Monday, April 29, 2013

በስታቫንገር ኖርዌይ ነዋሪ የሆነው ወጣት አብዮ ጌታቸው ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና ስለ ቦንድ ግዢ የሚለን ነገር አለ

እስክንድር  አሰፋ
ከኦስሎ  ኖርዌይ 
april 29.2013

watch video
 ወጣት አብዮ ጌታቸው በኖርዌይ እስታቫንገር ነዋሪ ሲሆን ለብዙ አመታት በዚሁ ከተማ የኢትዮጵያን ወራሪ መንግስትን በመቃወም ዲሞንስትሬሽን  በማድረግና እንዲሁም ማንኛውንም እናት ሐገሩ የምትፈልገውን ነገር በአቅሙ እያገለገለ  የሚኖር እውነተኛ ዜጋ ነው።

 የወያኔ መንግስት በሐገራችን ህዝብ ላይ በአባይ ግድብ ስም ከእለት ጉርሱ ላይ እየነጠቀ ለግል ጥቅሙ እንደሚያውል አመታት አስቆጥሯዋል  እንዲሁም   በሐገር ቤት አልበቃ ብሎት ወደ ዲያስፖራው ፊቱን በማዞር አለምን በማካለል  ይገኛል  ለምሳሌ በምድረ አሜሪካን ፤በአውሮፓ፤ ሳውዝ አፍሪካ እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ የሚገኙትን ኢትዮጵያኖች አምታትቼ ኮሮጆዬን እሞላለሁ በሚል የህልም ቅዥት በሄደበት አህጉራት ሁሉ የቅሌትን ሸማ  ተከናንቦ  እየተዋረደ ይገኛል  ። 

አሁንም በምድረ ኖርዌይ ይህንኑ ቅሌቱን በአለም ላይ እራሱን  ለማዋረድ ቀና ደፋ ሲል ቆይቶ በApril 20 .2013 stavanger  ሊያደርግ ያሰበውን የቦንድ ሽያጭ ማሰባሰቢያ  በጀግኖች ልጁቻችን መደናቀፉና መዋረዱ የቅርብ ቀን ትዝታ ነው ።

 እናም በዛ ወቅት በእስታቫንገር ከሚኖሩ የናት ሀገራቸን የቁርጥ ልጆች ከሆኑት አንዱ የሆነው ወንድማችን አብዮ ጌታቸው ሲሆን  ለወያኔ ካዝና ማደለቢያ ሊጋዝ የነበረውን ገንዘብ አዘጋጆቹ እንደቋመጡ  እንዲቀር  ካደረጉት አንዱ ወገናችን ሲሆን  እንዲሁም በዛ ወቅት ከተለያየ አካባቢ ለሄድነው ወገኖቹ የሚሆን መስተንግዶና ማረፊያ በቀላሉ እድናገኝ ያደረገና እንዲሁም  በብዙ ነገር ሃላፊነትን ተረክቦ ቀና ደፋ ሲል የነበረ  ታጋይ  ነው ።

 በዛው ቀን በተገነናኘንበት ጊዜ ትንሽ ስለ ዝግጅቱ ሁኔታና ስለሐገራችን ወቅታዊ  ጉዳይ  ተወያይተን ነበር በእለቱም  በምስል ስለቀረጽኩት እንድትመለከቱት ስል በትህትና  እጠይቃችኋለው።

ድል ለኢትዮጵያ ሞት ለዘረኙችና ለከፋፋዮች
ቸር ያሰማን 



Friday, April 26, 2013

semayawi party leaders in benshangul part 1 and 2 በቤንሻንገል ክልል መተከል ዞን በጵሪ ቀበሌ ተፈናቅለው በድጋሚ ተመለሱ የተባሉ የአመራ ተወላጆች የደረሰባቸውን በደል ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሲገልጹ የሚያሳይ ቪዲዮ

በቤንሻንገል ክልል መተከል ዞን በጵሪ ቀበሌ ተፈናቅለው በድጋሚ ተመለሱ የተባሉ የአመራ ተወላጆች የደረሰባቸውን በደል ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሲገልጹ የሚያሳይ ቪዲዮ






semayawi party leaders in benshangul part 2






Monday, April 22, 2013

ቤንሻንጉል የተፈናቃዩች ሁኔታ


ኢትዮጵያ

ቤንሻንጉል የተፈናቃዮች ሁኔታ

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተባረዉ እንደገና እንዲመለሱ የተደረጉ የአማራ ብሄር አባላት በአስከፊ ሁኔታ እንደሚገኙ ሰማያዊ ፓርቲ መግለፁን የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን የላከልን ዘገባ ያመለክታል።
ይህን ጥናት ለማድረግ ወደክልሉ የተጓዙ የፓርቲዉ አመራር አባላት ለአምስት ሰዓታት ያህል ታስረዉ መለቀቃቸዉም ታዉቋል። ዝርዝሩን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ልኮልናል
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ

Sunday, April 21, 2013

Politiet stoppet møte i Tasta bydelshus


Politiet rykket ut med tre biler og seks politimenn og stoppet et møte i Tasta bydelshus der stemninga var i ferd med å bli svært så amper blant de vel 300 frammøtte.

De rundt 300 frammøtte var etiopiske asylsøkere eller folk med etiopisk bakgrunn. Politiet fryktet at det skulle komme helt ut av kontroll da folk i salen gikk til hard verbal konfrontasjon mot to representanter fra den etiopiske ambassaden i Stockholm som hadde innkalt til og ledet møtet.

Politiet ga først beskjed om at alle demonstrantene måtte forlate møtet, mens de to ambassadefolkene og deres eventuelle støttespillere kunne bli sittende.

 Dette nektet de frammøtte demonstrantene, og flere fryktet at det skulle komme til åpen konfrontasjon mellom politiet og folk i salen. Deretter bestemte innsatslederen Øyvind Sveinsvoll ved Rogaland politidistrikt seg for å stoppe hele møtet og rydde hele salen.

Det var en klok avgjørelse, mente flere av de frammøtte demonstrantene. De ville ikke at de to ambassadefolkene skulle bli sittende igjen som «seiersherrer» mens de selv ble kastet ut.

- Målet vårt var å stoppe møtet. Det klarte vi, sier en av dem til Aftenbladet.

ARTIKKELEN FORTSETTER UNDER BILDET
Mange av dem i salen tok ordet og fortalte om slektninger som var blitt fengslet, drept eller som hadde forsvunnet i politiets varetekt.
Mange av dem i salen tok ordet og fortalte om slektninger som var blitt fengslet, drept eller som hadde forsvunnet i politiets varetekt.
FOTO: Jarle Aasland
 

Måtte isolere ambassadefolkene

Stemningen ble spent at politiet valgte å isolere de to ambassadefolkene fra resten av møtedeltakerne. De eskorterte dem ut til en privat bil som fraktet dem vekk fra området. De 300 frammøtte fikk deretter slippe ut av salen.
Det var generalkonsul ved den etiopiske ambassaden, Mebrat Beyene Abay, som skulle lede møtet sammen med ambassade-sekretæren. Hovedtemaet var innsamling av penger i det etiopiske eksilmiljøet til et meget omstridt oppdemningsprosjekt - et prestisjeprosjekt for regimet i Etiopia.

