህግ አያስፈልጋትም ማለት እንዳልሆነ የገለፁት የንቅናቄው ኮሚቴ አባል አቶ ትዕግስቱ አወል፤ አሁን ስራ ላይ ያለው የፀረ ሽብር አዋጅ ግን ሰዎችን እና ተቋማትን የሚያጠቃ ነው ብለዋል፡፡

ከተጠቁት ተቋማት ውስጥ አንድነትና መድረክ ዋነኞቹ እንደሆኑ፣ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ሰዎችም የዚሁ አዋጅ ሠለባ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ከህገ መንግስቱ ጋርም በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚቃረን ትኩረት አድርገንበታል ሲሉም አክለዋል፡፡ “ምንም እንኳን በፍትህ ተቋማቱ ላይ ያለን እምነት የተሸረሸረ ቢሆንም አሁንም መብታችንን ከመጠየቅ የሚያግደን የለም” ያሉት የንቅናቄው ኮሚቴ አባል አቶ ዳንኤል ተፈራ፤ መንግስት የ1 ሚሊዮን ሠው ድምፅና ጥያቄ አልቀበልም ካለ የፓርቲውን ሳይሆን የህዝቡን ጥያቄ አልመልስም እንደማለት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ፓርቲው በሶስት ወሩ ህዝባዊ ንቅናቄ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካተት ገልፆ፤ በዋናነት ህገ-መንግስቱን የሚፃረረውን የፀረ ሽብር አዋጅ ማሰረዝ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን በገጠርና በከተማ የዜጐች መፈናቀልና የመሬት ቅርምት ማስቆም፣ የስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት እንዲቀረፍ ማድረግ፣ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃ እንዲወሠድና የንግዱ ማህበረሠብ ከወንጀለኝነት ስምና ስግብግብ ከመባል ወጥቶ ጤናማ ውድድር እንዲኖር፣ እንዲሁም ማጥላላትና ማዋከብ እንዲቆም ማድረግ የሚሉት በዋናነት ተቀምጠዋል፡፡ የንቅናቄው ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ተክሌ በቀለ፤ ንቅናቄው አሁን የተጀመረበትን ምክንያት ሲያብራሩ፤ “እስከዛሬ ንቅናቄውን ያልጀመርነው ፓርቲው በአየር ላይ የተንጠለጠለ እንዳይሆን በእግሩ እንዲቆም በማድረግ ስራ ላይ እና በውስጥ አደረጃጀት ተጠምደን ስለነበር ነው” ብለዋል፡፡

“እስከዛሬ እግር ሲያወጡ እንቆርጣቸዋለን እየተባለን፣ እግር ስናወጣና ስንቆረጥ ቆይተናል” በማለት ያከሉት አቶ ተክሌ፤ አሁን ግን በኢህአዴግ የሚደርስብንን ብቻ ሳይሆን የውስጥ ህመማችንንም ስናክም ቆይተን ከጨረስን በኋላ በእውቀት ላይ የተመሠረተ የህዝብ ንቅናቄ ለመጀመር ጊዜው አሁን እንደሆነ ውሳኔ ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡ “በፍ/ቤቶች ላይ እምነታችን ቢሸረሸርም ፍትህ መጠየቃችንን አናቆምም” ያሉት አቶ ዳንኤል፤ የአንድ የሚሊዮኖችን ድምፅ የምናሠባስበውም ለዚሁ ነው ብለዋል፡፡

ዶ/ር ሀይሉ አርአያ በሠጡት አስተያየት አንድ አካል አጥፍቶ ያለመጠየቅን ነገር ፈረንጆቹ (Impunity) ይሉታል” ካሉ በኋላ “እዚህ አገርም አጥፍቶ የሚጠየቅ የለም፤ ስለዚህ በአገራችን ፍ/ቤት ካልተሳካ ወደ አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሚኬድበት አማራጭም መዘንጋት የለበትም” ብለዋል፡፡ ነጋዴዎችን በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ “የዚህን አገር ነጋዴዎች ለማወቅ የግድ የመጫኛ ነካሽ ልጅ መሆን አያስፈልግም” በማለት ምላሽ መስጠት የጀመሩት የንቅናቄው ኮሚቴ አባል አቶ አቶ ዳዊት ሰለሞን፤ በአሁኑ ሰዓት ነጋዴው ሌባ፣ ዘራፊ፣ ሙሰኛ እየተባለና እየተብጠለጠለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ “ገዢውን ፓርቲ የተጠጉ አካላት በአንድ ጀምበር የሀብት ማማ ላይ ሲወጡ፣ በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎች በስቃይ ላይ ናቸው ያሉት አቶ ዳዊት፤ የጥሬ እቃ እጥረትና መሠል ችግር ሲፈጠር መንግስት ጣቱን በነጋዴ ላይ እንደሚቀስር ጠቁመው፣ ነጋዴው በአገሩ አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር የሚደረግበት አካሄድ እንዲቆም እንጠይቃለን ብለዋል፡፡

