Thursday, April 18, 2013

የወያኔ መንግስት በአማራ ተወላጆች ላይ እያደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋትና ከመኖሪያ ስፍራቸው ማፈናቀልን በመቃወም የተደረገ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌ ኦስሎ ተካሄደ

አፕሪል 18 2013 
watch video
 በአሁኑ ወቅት በአማራ ህዝብ ላይ መንግስት  እያደረገ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና ከሚኖሩበት ስፍራ ያለአግባብ ማፈናቀሉን  እንዲቆም የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ አፕሪል 18 2013 በኖርዌ ኦስሎ በደማቅና በተሳካ ሁኔታ ተካሂዶ ውሏል። ፕሮግራሙም በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 14፡00 የተጀመረ ሲሆን ከተለያየ የኖርዌይ ከተማ የተሰባሰቡ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያኖች በሰአቱ በመድረስ ሰላማዊ ሰልፉን የተሳካ እንዲሆን አድርገውታል። 

 በአሁን ሰአት ህዝባችን በሚፈናቀልበት እና መከራውን በሚያይበት ስፍራ ይኖሩ የነበሩና ስለቦታው ጠንቅቀው የሚያውቁት አቶ ማህተቤ መለስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ም/ሊቀመንበር ዝግጅቱን በንግግር ሲከፍቱ በንግግራቸውም ላይ ስለሆነው አስከፊ ሁኔታ እና መንግስት ስለሚደረገው የዘር ማጽዳት እና መሰሪ ድርጊቱን ከስር መሰረቱ በማብራራት ለታዳሚዎቻቸው አጋልጠዋል።

 በዝግጅቱም ላይ ስለሁኔታው የሚገልጹ መፈክሮች እና በኢትዮጵያ ባንዲራ ያሸበረቀ ሰላማዊ ሰልፍ ሲሆን የተለያዩ መፈክሮችም ይሰሙበት  ነበር። 

እንዲሁም የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮች መንግስት በአማራ ወገኖቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና ሰዎችን ከመኖርያ ስፍራቸው በማፈናቀል ያለምንም መጠለያ ሜዳ ላይ መጣላቸውን ተቃውመው ለድርጊቱም ፈላጭ ቆራጭ የሆነውን የወያኔን መንግስት በአለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ የሚያስችል ድርጊት በመሆኑ ለፍርድ እንደሚያቀርቡት ገልጸዋል ።

 እንዲሁም ከሀይማኖት ተቋማት የሙስሊም ድምፃችን ይሰማ ኮሚቴ በኖርዌይ ተወካይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም መንግስት በክርስቲያን የሃይማኖት ተከታዮች እና በሙስሊም የሃይማኖት ተከታዮች መካከልጣልቃ በመግባት ለማጋጨት ቢሞክርም እኛ አንለያይም ሁል ጊዜም አንድ ነን በሚል ጠንከር ባለ ንግግር የመንግስትን ሴራ አውግዘዋል። 

እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በማሰብ ምንግዜም ከጎናችሁ ነን በሚል አጋርነታቸውን ተግቢር ተግቢር በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል ። የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሴቶች ዘርፍና የወጣት ክፍሉ አጫጭር ቀስቃሽ የሆነ መልዕክት ካቀረቡ በሓላ  የተለያዩ የሲቪክ ማህበረሰብ ተወካዮችም ንግግር አድርገዋል ። 

የተቃውሞ ሰልፈኛውም በአንድነት በመሆን በታላቅ ድምጽ የወያኔ መንግስት በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ጭቆናና አፓርታይዳዊ አገዛዝ ኮንነው ይህንን አገዛዝ ከስር መሰረቱ ገርስሶ ለመጣል ሁላችንም አንድ ሆነን በመነሳትና የበኩላችንን አስተዋጽዎ በማድረግ ሐገሪቷ ከወደቀችበት አዝቅጥ ውስጥ ለማውጣት ጠንክረን መታገል አለብን በሚል በመላው አለም ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ ጥሪያቸውን በማስተላለፍ ፕሮግራሙን በኖርዌይ ሰአት አቆጣጠር 16፡00 ሰአት  የፕሮግራሙ መሪ የማጠቃለያ ንግግር ካደረጉ በኋላ አጠናቀዋል ።

ይህንን ፕሮግራም በመተባበር ያዘጋጁት ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ እና ኢህአፓ በኖርዌይ  ሲሆኑ  ከድርጅቶቻቸው አባላት እና ከሲቪክ ማህበረስብ የተውጣጡ ቡድኖችን task force በመፍጠር ታክስ ፎርሱም በመሰባሰብ የተለያየ እቅዶችን ለማዘጋዘት ወስኖ ሰላማዊ ሰልፉንም የመጀመሪያ እቅዶ በመሆኖ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተረባርበው በሰሳካ ሁኔታ ሊያዘጋጁት ችለዋል ። 

ቸር ያሰማን 

ማዲንጎ አፈወርቅ- በላይ 


 ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኑር 
አዘጋጅ ፤እስክንድር አሰፋ
ኦስሎ
ኖርዌይ 

No comments:

Post a Comment