Massedemonstrasjoner i utlandet

De etiopiske myndighetene har forsøkt å holde lignende "innsamlingsmøter" både i Sør-Afrika, Saudi Arabia, USA og Tyskland, og hver gang har møtene endt i svære demonstrasjoner mot brudd på menneskerettighetene i Etiopia. Folk fengsles uten lov og dom, frie valg er avskaffet, ytringsfriheten likeså, avisene er statskontrollert og mange journalister sitter fengslet.

Ikke frivillig betaling

Flere tok til ordet under møtet på Tasta bydelshus og sa dette ikke var en frivillig innsamlingsaksjon. De som ikke betalte inn penger, kunne forvente seg problemer når de henvendte seg til ambassaden for å få pass eller id-papirer.

Ruster seg til Oslo-opprør

Lørdagsmøtet var det første i sitt slag i Norge. Og eksil-etiopierne kom i egne busser fra Oslo, andre kom fra Steinkjær, Otta, Stord og Bergen for å demonstrere i Tasta bydelshus mot det sittende regimet i Etiopia.

28. april skal den etiopiske ambassaden i Stockholm holde et lignende møte i Oslo.

- Vi kommer til å fylle hele busser med demonstrant.

Friday, April 19, 2013

ESAT Efeta 18 April 2013


Ambassador Girma Birru faced fierce opposition

By Esconder . A
18.04.2013
ወያኔ በጭቁኑ ኢትዮጵያዊያን ላይ  መሳሪያ በመደቀን ክብሩን በሀገሩ ውስጥ ቢገፈውም በውጪ ያሉት ውድ ወገኖቹ ደግሞ
ከአባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ በሚል በየአለሙ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ። ስለዚህም የወያኔን  አምባሳደር በUSA ግርማ ብሩን ከተጋበዘበት ሆቴል ቅንድቡን ብለው አባረውታል ። VIVA USA ETHIOPIAN

Thursday, April 18, 2013

የወያኔ መንግስት በአማራ ተወላጆች ላይ እያደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋትና ከመኖሪያ ስፍራቸው ማፈናቀልን በመቃወም የተደረገ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌ ኦስሎ ተካሄደ

አፕሪል 18 2013 
watch video
 በአሁኑ ወቅት በአማራ ህዝብ ላይ መንግስት  እያደረገ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና ከሚኖሩበት ስፍራ ያለአግባብ ማፈናቀሉን  እንዲቆም የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ አፕሪል 18 2013 በኖርዌ ኦስሎ በደማቅና በተሳካ ሁኔታ ተካሂዶ ውሏል። ፕሮግራሙም በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 14፡00 የተጀመረ ሲሆን ከተለያየ የኖርዌይ ከተማ የተሰባሰቡ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያኖች በሰአቱ በመድረስ ሰላማዊ ሰልፉን የተሳካ እንዲሆን አድርገውታል። 

 በአሁን ሰአት ህዝባችን በሚፈናቀልበት እና መከራውን በሚያይበት ስፍራ ይኖሩ የነበሩና ስለቦታው ጠንቅቀው የሚያውቁት አቶ ማህተቤ መለስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ም/ሊቀመንበር ዝግጅቱን በንግግር ሲከፍቱ በንግግራቸውም ላይ ስለሆነው አስከፊ ሁኔታ እና መንግስት ስለሚደረገው የዘር ማጽዳት እና መሰሪ ድርጊቱን ከስር መሰረቱ በማብራራት ለታዳሚዎቻቸው አጋልጠዋል።

 በዝግጅቱም ላይ ስለሁኔታው የሚገልጹ መፈክሮች እና በኢትዮጵያ ባንዲራ ያሸበረቀ ሰላማዊ ሰልፍ ሲሆን የተለያዩ መፈክሮችም ይሰሙበት  ነበር። 

እንዲሁም የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮች መንግስት በአማራ ወገኖቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና ሰዎችን ከመኖርያ ስፍራቸው በማፈናቀል ያለምንም መጠለያ ሜዳ ላይ መጣላቸውን ተቃውመው ለድርጊቱም ፈላጭ ቆራጭ የሆነውን የወያኔን መንግስት በአለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ የሚያስችል ድርጊት በመሆኑ ለፍርድ እንደሚያቀርቡት ገልጸዋል ።

 እንዲሁም ከሀይማኖት ተቋማት የሙስሊም ድምፃችን ይሰማ ኮሚቴ በኖርዌይ ተወካይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም መንግስት በክርስቲያን የሃይማኖት ተከታዮች እና በሙስሊም የሃይማኖት ተከታዮች መካከልጣልቃ በመግባት ለማጋጨት ቢሞክርም እኛ አንለያይም ሁል ጊዜም አንድ ነን በሚል ጠንከር ባለ ንግግር የመንግስትን ሴራ አውግዘዋል። 

እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በማሰብ ምንግዜም ከጎናችሁ ነን በሚል አጋርነታቸውን ተግቢር ተግቢር በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል ። የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሴቶች ዘርፍና የወጣት ክፍሉ አጫጭር ቀስቃሽ የሆነ መልዕክት ካቀረቡ በሓላ  የተለያዩ የሲቪክ ማህበረሰብ ተወካዮችም ንግግር አድርገዋል ። 

የተቃውሞ ሰልፈኛውም በአንድነት በመሆን በታላቅ ድምጽ የወያኔ መንግስት በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ጭቆናና አፓርታይዳዊ አገዛዝ ኮንነው ይህንን አገዛዝ ከስር መሰረቱ ገርስሶ ለመጣል ሁላችንም አንድ ሆነን በመነሳትና የበኩላችንን አስተዋጽዎ በማድረግ ሐገሪቷ ከወደቀችበት አዝቅጥ ውስጥ ለማውጣት ጠንክረን መታገል አለብን በሚል በመላው አለም ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ ጥሪያቸውን በማስተላለፍ ፕሮግራሙን በኖርዌይ ሰአት አቆጣጠር 16፡00 ሰአት  የፕሮግራሙ መሪ የማጠቃለያ ንግግር ካደረጉ በኋላ አጠናቀዋል ።

ይህንን ፕሮግራም በመተባበር ያዘጋጁት ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ እና ኢህአፓ በኖርዌይ  ሲሆኑ  ከድርጅቶቻቸው አባላት እና ከሲቪክ ማህበረስብ የተውጣጡ ቡድኖችን task force በመፍጠር ታክስ ፎርሱም በመሰባሰብ የተለያየ እቅዶችን ለማዘጋዘት ወስኖ ሰላማዊ ሰልፉንም የመጀመሪያ እቅዶ በመሆኖ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተረባርበው በሰሳካ ሁኔታ ሊያዘጋጁት ችለዋል ። 

ቸር ያሰማን 

ማዲንጎ አፈወርቅ- በላይ 


 ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኑር 
አዘጋጅ ፤እስክንድር አሰፋ
ኦስሎ
ኖርዌይ 

ሁሉም ለሀገሩ ዘብ ይቁም!!