Thursday, June 20, 2013

Monday, June 17, 2013

Questions to those who support the Woyanne Nile dam scam

Postby elias » 



Those Ethiopians who claim that they are supporting Woyanne Nile scam on national interest grounds have set aside the knowledge they have about Woyanne's over 20 years of lies, deceit, secret deals, the give away of Ethiopian land to Sudan and others, mass murders, and all of its anti-Ethiopia activities. I am encouraged that many patriotic Ethiopians are starting to raise questions, but to those who are still putting their trust on the anti-Ethiopia Woyanne to build a dam that will benefit Ethiopia, I have the following questions:

1. What do you know about the secret deals Woyanne signed with Sudan and others regarding Nile? For example, do you know that the dam will be only partially owned by Ethiopia, if at all?

2. Why is the dam being built right at the border with Sudan, in 'Benishangul-Gumuz region', a region that is carved out of Gojjam by Woyanne?

3. Why did Egypt keep quite for the past 2 years and just now has started to voice opposition? And why is Sudan, who historically opposed any dam on the Nile in Ethiopia, is fully supporting Woyanne's Nile scam now?

4. There are many rives in Ethiopia that are not being utilized for irrigation and hydroelectric power. Instead of spending billions of dollars on building a giant dam over Nile, why not utilize those rivers first?

5. What guarantee do you have that Woyanne doesn't invoke Article 39 of its constitution and make Benishangul-Gumuz an independent country to be exploited by "Greater Tigray", Sudan and others? Currently, Gambella and Benishangul are being emptied of their indigenous people and the land is being taken over by Woyanne and foreign investors, according to the Oakland Institute. How could any Ethiopian, who knows Woyanne's history of selling and harming Ethiopian interests and looting the country dry, trusts the same Woyanne to build a dam that benefits Ethiopia? Isn't this mind-boggling foolishness?

6. People from the Amhara ethnic group are particular targets of the Woyanne apartheid regime. Woyanne has been committing genocidal crimes against Ogaden and Gambella people. And while Oromo farmers are suffering, Woyanne is forcing them to sell their cattle and farm products below market prices for export to the Middle East. Most Ethiopians are second class citizens in their own country. Do you really believe that the same brutal regime that is tormenting the people of Ethiopia will build a dam that benefits them?

7. Some argue that the dam will stay after Woyanne is gone? Given the anti-Ethiopia nature of Woyanne and the polices it is currently implementing, how can you be sure that Ethiopia will continue to exist as a country after Woyanne is gone? Why don't we focus on getting rid of the anti-Ethiopia Woyanne junta, instead of giving it a boost to continue to brutalize and torment our people, and put Ethiopia's survival at risk?

I'd appreciate answers to the above questions by those non-Woyannes who are saying that they support the Nile scam.

የታሠርኩት ከሕግ ውጭ መኾኑን ተረድታችሁ በሁሉም መንገድ እንድፈታ ለወተወታችሁ፣የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡

http://ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Eskinder_Nega_3.jpg

ሰው ገብቶ እንዲጠይቀው ተፈቅዶለታል

‹‹ስላደረጋችኹልኝ እና ስለምታደርጉልኝ ኹሉ አመሰግናለሁ›› ብሏል


ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቃሊቲ የሚገኘው እስር ቤት ከገባ ከዐሥራ ስምንት ወራት በላይ አስቆጥሯል፡፡ ለዚህን ያህል ጊዜም ከባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ናፍቆት በስተቀር አንድም ሰው ገብቶ እንዲጠይቀው አልተፈቀደለትም ወይም በወዳጅ ዘመዶቹ የመጠየቅ መብቱ ተነፍጎ ነበር፡፡ ከቀናት በፊት ግን ይህ መብቱ ተከብሮለት ሰዎች ገብተው እንዲጠይቁት መፈቀዱን ሰማኹና ዛሬ ጠዋት እስክንድርን ለማየት ወደ ቃሊቲ አመራሁ፡፡ እስክንድርንም አገኘኹት ብዙም ተጨዋወትን፡፡ እስክንድር ለዚህን ያህል ወራት እስር ቤት መቆየቱን ተጠራጠርኩ ጥንካሬው አሁንም አብሮት አለ፡፡

ከእርሱ ይልቅ እርሱን ያሳሰበው በውጭ ያሉት ወዳጆቹ ጤንነት እስኪመስለኝ ድረስ በጋራ የምናውቃቸውን ሰዎች እና ጓደኞቻችንን ስም እያነሳ ጠየቀኝ፡፡በቻልኩት መጠን ሰላምታ እንዳቀርብለትም አሳሰበኝ፡፡ በመጨረሻም እንዲህ አለኝ፤‹‹የታሠርኩት ከሕግ ውጭ መኾኑን ተረድታችሁ በሁሉም መንገድ እንድፈታ ለወተወታችሁ፣ላሰሰባችሁ፣አሁንም እየወተወታችኹ ላላችኹና ባላችኹበት ላሰባችኹኝ ኹሉ ዲሞክራሲ በአገራችን ሰፍኖ ከእስር ወጥቼ በአካል ምስጋናዬን እስካቀርብላችሁ ድረስ ባላችሁበት የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ›› መልዕክቱን… እንደማስተላልለት ቃል ገብቼለት ተሰናብቼው ወጣሁ፡፡ በገባሁት ቃል መሠረትም ምስጋናውን አድርሻለኹ፡፡


እስክንድር ነጋ የሞያ አጋሬ ብቻ አይደለም፤በቀናነታቸው እና በአስተዋይነታቸው የመጀመሪያውን የወዳጅነት ቦታ ከምሰጣቸው ጓደኞቼ ውስጥ የምመድበው ሰው ነው፡፡ እስክንድር በአሳሪዎቹ እጅ ወድቆም ስለ ሌሎች ማሰብ ባለማቋረጡ እየተገረምኩ ቃሊቲን ለቅቄ ወጣሁ፡፡ ወዳጆቼ በዚህ ቤት መታሠር ሚያቆሙት መቼ ይኾን ስልም ራሴን ጠየኹ!

አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ የአሜሪካ ኮንግረስ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ የተለያዩ ተናጋሪዎችን ጋብዟል።

  post meles




ኢትዮጵያ ከመለስ ሞት በኋላ!!
አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ የአሜሪካ ኮንግረስ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ የተለያዩ ተናጋሪዎችን ጋብዟል። እኤአ ሰኔ 20፤2013 ቀን በሚካሄደው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ የሚሰማበት ውይይት ከኢትዮጵያ ሁለት ተናጋሪዎች ተጋብዘዋል።
ታዋቂው የመብት ተሟጋች፣ በከፍተኛ ደረጃ የኢትዮጵያዊያንን ድጋፍ እያገኙ ያሉትና   በውጭው ዓለም የዲፕሎማሲና የፖለቲካ መስመር ተሰሚነታቸው እያደገ የመጣው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ፣ እንዲሁም በበክኔል ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በዕለቱ ተናጋሪ መሆናቸውን ስብሰባውን ያዘጋጁት ክፍሎች ይፋ አድርገዋል።
ከሁለቱ ኢትዮጵያዊያን በተጨማሪ  ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ  ጸሐፊ ሆነው እየሰሩ ያሉት ዶናልድ ያማማቶ፣  የአሜሪካ የዓለምአቀፍ የልማት ተራድዖ የአፍሪካ ቢሮ ረዳት አስተዳዳሪ ኤሪል ጋስትና የማይክል አንሳሪ የአፍሪካ ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ፒተር ፓሃም ንግግር ያቀርባሉ። ምክከሩ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ሲሆን የውይይቱ ዋና ጉዳይ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና ከመለስ ሞት በበኋላ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝና የዲሞክራሲ አተገባበር ዙሪያ ጭብጥ የሚያዝበት ነው። (የጥሪው ደብዳቤ መሉ ቃል እንዲህ ይነበባል)
SUBCOMMITTEE HEARING NOTICE
COMMITTEE ON FOREIGN AFFAIRS
Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights, and International Organizations Christopher H. Smith (R-NJ), Chairman
TO: MEMBERS OF THE COMMITTEE ON FOREIGN AFFAIRS
You are respectfully requested to attend an OPEN hearing of the Committee on Foreign Affairs, to be held by the Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights, and International Organizations in Room 2172 of the
Rayburn House Office Building (and available live on the Committee website at www.foreignaffairs.house.gov):
DATE: Thursday, June 20, 2013
TIME: 10:00 a.m.
SUBJECT: Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights
WITNESSES: Panel I
The Honorable Donald Y. Yamamoto
Acting Assistant Secretary of State
Bureau of African Affairs
U.S. Department of State
The Honorable Earl W. Gast
Assistant Administrator
Bureau for Africa
U.S. Agency for International Development
Panel II
 Berhanu Nega, Ph.D.
Associate Professor of Economics
Bucknell University
 J. Peter Pham, Ph.D.
Director
Michael S. Ansari Africa Center
Atlantic Council
Mr. Obang Metho
Executive Director
Solidarity Movement for a New Ethiopia