writer and author from norway
በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በሀገራችን ዉስጥ የተጣለብን ከፋፍለህ ግዛ ዘመቻ ከቀድሞው በተለየ እጅግ ዘግናኝና አስከፊ በሆነ ሁኔታ ላይ መገኘት የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ወኔና ሞራል ሳይነካ አይቀርም ብዬ እገምታለሁ።  ከዚህም ውስጥ ዋነኛውና የመጀመሪያው ሰሞኑን በአማራዉ ብሔረሰብ ላይ በመድረስ ላይ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ህዝቡን ከአድማስ አድማስ እያነጋገረው መምጣቱ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሬ ምን ሠራሁ በማለት እራሱን እየጠየቀ ? ይህን ዘረኛ የሆነ የወያኔ መንግስት ከስር መሰረቱ ነቅሎ ለመጣል በቁርጠኝነት በመነሳት ሀገራዊ የዜግነት ግዴታውን መወጣት አለበት ፡፡ 


ለዚህም በዋንኛነት ትኩረት ተሰጥቶት ለነገ ይደር የማይባልበት ጉዳይ ፣ ማናቸውም የተቃዋሚ ፓርቲዎችና ፥ የድጋፍ ድርጅቶች ፣ አንድ በመሆንና እጅ ለእጅ በመያያዝ ቅድሚያ ለሀገር ሰጥቶ የመጣብንን የወያኔ ሰደድ እሳት ማጥፋት ግድ ይለናል ፡፡

ለዚሁም ለ- April 8 ቀን  በኦስሎ ኖርዌይ የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያና  ኢህአፖ የጠሩት ሀገርህን አድን ዘመቻ ጥሪ እንደ አንድ አብነት ሆኖ የሚጠቀስ  ነው ፡፡  ዘረኛው የወያኔ መንግስት ከጥነሰሱ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ስልጣን ላይ ፊጥ ብሎ እስከቀጠለበት ድረስ ሰንቆ ያመጣውን የሀይማኖትና የዘር ማጥፋት ትልም በተግባር ላይ ማዋል ከጀመረ እነሆ ብዙ አመታትን አስቆጥሯል ፡፡ ይኸውም የመጀመሪያው በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የተጀመረው የሀይማኖት ብጥብጥ በአይበገሬው የሙስሊም ወንድሞቻችን ትግል ዕለት በዕለት እየተፋፋመ ወያኔን እንቅልፍ ቢነሳውም ፣ ህወሃት-ኢሃዴግ ተስፋ ባለመቁረጥ እንደገና ፊቱን ወደ ኦርቶዶክስ ኃይማኖት በማዞር የተለመደውን የስልጣን ማራዘም ዘመቻና ህዝብን ከህዝብ የማፋጀት አባዜን በማፋፋም እነሆ አሁን ደግሞ የአማራውን ህዝብ ከእናት ምድሩና ሀገሩ የማባረርና ዘር የማጽዳት ዘመቻውን በሰፊው ተያይዞታል።

ይህም ከማናለብኝነትና ለህዝቡ ካለው ከፍተኛ ጥላቻና ንቀት የመነጨ በመሆኑና በአንድ ዘር የበላይነት ብቻ የማመን ጠባብነት ጭምር የተጸናወተው በመሆኑ ነው ። ወያኔ ከመጀመሪያው ጀምሮ በኢትዮጵያ አንድነት የማያምንና ጭራሽ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንደሌለችና ኢትዮጵያ የሚለውንም ስም ያገኘችው በሚኒሊክ ዘመነ መንግሥት መሆኑን ለማሳመን የሚያደርጉትን ባዶ ጥረት በመረጃ  አንድ ግለሰብ በኢሳት ቲቪ ላይ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አገኔ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ከነ መረጃቸው አስደምጦናል ። ይህም ማለት አማራው ለትግራይ ህዝብ ጠላቱ መሆኑን አስምረው አረጋግጠውልናል ማለት ነው ። እንደውም ለአማራ ያላቸውን ጥላቻና ዘረኝነት ለመግለጽ ሲሉ ! ሆስፒታል ውስጥ አንድ በሽተኛ ከፈረንጅ ሀኪምና ከአማራ ሀኪም ማን እንዲያክምህ ትፈልጋለህ ተብሎ ምርጫ ሲቀርብለት የመለሰው መልስ አማራ ከሚያክመኝ ፈረንጁ የፈለገውን ቢያደርገኝ ይሻለኛል ብሎ በሽተኛው እስከመመለስ መድረሱን አድምጠናል።

ጎበዝ ! ወያኔዎች እኮ ዛሬ አማራውን ነገ ደግሞ ጉራጌውን ከዛም ኦሮሞውን ከሀገር በማፈናቀል እንደተባለውም ኢትዮጵያ የተባለችውንና ለዘመናት ተከብራና ታፍራ የኖረችውን፤ ጀግኖች አባቶቻችን አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው ያስረከቡንን ሀገር ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ሆን ብለው የተነሱ አረሞች ናቸው።  እምነበረድ ይክበዳቸውና ! አሁን በአካለ ህይወት የሌሉት ፣ የቀድሞው ጠ.ሚኒስተር የነበሩት በራዕያቸው ግን አገሪቱን የሚያስተዳድሩት ሰው ባለቤት የሆንችው ወ\ሮ አዜብ መስፍን(ጎላ) ሰሞኑን በኢቲቪ ማቅ (ጥቁር ለብሳ)  እኛን ግን ሳቅ  አላብሳናለች ፣ ስለ ባለቤትዋ የወር ደሞዝ ማለት ነው ለኢህአዲግ መዋጮ ከፍሎ የሚደርሰው 4,000ብር ብቻ ነው ብላናለች ፡፡  አንድም ቀን ልጆቼን ፣ ቤቴን ሳይል ለሀገሩ 24 ሰአት ያገለገለ መሪ ነው ፥ ወደዚህ ሀገር ሲመጣም ጭንቅላቱን ብቻ ነው ይዞ የመጣው ብላናለች ። ሌላው ሰው ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ምን ጨብጦ እነደመጣ ፣ ኧህ ! ካሏት አዜብ መስፈን ብዙ ቀልዶችን ሳትነግረን አትቀርም ፡፡

ወይዘሮዋን አንድ ያልገባት ነገር ቢኖር ፣  መለስ  ጭንቅላቱን አሟጦ የተጠቀመበት ፣ የባንዳ ልጅ እየተባለ ያደገበትን በቀል ፣ህዝቡ ላይ በመበቀል ሙሉ ኃይሉን የተጠቀመ  አረመኔ ፥ ጨካኝና ዘረኛ  መሪ መሆኑን ያለመረዳቷ ጉዳይ ነው ። ከዚህ በፊት የመለስ ራእይ ሳይደለዝና ሳይበረዝ ትግሉ ወደ ፊት ይቀጥላል ያልሽው እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ዛሬ ደሞ በትንሽ ደሞዝ እየተከፈለው ሌት ተቀን እየሰራ ሀገራችንን ትልቅ ደረጃ ላይ እንድትደርስ ያደረገ የመጀመሪያው መሪ መሆኑ ተሰምሮበት (Guinness book of records) ላይ ተመዝግቦ መቀመጥ አለበት አይነት ትእዛዛዊ የማስጠንቀቂያ መልክት በማስተላለፍ “የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ” አይነት ጨዋታሽን በጥሩ ተውኔታዊ ገቢር ! የሃዘን ልብስሽን እንደ ጉሬዛ ግንባርሽ ድረስ ተከናንበሽ ትውነሽልናል ፡፡