Monday, June 10, 2013

Pro-OLF refugees in Cairo demonstrate against Ethiopia’s Renaissance Dam

Posted by on June 10, 2013

 
                                                                                                           Oromo refugees in Egypt
Awramba Times (Phoenix, Arizona) – Refugees from Ethiopia’s Oromo community protest outside the office of the United Nations High Commissioner for Refugees (UNHCR) in Cairo, Egypt against the construction of the Great Renaissance Dam.
Abdel-Kader Goumy, one of the protesters, told Al-Ahram’s Arabic language news website that the Renaissance Dam is intended to generate electricity, and, as such, there is no reason it should be built on the Nile, rather than on Ethiopia’s other rivers.
 
The tribe supports Egypt’s right not to be adversely affected [by the dam]… Addis Ababa is not in need of water, rather it aims to build the dam for political purposes,” he added.
Yehia Mohamed, another Ethiopian refugee belonging to the Oromo tribe, said, “Sunday’s protest comes after we have suffered harassment by some Egyptians due to the Ethiopian government’s decision to build the Renaissance Dam.” Mohamed also added that the Ethiopian government excludes the Oromo from all decision-making, including the decision to build the Renaissance Dam. Protesters lifted Egyptian and Ethiopian flags, declaring their refusal to support a dam that will “damage Egypt and will not help Ethiopia.”
 
Meanwhile, Sudan is warning of a possible water war between the Nile Basin countries because of Egypt’s ‘provocative’ stance.
Sudanese government spokesman Ahmed Bilal has asked Egypt to stop what he called provocations after an Egyptian opposition leader, Ayman Nour, publicly described the Sudanese stand on the Nile as disgusting.

The statement by Sudanese foreign ministry said Sudan would not be affected by the project, stressing that there were agreements and consultations between Sudan, Egypt and Ethiopia. “Sudan respects the agreements to cooperate with those two countries (Egypt and Ethiopia) in matters that concern sharing the waters of the Nile and sharing mutual revenues,” the ministry said.

The United States government has asked the three countries to resolve the problem amicably through political dialogue.

Saturday, June 8, 2013

Friday, June 7, 2013

Demonstration at Anwar Mesjid "Full Video" 07.06.2013 MUST WATCH



ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን አሰሙ

 ግንቦት 30 በአዲስ አበባና በበርካታ የክልል ከተሞች “የሀይል እርምጃ ለህዝብ መልስ አይሆንም” በሚል ርዕስ የተጠራው የሙስሊሞች ተቃውሞ በደማቅና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ታውቋል።

በአዲስ አበባና በበበርካታ የክልል ከተሞች ተቃውሞ ያሰሙት ሙስሊሞች ካስተጋቧቸው መፈክሮች መካከል፦” መብታችንን ለማስከበር የምናደርገው ትግል በሀይል እርምጃ አይጨናገፍም!፣ ለህዝብ የመብት ጥያቄ ሀይል መልስ አይሆንም! የታሰሩት መሪዎቻችን ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ይፈቱ! መንግስት ከሀይማኖታችን ላይ እጁን ያንሳልን! እና ፍትህ እንሻለን!”የሚሉት ይገኙበታል።


እንዲሁም በፍትህ እጦት የተማረሩት እነዚሁ ሰልፈኞች፦<<መንግስት የለም ወይ? መንግስት የለም ወይ? >>እያሉ በዜማ ተማጽኖአቸውን ሲያሰሙ ተደምጠዋል።
ድ ም ጻችን ይሰማ ለሰልፉ ጥሪ በባደገበት መግለጫው፦<<የትግላችንን ሂደት ለመግታት መንግስት ከውስጥም ከውጪም የተለያዩ ጥቃቶችን ሲሰነዝር ቀይታል፤ በጥቃቱ ሙስሊሞችን ከትግሉ ሜዳ ለማስወገድ ታስቦ የነበረ ቢሆንም መንግስት የሚያስበውን ያህል ሲሳካለት ግን አልታየም፡፡>>ብሏል።

<<ይህ የመንግስት ጥቃት ሌት ተቀን አከብረዋለሁ ብሎ የሚለፍፍለትን፣ በተግባር ግን ሊገዛለት የማይፈቅደውን ሕገ መንግስት በመጣስ በተደጋጋሚ የተፈጸመ >>ሲልም አክሏል -ድምፃችን ይሰማ ኮሚቴ።
በሌላ በኩል የመንግስት ባለስልጣናት ባለፈው ሳምንት ተጠርቶ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ – በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጲያዊያን ሙስሊሞች ከአንድ ዓመት በፊት ካነሱት ሃማኖታዊ ጥያቄ ጋር ለማያያዝ ሞክረዋል ያለው ኮሚቴው፤ይህም ለህዝብ ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ነው በሏል።

ዛሬ አዲስ አበባን ጨምሮ በ30 ከተሞች በተደረገው እጅግ ደማቅ ሰልፍ ሴት ሙስሊሞች ከወትሮው በተለየ መልኩ በዝተው መስተዋላቸው ተመልክቷል።
በተለይ በ አንዋር መስጊድ በተደረገው የተቃውሞ መርሀ-ግብር ሴት ሙስሊሞች በከፍተኛ እልህና ወኔ መሪዎቻቸው እንዲፈቱ በመጠየቅ ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ተስተውለዋል።

የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ሳቢያ “ የ አሸባሪነት ክስ ተመስርቶባቸው የታሰሩት የሙስሊም አመራሮች ያለ አንዳች ፍትሕ ወህኒ ከተወረወሩ 18 ወራት እንዳለፋቸው ይታወቃል።
ሙስሊሞች ዛሬ ባደረጉት ሰልፍ መሪዎቻቸው እስኪፈቱ እና ሀይማኖታዊ ጥያቄዎቻቸው እስኪመለሱ ድረስ የተቃውሞ መርሀግብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

Thursday, June 6, 2013

የተለያዩ የግል ተቋማት የህክምና ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማቸውን ቀጥለዋል


ግንቦት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከ14 የግል ኮሌጆች የተሰባሰቡ ከ5 ሺ በላይ የሚጠጉ የህክማን ተማሪዎች  ሰኔ 27፣ 2005 ዓም የጀመሩትን የትምህርት ማቆም አድማ የቀጠሉ ሲሆን መንግስት ለችግራቸው መፍትሄ የማይሰጥ ከሆነ በአድማው ለመግፋት መወሰናቸውን ተናግረዋል።
የትምህርት ሚ/ር ባለስልጣናት ተማሪዎቹ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውን ፣ የተማሪዎች ተወካይም እስከትናንት ድረስ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሲነጋገር ከቆየ በሁዋላ ተማሪዎች ሊያገኙት አለመቻሉን መዘገባችን ይታወሳል።
የተማሪዎች ተወካይ የሆነው ተማሪ እያሱ ኩሚሳ ትናንት ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሲደረግ የነበረው ውይይት ውጤት ለማስገኘት ባለመቻሉ ተማሪዎች በትምህርት ማቆም አድማው ለመግፋት መወሰናቸውን ዛሬ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር ባለስልጣናት  ችግሩን መንግስት እንደፈጠረው ቢያምኑም ለማስተካካል እንደማይችሉ ግን ገልጸውልናል አለው ተማሪ እያሱ፣ ተማሪዎቹ የፈለገው ቢመጣ አንማርም የሚል አቋም ሲይዙ፣ ባለስልጣናቱ” አንድን ግንብ ስታዩት የማይወድቅ መስሎ ከታያችሁ አትጋፈጡትም፣ ነገር ግን ሳስቶ የምታዩት ከሆነ ግን እንጥለዋለን ብላችሁ ለመግፋት ትሞክራላችሁ፤ የእናንተ ጉዳይም እንደዚሁ ነው አርፋችሁ ብትቀመጡ ይሻላችሁዋል ” የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ገልጿል።
መንግስት የክሊናካል ነርስ ተማሪዎችን በተመለከተ በድንገት ያወጣው አዲስ መመሪያ ተማሪዎችን ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርግ በመሆኑ ተማሪዎች እንደተቃወሙት መግለጻችን ይታወሳል። በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬም የመንግስት ባለስልጣናትን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

Wednesday, June 5, 2013

Voices in Danger: Jailed for 18 years for criticising Ethiopia's government, journalist Eskinder Nega vows to keep fighting

The Independent has seen a defiant letter smuggled out of jail by a man who pines for democracy

an Ethiopian journalist who was jailed after publishing a series of articles calling for democratic reforms has penned a letter from prison, seen exclusively by The Independent, in which he decries the “human rights crisis” unfolding in Ethiopia and describes the personal toll of facing 18 years behind bars.

The call to action: You can help Eskinder’s case. Please share these stories, his journalism, and his prison letter, as widely as you can through social media. Wherever you are in the world, please raise his case with your elected officials and governmental foreign ministers.



Eskinder Nega, 45, was sentenced last year under a broad 2009 anti-terrorism law which freedom of speech activists, the United Nations and various members of the US congress and European Parliament  say effectively ban independent journalism in Ethiopia.  At trial, Mr Nega admitted he had criticised the government, but said he had only ever called for peaceful steps towards democratic reforms.
A copy of Mr Nega’s letter, smuggled out of his cell in Addis Ababa’s notorious Kality Prison, was passed to The Independent for publication as part of its Voices in Danger campaign, which is aimed at publicising the plight of jailed, attacked or harassed reporters around the world.