ምናልባት መለስ ዜናዊ ትግራይን አልምቶ ይሆናል አላውቅም በእርግጠኝነት ግን መናገር የምችለው ቀሪዋን ኢትዮጵያን አድምቷል ። ህዝቡንም እርስ በእርሱ ደም እንዲቀባባና ፥ በዘርና በሀይማኖት በመከፋፈል የሀገሪቷንም መሬት ለባእዳን በመሸጥ ህዝቡን ለከፍተኛ ችግርና መከራ አጋፍጦ ፣ ዜጋ ሁሉ የሚወዳትን ሀገሩን እየጣለ በየአረብ ሀገሩና አውሮፓ ውስጥ እንዲሰደድ ያደረገ ትልቅ የማይረሳ ነቀርሳና ጠባሳ ህዝቡ ላይ  ትቶ የሄደ መሪ ነው ። የእርሱን ራእይ በመከተል እነሆ አሁንም ያሉት መሪ ተብዬ ጃሌዎቹ ከሱ በባሰና አስከፊ በሆነ ሁኔታ ህዝቡን ከተወለደበትና እትብቱን ከቀበረበት ቀዬ በግፍና በጭቆና እያባረሩት ይገኛሉ ። ስለዚህ ጎበዝ ይህን ጉዳይ ዝም ብለን ማየት የማንችለውና ሁላችንም በአንድ ላይ ሆነን እጅ ለእጅ ተያይዘን ወያኔንና አንጃዎቹን “በቃ” ማለት የሚጠበቅብን ወቅቱ  ከምንግዜውም በላይ አሁን ነው ።

በመጨረሻም ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር የኢህአፓ ወክንድ የሚያደርገው እንቅስቃሴ እጅግ የሚያኮራ በመሆኑ ሳይደነቅ መታለፍ የሌለበት ጉዳይ ነው። ለዚሁም ከዚህ በፊት በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ወያኔ ያደረሰውን በደል አብሮ ከጎኑ በመሰለፍ ፣በኦርቶዶክስ ሀይማኖት ላይም እንዲሁ ችግሩን አብሮ በመጋፈጥና አሁን ደሞ በአማራው ህዝብ ላይ ወያኔ የሚያደርሰውን አሰቃቂ በደል በመቃወም በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። ሌላው ደግሞ ማናቸውም ለሀገራችን ተቆርቋሪዎች ነን የሚሉ ኢትዮጵያዊያኖች ወገኖቻችንን በሙሉ የሚያሳትፍ (keep of fighting ethiopian youth forum KOFEYF) የሚል የፓልቶክ (paltalk room) ከፍቶ ዘውትር በየሳምንቱ እሁድ ከ15፡00 – 3፡00pm ሰአት ጀምሮ አንጋፋ የሆኑ የፖለቲካ ባለሞያዎችንና የሀገር ተቆርቋሪዎችን በመጋበዝ ትልቅ አስተዋጾ በማድረግ ላይ ይገኛል ። እርሶም ይህን እድል በመጠቀም ያለዎትን እውቀት ለማህበረሰቡ በማስተማርና በመማር ለሀገርዎ  ትልቅ አስተዋጽኦ በማድረግ ዉድ ሀገራችንን  ኢትዮጵያን ከገባችበት የድጥ ማጥ ውስጥ እናውጣት የሚል ተማጽኖዬን በማክበር እጠይቃለሁ።

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!!

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያ ሀገራችንን በምህረቱ ይጎብኛት!!!
Dawit Abebe, April 2013. Oslo

Wednesday, April 17, 2013

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ኤምባሲዎችን መጠለያ እየጠየቁ መሆኑ ተጠቆመ




-    የቀን ተማሪዎች እንዳይማሩ ኮሌጁ ተዘግቷል
-    በረሃብ አድማው ምክንያት ተማሪዎች ሆስፒታል ገብተዋል
-    ልብሳቸውን አንጥፈው መለመን ጀምረዋል

በመሀል አራት ኪሎ የሚገኘውና ለበርካታ ዘመናት መንፈሳዊ ትምህርት በማስተማር፣ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ መንፈሳዊ ምሁራንን ባፈራው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ በቀን ተማሪዎችና በኮሌጁ ኃላፊዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እየከረረ በመሄዱ፣ ተማሪዎቹ የኮሌጁን ግቢ ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው አንዳንድ ኤምባሲዎች መጠለያ እንዲሰጧቸው ደብዳቤ እየተጻጻፉ መሆኑ ተጠቆመ፡፡
7db105d1665f3ec4571b586cee2f157f_Lተማሪዎቹ በየካቲት ወር በኮሌጁ ውስጥ ይፈጸማሉ ያሏቸውን ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶች ማለትም የምግብ አቅርቦት፣ የትምህርት አሰጣጥ፣ አግባብ ያልሆነ ንብረት አያያዝና ሌሎችም ድርጊቶች እንዲስተካከሉ ለአዲሱ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ደብዳቤ በማቅረብ፣ ምላሽ እስከሚያገኙ ድረስ ትምህርት አቁመው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ጉዳዩ በኮሚቴ እንደሚታይና እስከዚያው ድረስ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በተላለፈላቸው ትዕዛዝ መሠረት፣ ተማሪዎቹ ያቋረጡትን ትምህርት በመከታተል ላይ እያሉ፣ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ መምህር ተመድበዋል በማለት፣ ‹‹ከሃይማኖታችን ውጭ ሌላ ሃይማኖት ያለው ሰው ሊያስተምረን አይገባም›› ማለታቸውን ተከትሎ አለመግባባቱ መካረሩ ታውቋል፡፡

 ‹‹አንዳንድ መምህራን ሊያስተምሩን አይችሉም ስላላችሁ ከማስተርስና የማታ ተማሪዎች በስተቀር ግቢውን ለቃችሁ ውጡ፤›› መባላቸውንና ከመጋቢት 30 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ትምህርት ሙሉ በሙሉ ማቆማቸውን አንዳንድ ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡


የረሃብ አድማ ካደረጉ አንድ ወር እንዳለፋቸውና ችግራቸውን ገልጸው በደብዳቤ ካሳወቋቸው ከቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከፓትርያርኩ፣ ከተወካዮች ምክር ቤት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ከፌዴሪል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ከፀረ ሙስና ኮሚሽንና ከሌሎች የሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ምንም ምላሽ በማጣታቸው፣ አንዳንድ ኤምባሲዎች መጠለያ እንዲሰጧቸው ደብዳቤ እየተጻጻፉ መሆኑን ያነጋገርናቸው ተማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡

ኃላፊነትን መውሰድ ፈርተው ወይም ከብዷቸው ክብ ማህተም በማድረግ ብቻ በተለጠፈ ደብዳቤ ግቢውን ጥለው እንዲወጡ መታዘዛቸውን የሚናገሩት ተማሪዎቹ፣ ላለፉት ቀናት ምዕመናኑ በሚሰጧቸው ዳቦና ሙዝ መክረማቸውን ገልጸዋል፡፡
በረሃብ አድማው የተጐዱና አቅም አንሷቸው ተዝለፍልፈው የወደቁ ሁለት ተማሪዎች ትናንትና ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሚናገሩት ተማሪዎቹ፣ ‹‹ኮሌጁን ልቀቁና ውጡ›› የሚላቸው ግለሰብ ወይም ማን እንደጻፈው በማይታወቅ ደብዳቤ ሳይሆን ቅዱስ ሲኖዶስ በመሆኑ፣ በረሃብ ሕይወታቸው ቢያልፍም ሲኖዶሱ ‹‹ልቀቁ›› እስከሚላቸው እንደሚቆዩ አስታውቀዋል፡፡