Under the headline “I shall persevere!”, Mr Nega’s letter is a reaction to a ruling handed down by the Ethiopian Supreme Court on 3 May, which rejected his appeal and upheld his 18-year jail sentence. In it, Mr Nega vows to continue his fight for freedom of speech in Ethiopia.
“Individuals can be penalised, made to suffer (oh, how I miss my child) and even killed,” he writes. “But democracy is a destiny of humanity which cannot be averted. It can be delayed but not defeated.”
Mr Nega quotes widely from literary figures such as Keats and Horace in his assessment of Ethiopia’s government, citing Alexander Solzhenitsyn’s analysis of the Stalinist purges of the 1930s, which “tortured you not to force you to reveal a secret, but to collude with you in a fiction.” He writes: “This is also the basic rational of the unfolding human rights crisis in Ethiopia.”
Ethiopia is courted by western governments including Britain, partly because it is seen as a relatively stable nation in the Horn of Africa. But critics say that behind this reputation lies one of the continent’s most repressive regimes when it comes to free journalism.
At least 72 publications, including those for whom Mr Nega worked, have been forced to close under government pressure over the last two decades, according to the Committee to Protect Journalists.
Educated in the US, Mr Nega has been imprisoned nine times for his journalism. His wife, Serkalem Fasil, was also jailed at one stage for her activities as a newspaper publisher and even gave birth to their son in prison. She once described jail as “a home away from home” for her husband.
In his prison cell letter, he concludes: “I sleep in peace, even if only in the company of lice, behind bars,” he writes in his letter from jail. “The same could not be said of my incarcerators though they sleep in warm beds, next to their wives, in their homes.”
Mr Nega’s calls for freedom of speech echo those voiced on Sunday, when around 10,000 Ethiopians marched through the capital of Addis Ababa in the first large-scale anti-government protests since the disputed 2005 election which ended in street violence that killed 200 people.
After Mr Nega and his wife published columns criticising what they described as the government’s brutal crackdown on those2005  protests, they were both arrested and charged with treason. They were both  acquitted after 17 months in jail, where Serkalem gave birth to their son, Nafkot.
Speaking after Sunday’s march, Yilekal Getachew, chairman of the Semayawi (Blue) party, which organised the protests, said: “We have repeatedly asked the government to release political leaders, journalists and those who asked the government not to intervene in religious affairs.”

Journalists are not terrorists

Mr Nega is one of 11 journalists convicted in total under the country’s controversial 2009 anti-terror law, including two Swedish nationals, who were later released after pressure from their government, and six Ethiopian journalists convicted in absentia.
Of the 11 journalists convicted, three are currently jailed (Eskinder, Woubshet Taye and Reeyot Alemu). A further two, Yusuf Getachew and Solomon Kebede, were arrested in 2012 – both are awaiting trial on terror accusations.
The new laws were brought in after Ethiopia became a key regional security partner of of America’s so-called ‘war on terror’.
While the government claims the laws are necessary to maintain stability,  critics say they confuse the actions of a free press with terrorism.
Ethiopia has the highest number of exiled journalists in the world, the CPJ claims. Against a backdrop of increasing pressure from the authorities, between 2007 and 2012, 49 journalists fled the country. According to the CPJ, there are currently seven journalists in jail in Ethiopia, some without charge. In Africa, only Eritrea jails more.
Ethiopia’s government says all the journalists currently in jail are there due to their terrorist activities. It says Mr Nega is in jail for writing “articles that incited the public to bring the North African and Arab uprisings to Ethiopia.”
In contrast, a recent ruling by a panel of five independent United Nations experts said Mr Nega’s imprisonment came “as a result of his peaceful exercise of the right to freedom of expression”. The US state department’s latest human rights reports described the trials of Mr Nega and other journalists and dissidents as “politically motivated.”
Throughout his career, Mr Nega has refused to be exiled or silenced, even publishing critical pieces about the government right up until the days before his trial last year.
His last article, published on 9 September 2011, five days before his arrest, came in response to the arrest of dissident actor Debebe Eshetu, and discussed how improbable it was that those who were being jailed under the new laws were really “terrorists”.

Eskinder Nega’s letter: I will live to see the light  at the end of the tunnel

I shall persevere! ‘So I may do the deed that my own soul has to itself decreed’ – Keats.
Individuals can be penalised, made to suffer (oh, how I miss my child) and even killed. But democracy is a destiny of humanity which can not be averted. It can be delayed but  not defeated.
No less significant, absent trials and tribulations,  democracy would be devoid  of the soul that endows it  with character and vitality. I accept my fate, even embrace  it as serendipitous.
I sleep in peace, even if only in the company of lice, behind bars. The same could not be said of my incarcerators, though – they sleep in warm beds, next to their wives, in their homes.
The government has been able to lie in a court of law effortlessly as a function of the moral paucity of our politics. All the great crimes of history, lest we forget, have their genesis in the moral wilderness of their times. The mundane details of the case offer nothing substantive but what Christopher Hitchens once described as “a vortex of irrationality and nastiness”. Suffice to say that this is Ethiopia’s Dreyfus affair. Only this time, the despondency of withering tyranny, not smutty bigotry, is at play.
Martin Amis wrote, quoting Alexander Solzhenitsyn, that Stalinism (in the 1930s) tortured you not to force you to reveal  a secret, but to collude in  a fiction.
This is also the basic rationale of the unfolding human rights crisis in Ethiopia. And the same 1930s bravado that show-trials can somehow vindicate banal injustice pervades official thinking.
Wont to unlearn from history, we aptly repeat even its most brazen mistakes.
Why should the rest of the world care? Horace said it best: Mutato nomine de te fabula narratur. (Change only the name and this story is also about you). Where ever justice suffers, our common humanity suffers, too.
I will live to see the light at the end of the tunnel. It may or may not be a long wait. Whichever way events may go, I shall persevere!
Liberté, égalité, fraternité. History shall absolve democracy.
Written by Eskinder Nega from Kaliti Prison in Addis Ababa

African giant: Ethiopia profile

Africa’s oldest independent nation is also its second-most populated, and boasts one of the fastest-growing economies on the continent. It has long been seen by the West as a bulwark against radical Islamists in neighbouring Somalia, and is seen as one of the most stable countries in the Horn of Africa.
However, its government, led by the Prime Minister Hailemariam Desalegn, who was sworn in last September following the death of long-term leader Meles Zenawi, is also frequently criticised by human rights groups for cracking down on opposition and the media on the grounds of protecting national security. The country’s 547-seat legislature only has one opposition member.
Anti-terrorism legislation passed in 2009 has meant anyone who is caught publishing information that could induce readers into “acts of terrorism” are liable to jail terms of up to 20 years.
In addition to tightening its grip on the opposition and media, the government has also been accused of meddling in the day-to-day religious affairs of Ethiopians.
Muslims, who comprise about a third of Ethiopia’s 86.5 million people, have staged protests against the government, including mosque sit-ins in 2012, to call for some jailed religious leaders to be freed. The majority of Ethiopia’s population is Christian.
Ethiopia denies interfering in religious affairs, but also says it fears militant Islam is taking root in the country.

For more information:


Eskinder on Ethiopia's opposition
By Eskinder Nega | January 28, 2011

Egypt's and General Tsadkan's lesson to Ethiopian Generals.
By Eskinder Nega | February 4, 2011.

Meet Meles Zenawi: "World's poorest leader"
By Eskinder Nega | April 1, 2011






በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሱት ሀይሎች ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ የታች አርማጭሆ አንድነት ሰብሳቢ እና ሌሎች 15 ሰዎች ቶርቸር ተፈጸመባቸው


ግንቦት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጎንደር የታች አርማጭሆ ሰብሳቢ የሆኑት   ሚያዚያ 17 ፣ 2005 ዓም በቁጥጥር ስር በዋሉበት እለት ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ቤተሰባቸው ለኢሳት ገልጸዋል።
እህታቸው ወ/ሮ የንጉሴ ሲሳይ  ወንድማቸው ተዘቅዝቆ ለረጅም ሰአታት እንዲቆይ መደረጉን፣ በእጆቹ ጣቶች  መካከል ብረት እንዲገባ በመደረጉ ጣቶቹ ሽባ መሆናቸውን እንዲሁም እግሮቹ በድበዳ መመለጣቸውን  እያለቀሱ ተናግረዋል። አቶ ተገኝ በድብደባ ብዛት ለመሞት ሲቃረቡ ፖሊሶቹ በድንገት ሆስፒታል እንደተወሰዱ የገለጹት  ወ/ሮ የንጉሴ፣ ግንቦት21 ቀን የነበራቸው ቀጠሮም ወንድማቸው ለመዳን ባለመቻሉ ሳይቀርብ መቅረቱን ተናግረዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የፖሊስ ጣቢያውን አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ወረታው አለምን ያነጋገርናቸው ሲሆን፣ ኢንስፔክተሩም በሰጡት ምላሽ አቶ ንጉሴ አለመደብደባቸውን መታችሁ ማረጋገጥ ትችላላችሁ፣ ከዚህ በስተቀር ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት አልችልም ብለዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሙላት ፍሰሀ  አቶ ተገኝ ከሌሎች 8 ሰዎች ጋር በትጥቅ ትግል መንግስትን ለማስወገድ  ከሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ጋር ግንኙነት አለው ተብሎ ቢያዝም ፣ ድርጅታቸው የሚያውቀው በአንድነት ፓርቲ አመራርነቱ ነው ብለዋል።
በዚሁ ዞን በቃሮራ ወረዳ በሶረቃ ከተማ በተመሳሳይ መንገድ 7 ሰዎች ተይዘው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሎአል።