ከማታና ከማስተርስ ተማሪዎች በስተቀር ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች እንዲወጡ መታዘዛቸውን የገለጹት ተማሪዎቹ፣ መምህራንም እነሱን እንዳያስተምሩ መታዘዛቸውን ጠቁመዋል፡፡

ሚያዝያ 7 ቀን 2005 ዓ.ም. ተማሪዎቹ በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ በመገኘት ልብሳቸውን አንጥፈው ሲለምኑ፣ በፖሊስና ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ድብደባና እንግልት እንደተፈጸመባቸውም ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹ ሲለምኑ ያስተዋሉ ምዕመናን ፓትርያርኩ ወደሚያስቀድሱበት መንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው፣ ፓትርያርኩ ሊያስቀድሱ ሲመጡ እግራቸው ሥር ወድቀው ቢለምኗቸውም፣ ምንም ምላሽ ሳይሰጧቸው ማለፋቸውን ተማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

በመቀሌ የሚገኘው የከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች፣ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጣቸው ለፓትርያርኩ ደብዳቤ መጻፋቸውን፣ የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ደግሞ ለምግብና ለተለያዩ ወጪዎች ዕርዳታ እያደረጉላቸው መሆኑንና ምዕመናኑም እየረዱዋቸው እንደሆነ ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ጢሞቲዎስን፣ በተማሪዎቹ ላይ እየተወሰደ ስለሚገኘው ዕርምጃ ማብራሪያ እንዲሰጡን በሥፍራው ተገኝተን ብንጠይቅም፣ ‹‹የሉም፤ ፀሎት ላይ ናቸው፤›› በሚል ምላሽ ማግኘት አልቻልንም፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በሚገኙበት መንበረ ፓትርያርክ ቤተ ክህነት ቅጥር ግቢ ተገኝተን ለማነጋገር ያደረግነውን ሙከራ፣ ‹‹ሰሞኑን ስብሰባ ላይ ስለሆኑ ማንም መግባት አይችልም፤›› በማለት በጥበቃ ሠራተኞች ልንመለስ ችለናል፡፡

UNESCO awards Reeyot Alemu – Activists wary of her health


Columnist Reeyot Alemu has been awarded the 2013 UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize, according to the press release on UNESCO website. (read at full text at the bottom)
However, Ethiopian opposition activists are worried of health condition claiming that the prison administration is denying her proper medical care.
Activist Kirubel Teshome reported on his facebook account that:
Reeyot AlemuJailed Ethiopian woman Journalist, Reeyot Alemu was less cheerful than she used to be when we visited her yesterday, April 7, 2013.
She looks so tense and worried about her health and the ill treatment she is having in prison.
She went to medical checkup on March 19 where her new doctor, who has no follow up of her case and hardly knows her medical history, ordered for another appointment after three months.
However hard she insisted to know the exact appointment date, she is totally made out of the loop and it is still held a secret by the prison guards and management. The guard who escorted her to hospital told her that she received the appointment date but she is not ordered to tell her when.
Reeyot told us that she formally complained to Prison administrator about the lack of proper medical attention she should be having and impartial treatment of the rights to her education she is not yet allowed to enroll.
The prison administrators heard her appeals and grievances but instead of relieving her from the additional burden of injustice they formally charged her with an alleged accusation of not respecting and abiding prison rules and guards. Such charges utmost are punishable to solitary confinement with no permission to visitors, even close relatives.
*********
Here is the press release from UNESCO this week:
Ethiopian journalist Reeyot Alemu wins 2013 UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize
(April 16, 2013)
Imprisoned Ethiopian journalist Reeyot Alemu is the winner of the 2013 UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize. Ms Alemu was recommended by an independent international jury of media professionals in recognition of her “exceptional courage, resistance and commitment to freedom of expression.”
The Jury took note of Reeyot Alemu’s contribution to numerous and independent publications. She wrote critically about political and social issues, focusing on the root causes of poverty, and gender equality. She worked for several independent media. In 2010 she founded her own publishing house and a monthly magazine called Change, both of which were subsequently closed. In June 2011, while working as a regular columnist for Feteh, a national weekly newspaper, Ms Alemu was arrested. She is currently serving a five year sentence in Kality prison.
The UNESCO Guillermo Cano World Press Freedom Prize was created in 1997 by UNESCO’s Executive Board. It is awarded annually during the celebration of World Press Freedom Day on 3 May, which will take place this year in Costa Rica.
The Prize honours the work of an individual or an organization which has made a notable contribution to the defence and /or promotion of freedom of expression anywhere in the world, especially if risks have been involved. Candidates are proposed by UNESCO Member States, and regional or international organizations active in the fields of journalism and freedom of expression. Laureates are chosen by a jury whose members are appointed for a once renewable three-year term by the Director-General of UNESCO.
**********

Monday, April 15, 2013

በቤንሻንጉ ጉምዝ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ለተፈናቀሉት ወገኑቻችን መርጃ የሚሆን ገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በኦስሎ ከተማ


ለወገን ደራሽ ወገን ነበር የሚሉት አባቶቻችን አሁንስ ለዚህ ምስኪን ወገኖቻችን ማነው ደራሻቸው እኛው አይደለንም እንዴ ወገን በሉ ባለን አቅም እንድረስላቸው ወገን እርሃብ ቸነፈሩ ውርጩ ሲፈራረቅባቸው ህጻን አዛውንቱን ከቤት ንብረታቸው ሲያፈናቅሏቸው ማየቱ ምን ያህል ያሳዝናል በቦታው ላይ ያለ ያውቀዋል ስለዚህ ነገ ዛሬ ሳንል አሁኑኑ ያለንን እናግዛቸው ለምታደርጉት እርዳታ የአካውቱን ቁጥር ከፖስተሩ ላይ ወስዳችሁ አሁኑኑ ላኩላቸው ካስፈለገም ይሄውላችሁ ኢማኖ  Bank 05401729420 ለመንፈስም እርካታን ይሰጣል በአምላክም ዘንድም  ዋጋን ያስከፍላል በተረፈ ስለ ትብብሩ በእግዚአብሄር ስም እናመሰግናለን ፡ ተባረኩ ፡ ገለቱማ  ; ሜርሲ ቡኩ;thank you  ያቀኔሌይ ፡ረቢሲያን ከኙ  ..........
                      
                  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን  ይባርክ


ESAT WAZA ENA KUMENGER April 14 2013


Sunday, April 14, 2013

ESAT Ye Ehud Weg April 14 2013 Ethiopia


የኢትዮጵያ አደገኛ የፖከቲካና ማህባዊ ጉዞ ያሳሰባቸዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እራሰቸዉን በህቡዕ እያደራጁ መሆኑ ተነገረ




ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ባለፉት ሃያ አንድ አመታት የተከተላቸዉ የፖለቲካ፤የኤኮኖሚና ማህበራዊ ፖሊሲዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ያደረሰዉ ጥፋትና አሁንም አገሪቱ የምትጓዝበት አደገኛ አቅጣጫ ያሳሰባቸዉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እራሳቸዉን በህቡዕ እያደራጁ መሆኑን አንድ ምስራቅ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኘዉ የዚሁ የህቡዕ ድርጅት ህዋስ መሪ ከግንቦት ሰባት ድምጽ ጋር ባደረጉት የስልክ ምልልስ ገለጹ። እኚህ ለደህንነታቸዉ በመስጋት ቃለምልልሳቸዉ በሬድዮ እንዳይደተላለፍ የጠየቁን ከፈተኛ የጦር መኮንን በህቡዕ የመደራጀቱ እንቅስቃሴ ሠራዊቱ በብዛት በሚገኝባቸዉ ቦታዎች ሁሉ እየተካሄደ ሲሆን በቅርብ ግዜ ዉስጥ ከሌሎች ለለዉጥ ከሚታገሉ ሀይሎች ጋር በመሆን ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚጅምሩ ተናግረዋል።


የዚህ “አገርህን አድን” በሚል ስያሜ የሚጠራዉ አገር ወዳድ ቡድን አባላት የወያኔ ደህንነት የሚያደርግባቻዉን የሃያ አራት ሰአት ክትትል ጥሰዉ ለመጀመሪያ ግዜ የተሰባሰቡት ከአራት አመታት በፊት ሲሆን ያሰባሰባቸዉም ወያኔ ሠራዊቱ ዉስጥ የሚከተለዉን ጭፍን የዘረኝነት ፖሊሲ ለመቋቋም እንደሆነ ታዉቋል። ሆኖም ይህ በ“አገርህን አድን” ቡድን ስር በመደራጀት ላይ የሚገኘዉ ሠራዊት አላማ የሠራዊቱን መብትና ነጻነት አስጠብቆ ወደ ሠፈሩ መመለስ ሳይሆን የቡድኑ ተቀዳሚ አላማ ለህዝብ በገባዉ ቃል መሠረት ኢትጵያንና ህዝቧን ከወያኔ ዘረኝነትና ከፋፍለህ ግዛዉ ፓሊሱ ማዳን ነዉ ሲሉ የቡድኑ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

የወያኔ አገዛዝ በአማራዉ ወገናችን ላይ የሚያደርሰዉን ጥቃት በቅርብ እየተከታሉት እንደሆነ የተናገሩት እኚሁ ቃል አቀባይ እንደዚህ አይነቱን የማን አለብኝነት ወንጀልና ባጠቃላይ የወያኔ ዘረኞች በግልጽ የሚያካሄዱት መብት ረገጣ፤ግድያ፤ዝርፍያና የአገርን ብሔራዊ ጥቅም ለባዕዳን አሳልፎ መስጠት ወያኔ አስካልተወገደ ድረስ የማይቆም በመሆኑ ያለን አማራጭ በቻልነዉና በምናዉቀዉ መንገድ ሁሉ ወያኔን ለማስወገድ መታገል ዋናዉ አላማችን ነዉ ብለዋል።

በመጫረሻም ከነማን ጋር ትሰራላችሁ ተብሎ የተጠየቁትን ጥያቄ ሲመልሱ ዛሬ አገራችን ለመዉደቅ በመንገዳገድ ላይ በምትገኝበት ወቅት ያለን አማራጭ አልገዛም ካለና የእኩሎች አገር የምትሆን ኢትዮጵያን ለመገንባት ፍላጎቱና ቆራጥነቱ ካላቸዉ ወገኖች ጋር ሁሉ አብረን እንታገላለን ብለዋል። በአሁኑ ወቅት አያሌ ኢትዮጵአዉያን ወያኔን ለመታገል መሳሪያ ካነሱ ወገኖች ጋር በየቀኑ እየተቀላቀሉ ስለሆነ የኛም አላማ የትግል ስልትና የተለየ የትግል ቦታ ሳንመርጥ ወያኔን ያዋጣናል ባልነዉ ስልትና ይመቸናል ባልነዉ ቦታ ሁሉ እስከእለተ ሞቱ እንታገለዋለን ብለዋል።

Saturday, April 13, 2013

Ethiopia: Regime tries to break morale of jailed female journalist





In a protest letter to Birhan Hailu, Ethiopia's justice minister, Joel Simon, CPJ's Executive Director asked that Alemu, whose health has reportedly deteriorated since being held on terrorism charges, to withdraw the threat of placing her in solitary confinement.


















Friday, April 12, 2013

በብሄር ከፍፈሎ መግዛት የዛገ ፖሊሲ ነዉ!



በሀገራችን ኢትዮጵያ የዜጎች የመዘዋወር፣ ንብረትን የማፍራት፣ የመኖር፣ የመናገር፣ የመምረጥ እና የመመረጥ መብቶች የሚወሰነው በጥቂት የህወሃትና ጀሌ ባለስልጣኖች መልካም ፈቃድ እንጅ በመሰረታዊ የሰው ልጆች መብት ድንጋጌ አይደለም።