ዘረኛው የወያኔ ስርአትን በህዝብ ሰላማዊ አመፅ እንዴት መገርሰስ ይቻላል?


የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ ሰላማዊ አመፅን በተመለከተ በአለም አቀፍ ደረጃ ከታወቁ የሰላማዊ አመፅ ማሰልጠኛ ኮሌጆችና ተቋማት ጋር በመተባበር የስልጠና ፕሮግራሞችን ነድፎ ለአባላቶቹ የተሳካ ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል:: ንቅናቄው የተሳካ የህዝብ ሰላማዊ አመፅ በአባላቶቹ ተሳትፎ ብቻ የሚከናወን ሳይሆን የሁሉንም ህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያካተተ መሆን እንዳላበት ጠንቅቆ ያውቃል:: ይህ ታላቅ ሰላማዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ስኬታማ እንዲሆን ህዝቡ የሰላማዊ አመፅን ፅንሰ ሃሳብን በሚገባ መረዳትና ተግባራዊነቱም እንዴት መሆን እንዳለበት እንዲሁም የሚወሰዱ ጥንቃቄዎችን በሚገባ ማወቅና መለየት ይኖርበታል:: ስለሆነም ንቅናቄው ነፃ የሰላማዊ አመፅ አጫጭር የስልጠና ፕሮግራሞችን አዘጋጅቶ እያካሄደ ይገኛል::

ስልጠናውን እንዴት መቀላቀል ይቻላል? ስልጠናውን ለመከታተል 3 መሰረታዊ ቅድመሁኔታዎችን ማሟላት ያስፈልጋል::

1. ከሚቀርቧቸውና ከሚያምኗቸው የቅርብ ወዳጆችዎና ጓደኞችዎ ጋር በመሆን : ቢያንስ አስር አባላትን ያካተተ የራስዎን ቡድን ያቋቁሙ::
2. ሰላማዊ አመፅን መሰረት በማድረግ ከአባላትዎ ጋር ጠለቅ ያለ ውይይት በማካሄድ የቡድንዎን አላማ: ራእይ : እንዲሁም ተግባራትን በመወሰን ዝርዝር መመሪያዎችን ይንደፉ::
3. ከላይ የተዘረዘሩትን 2 ጉዳዮች ከፈፀሙ በኋላ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄን በድህረገጽ በፌስቡክ በኢሜልና በስልክ አድራሻዎቻችን ያግኙ::

ከተዘጋጁት የስልጠና ፕሮግራሞች መካከል:

1.መሰረታዊ የሰላማዊ አመፅ ፅንሰ ሃሳብና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታው
2. የሰላማዊ አመፅ ስኬታማነት በኢትዮጵያና መሰናክሎቹን እንዴት ማጥበብ ይቻላል
3. የሰላማዊ አመፅ ስትራቴጂ ታክቲክና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች
4. በህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የተሳታፊውን ደህንነት ለመጠበቅ ከመቀላቀል በፊት ሊደረጉ የሚገቡ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችና ዝግጅቶች
5. በህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የሰልፉን ሰላማዊነት ጠብቆ እስከመጨረሻው ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ስነልቦናዊና ስልታዊ እውቀቶችን ማወቅና መለየት
6. በህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የሚከሰቱ ማንኛውም ክስተቶችን ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ በሰአቱ ለማሳወቅ የሚቀርፁ እንዲሁም በቀጥታ በተለያዩ የሚዲያ ድህረገፆች ላይ የሚያስተላልፉ መሳሪያዎች አጠቃቀምና የቀረፃ ቴክኒኮች

እንዲሁም:-

1. መሰረታዊ የኢንተርኔትና የፌስቡክ አጠቃቀም
2. ከወያኔ የኦንላየን ሃከሮችና ስፓዮች እራስን እንዴት መከላከል ይቻላል
3. በፌስቡክና በኢሜል የሚደረጉ ሚስጥራዊ የመልክት ልውውጦች

Must-listen Interview with Abraham Yayeh Part one and two

Must-listen Interview with Abraham Yayeh Part  one



Must-listen Interview with Abraham Yayeh Part  two