በሩዋንዳ የተፈጸመው የሰውልጅን ዘር የማጥፋት ድርጊት፣ በሀገራችንም ኢትዮጵያ በህወሃት ኢህአዴግ አማካኝነት እየታየ ነው። ዜጎች በማንነነታቸው ከየት አካባቢ/ ብሄር/ ዘር ማንዘር ነው የመጣኸው/ሽው? እዚህ ለመኖር፣ ለመስራት፣ ንብረት ለማፍራትና ለመሳሰሉት የመኖሪያ ፈቃድ አለህ/ሽ ወይ? በሚል ብሄርን ከፋፍሎ መለያ በመስጠት ተከባብሮ የኖረን ህዝብ በትውልድ ሀገሩ እርስ በርሱ ለማጋጨት እየተደረገ ያለው የዛገ የፖለቲካ ፖሊሲ የሀገራችንን ህልውና እየተፈታተነ ነው።
በብሔር ብሔረሰብ ክፍፍል ላይ የተመሰረተ ዘርን በማጥፋት ፖለቲካ የተጠመዱት ወያኔዎች፣ እንደ ሰደድ እሳት በአገራችን ዜጎች ላይ ያላቸውን ጥላቻ ከወዲያ ወዲህ እየሄዱ ያሳዩናል። በተለይም በአማራው የተጀመረው የበቀል ርምጃ ቀጥሎና ተባብሶ የጥፋት በትራቸው የገረፋቸው የኦጋዴን፤ የጋምቤላ፤ የደቡብ ክልል፤ የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የዋልድባ አባቶች የቅርብ ግዜ በደሎች ሳይረሱ ከበደል ላይ በደል፣ ከጩኸት ላይ ጩኸት እየጨመረ በማን አለብኝነት የጀመረውን ዘርን የማጥፋት አባዜ ቀጥሎበታል።
የዜጎችን ሰዋዊ መብት ወያኔ በጠበንጃ ሃይል ጉልበት በመተማመን ንብረትን ቀምቶ፤ ነፍሰጡርንና አራስን አፈናቅሎ፣ ህጻናትን ሜዳ ላይ በትኖ ማባረር፣ የድብደባና የግድያ ወንጀሎች በአማራው ሕዝብ ላይ መፈጸሙ አዲስ ያልሆነና ከበፊቱም የነበረውን የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ የዛገ ፖሊሲ ተግባራዊ እያደረጉት እንደሆነ ያሳየ ምልክት ነው። ይህ ዓይነቱ ዘግናኝ ወንጀል በተለያዩ ጊዜያትና አካባቢዎች በተለይም በኦጋዴን፣ በአኝዋክ፣ በኦሮሞ፣ በደቡብ፣ በአፋር፣ በሙርሲ እና በሌሎችም የማህበረሰባችን ክፍል ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ተፈጽሟል። አሁንም እየተፈጸመ ነው።
ህወሃት/ኢህአዴግ ይህንን የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈጽመበት ዋናው ምክንያት የአንድን ዘር የፓለቲካ፣ የኤኮኖሚና ወታደራዊ የበላይነቱን ለማስጠበቅ ስለሆነ፤ ለዚህ እኩይ ዓላማው መሳካት እንቅፋት ናቸው ብሎ በሚገምታቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ ወደፊትም ተመሳሳይ እርምጃ ከመፈጸም እንደማይቆጠብ እየነገረን ነው።
ይሁን እንጅ ወያኔና አበሮቹ ይህ ዘርን የማጥራት (Ethinc Cleansing) ወንጀል ሲፈጽሙ በየትኛውም ግዜና ዘመን ከተጠያቂነት ወይም በወንጀል ከመፈለግ እንደማይድኑ የተረዱ አልመሰለንም።
የወያኔን የዘር ማጥራት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚቃወመዉ እና በተለይም አማራዉ ከትውልድ ቀዪው በግዳጅ ተባሮ ለጎዳና ተዳዳሪነት ሲዳረግ የተመለከተ የአካባቢዉ ነዋሪ ህዝብ በፍጹም ወያኔን ያልደገፈና ያልተባበረ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ማፈናቀሉን ተቃዉሞ ተፈናቃዮቹን እንባ እያፈሰሰ፣ ለስደት ጉዟቸው ይሆን ዘንድ ራሱ አማራው አርሶና ቆፍሮ እሸት ካፈራበት ማእድ ወይም የዛሬ የበይ ተመልካች ከሆነበት ማሳ ስንቅ እየቋጠረ ነበር የሸኛቸው።
ለብዙ አመታት አብረዉ ከመኖራቸዉ የተነሳ የአብሮ መኖር ኢትዮጵያዊነት መንፈስ የገነቡና በጋብቻና በማህበራዊ ኑሮ የተሳሰሩ ዜጎች በወያኔ ፖሊሲ ምክንያት ሳይፈልጉ ሲለያዩ ማየት ምን ያህል አሳዛኝ መሆንን የኢትዮጵያ ህዝብ ይረዳል።
በሌሎች አለማት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት የስደት ሀገር የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት በፍርድ ቤት እና በተለያዩ ሚዲያዎች የመኖር መብታቸው ይከበር ዘንድ ሲከራከሩ፤ እኒህ ምስኪን የሀገራችን ዜጎች ግን በትውልድ ሀገራቸው፣ መንደራቸው የመኖሪያ ፈቃድ ተነፍጓቸው፣ ይህንንም እንዳይጠይቁ ሆነው ይባረራሉ።
ታዲያ ይህንና ሌሎች በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደሎች በጋራ ሆነን ለመታገል እንዲሁም ለአለም ድምጻችን ለማሰማት ኢትዮጵያዉያን ለብዙ ግዜ በትላልቆቹ የአገራችን ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም መያዝ አቅቶን ብዙ ዘመን ቆይተናል:: አሁን ግን ሌላ ቢቀር ከምን ግዜም በተሻለ ሁኔታ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች በኢትዮጵያ አንድነትና በዚህ አንድነት ዉስጥ መመስረት ሳለለበት የዲሞክረሲ ስርአት የጋራ አመካከት መጥቷል።
ይህንን ኢትዮጵያዊ አንድነት የጋራ ትግልና የዜጎችን ሁለንተናዊ መብት የማስጠበቅ የነጻነት ትግልን ትብብር እውን እንዲሆን ባለፈው ግዜ በከማል ገልቹ የሚመራዉ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር  ከሁለት አመት በፊት የወሰደዉ የአቋም ለዉጥ እና በቅርቡ ደግሞ በኦነግ ታሪክ ዉስጥ ከፍተኛ ቦታ የነበራቸዉ ሰዎች የወሰዱት ተመሳሳይ አቋም የሚያሳየዉ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዉያን በብሄር ከፋፍለህ ቅጣዉ ፖሊሲ ከኢትዮጵያ መወገድ እንዳለበት እና በሁሉም ወገናችን የሚደርሰው በደል ሰቆቃና ስደት የሁሉም ፖለቲካ ድርጅቶች ጉዳይ መሆኑንና በጋራ ሆነን የዛገንየወያኔን የዘር ማጥራት ፖሊሲ የምናስቆበት፣ ለአንዴ ለመጨረሻ ግዜ ታግለን የምናስወግድበት ሰአት ላይ ነን።
በተጨማሪ ወያኔ አገራችንን በብሄር መነጽር ብቻ የሚመለከትበትን መንገድና የሚሸርበዉ ሴራ በብሄር የተደራጁ ድርጅቶችንም እያንገሸገሻቸዉ መምጣቱን፣ ወቅቱ የሚጠይቀውን ወያኔን የማስወገድ እና ኢትዮጵያን የማዳን የትግል ደወል ጥሪ ላይ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው።
ስለሆነም ግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲና ነጻነት ንቅናቄ በህዝባችን እየደረሰ ያለውን መፈናቀልና እልቂት ለማስቆም የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል። የዲሞክራሲ ሃይላት ድርጅቶችም ሆነ የሀገራችን ወጣቶች፤ የአማራውና የተቀረው ህዝባችን ጮኸትና ዋይታ በደልና ሰቆቃ በሁሉም የሀገራችን ህዝቦች እየደረሰ ያለ ጥቃት ነውና ለጥሪያቸው የማያዳግም መልስ ለመስጠት ትግሉን  ትቀላቀሉ ዘንድ ጥሪያችን ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Wednesday, April 10, 2013

ወደ ቅሊንጦ እስርቤት ያመሩት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እስረኞችን እንዳይጠይቁ ተከለከሉ


አቶ አስራት ጣሴ፣ አቶ ሙላት ጣሰው እና አቶ ዳንኤል ተፈራ ሚያዚያ 1 ቀን 2005 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከከተማ ውጭ ወደሚገኘውና መንገዱ እጅግ አስቸጋሪ ወደ ሆነው ቅሊንጦ እስርቤት  እስረኞችን ለመጠየቅ ቢሄዱም ተፈትሸውና መታወቂያ አስይዘው ወደ ውስጥ ገብተው ለ45 ደቂቃ የሚሆን እንዲጠብቁ ተስፋ ከተሰጣቸው በሁዋላ ሃላፊው የሉም ለስብሰባ ስለወጡ ስልክ አያነሱም በሚል ተራ ሰበብ እንዳይገናኙ መደረጋቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አስታውቋል፡፡
የህዝብ ግንኙነቱ እንደገለፀው አመራሩ ወደ እስርቤቱ በር እንደደረሱ መታወቂያ ከጠየቋቸው የእለቱ ሰራተኞች፡- ‹‹መጠየቅ ምትፈልጉት ግንቦት ሰባቶችን ነው ወይ?›› የሚል አስደንጋጭ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡

 አመራሮችም ‹‹አይ እኛ የምንጠይቀው ግንቦት ሰባቶችን ሳይሆን የፖለቲካ እስረኞችን ነው፡፡ እናንተም እንደዚህ ብላችሁ መጥራታችሁ ትክክል አይደለም›› በማለት አነጋገራቸውን እንዲያርሙ አሳስበዋል፡፡ ሰራተኞችም፡- ‹‹እኛ ሁልጊዜም ግንቦት ሰባቶች ነው የምንላቸው›› ካሉ በኋላ መታወቂያ ይዘውና ፈትሸው ወደ ውስጥ እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡

አራቱ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ቂሊንጦ እንዲያመሩ ያደረጋቸው በተደጋጋሚ በፖለቲካ እስረኞች ይደርሳል የሚባለውን የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት እንዲሁም ግፍና በደል ይደርስብናል የሚል ጥቆማ ከእስረኞች በመድረሱና እሱንም ከእስረኞች ለመስማትና አጠቃላይም ስላለው አያያዝ ለመወያየት እንደሆነ የህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል፡፡ ነገርግን የሚመለከታቸው አካላት ማነን መጠየቅ እንደሚፈልጉ ከመዘገቡ በሁዋላ ጠብቁ በማለት እንደምንገምተው እላይ ካሉ ባለስልጣናት ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በሁዋላና ብዙ ከጠበቁ በሁዋላ መጠየቅ እንደማይችሉ፣ ምክንያቱም ሃላፊው በመውጣታቸውና ስልክ ባለማንሳታቸው እንደሆነ የሚል ሰበብ በመናገር የአንድነት አመራሮች ጊቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል፡፡

ይህ ድርጊትም አሁንም ገዥው ፓርቲ መሰረታዊ የሆኑ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማፈን ለመቀጠል መቁረጡን ከሚያሳዩ ሁነቶች አንዱ ነው በማለት የህዝብ ግንኙነት ይገልፃል፡፡

አቶ አስራት ጣሴ፣ አቶ ሙላት ጣሰው እና አቶ ዳንኤል ተፈራ ሚያዚያ 1 ቀን 2005 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከከተማ ውጭ ወደሚገኘውና መንገዱ እጅግ አስቸጋሪ ወደ ሆነው ቅሊንጦ እስርቤት  እስረኞችን ለመጠየቅ ቢሄዱም ተፈትሸውና መታወቂያ አስይዘው ወደ ውስጥ ገብተው ለ45 ደቂቃ የሚሆን እንዲጠብቁ ተስፋ ከተሰጣቸው በሁዋላ ሃላፊው የሉም ለስብሰባ ስለወጡ ስልክ አያነሱም በሚል ተራ ሰበብ እንዳይገናኙ መደረጋቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አስታውቋል፡፡

የህዝብ ግንኙነቱ እንደገለፀው አመራሩ ወደ እስርቤቱ በር እንደደረሱ መታወቂያ ከጠየቋቸው የእለቱ ሰራተኞች፡- ‹‹መጠየቅ ምትፈልጉት ግንቦት ሰባቶችን ነው ወይ?›› የሚል አስደንጋጭ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡ አመራሮችም ‹‹አይ እኛ የምንጠይቀው ግንቦት ሰባቶችን ሳይሆን የፖለቲካ እስረኞችን ነው፡፡ እናንተም እንደዚህ ብላችሁ መጥራታችሁ ትክክል አይደለም›› በማለት አነጋገራቸውን እንዲያርሙ አሳስበዋል፡፡ ሰራተኞችም፡- ‹‹እኛ ሁልጊዜም ግንቦት ሰባቶች ነው የምንላቸው›› ካሉ በኋላ መታወቂያ ይዘውና ፈትሸው ወደ ውስጥ እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡

አራቱ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ቂሊንጦ እንዲያመሩ ያደረጋቸው በተደጋጋሚ በፖለቲካ እስረኞች ይደርሳል የሚባለውን የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት እንዲሁም ግፍና በደል ይደርስብናል የሚል ጥቆማ ከእስረኞች በመድረሱና እሱንም ከእስረኞች ለመስማትና አጠቃላይም ስላለው አያያዝ ለመወያየት እንደሆነ የህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል፡፡ ነገርግን የሚመለከታቸው አካላት ማነን መጠየቅ እንደሚፈልጉ ከመዘገቡ በሁዋላ ጠብቁ በማለት እንደምንገምተው እላይ ካሉ ባለስልጣናት ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በሁዋላና ብዙ ከጠበቁ በሁዋላ መጠየቅ እንደማይችሉ፣ ምክንያቱም ሃላፊው በመውጣታቸውና ስልክ ባለማንሳታቸው እንደሆነ የሚል ሰበብ በመናገር የአንድነት አመራሮች ጊቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል፡፡

ይህ ድርጊትም አሁንም ገዥው ፓርቲ መሰረታዊ የሆኑ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማፈን ለመቀጠል መቁረጡን ከሚያሳዩ ሁነቶች አንዱ ነው በማለት የህዝብ ግንኙነት ይገልፃል፡፡

.ESAT Daily News Amsterdam April 09 2013 Ethiopia .


ESAT Daily News Amsterdam April 09 2013 Ethiopia

Monday, April 8, 2013

የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከመንግስት ሸሽተው ተሰደዱ!



Araya na mastwalየፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የሆነችው ማስተዋል የህትመት ስራ ድርጅት ስራ አስኪያጅ የነበረው ማስተዋል ብርሃኑ እና የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የሆነው አርአያ ጌታቸው መንግስትን ሸሽተው ከሀገር ተሰደዱ!
ማስተዋል ብርሃኑ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚያዘጋጃት ፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የነበረ ሲሆን በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኋላ ፍትህ፤  ”ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሞቱስ ለምን ሞቱ ትላለች…” ተብላ ከሰላሳ ሺህ ኮፒ በላይ እንድትቃጠል ቢደረግም መንግስታችን በቅጡ ስላልተደሰተ በአዘጋጁ ተመስገን እና በአሳታሚው ማስተዋል ብርሃኑ ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል፡፡ (የማይታወቅ ከሆነ አሁን ይታወቅ)
እነ ማስተዋል ብርሃኑ በተከሰሱበት በዚህ ክስ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ተለቀው ለሚያዝያ 17 2005 የተቀጠሩ ሲሆን በክሱ ጥፋተኛ ከተባሉ እስከ አስራ ሰባት አመት እስር ይጠብቃቸዋል፡፡ ማስተዋል ሸሽቶ ከመውጣቱ በፊት የመንግሰት ደህነነት ሰዎች በተደጋጋሚ እየተከታተሉ የእጅ ስልኩን በመንጠቅ ከማን ጋ እንደተደዋወለ እና ምን አይነት መልዕክት (ሜሴጅ) እንደተለዋወጠ በግድ ያዩበት እንደነበር ነግሮኛል፡፡